ANRS Planning Institute

  • Home
  • ANRS Planning Institute

ANRS Planning Institute Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ANRS Planning Institute, Government Organization, Bahir Dar, .

ለመለው የሀገራችንና ክልላችን ህዝቦች እንዲሁም የአብክመ ፕላን ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች እንኳን ለአዲሱ ዓመት (2019) በሠላም አደረሰችሁ አደረሰን!!አዲሱ ዓመት የሀገራችንና የክል...
10/09/2026

ለመለው የሀገራችንና ክልላችን ህዝቦች እንዲሁም የአብክመ ፕላን ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች እንኳን ለአዲሱ ዓመት (2019) በሠላም አደረሰችሁ አደረሰን!!

አዲሱ ዓመት የሀገራችንና የክልላችን ከፍታ ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ

መልካም አዲስ ዓመት!!
ምትኩ አለማየሁ (ዶ/ር)
አብክመ ፕላን ኢንስቲትዩት
ዋና ዳይሬክተር

04/09/2026
27፣12፣2018 ዓ.ምባህርዳርየአብክመ ፕላን ኢንሰቲተዩት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም የእውቅና መድረክ እና የ2019 በጀት ዓመት የ2ወራት እቅድ አፈፃፀም የዞን አስተዳደር ፅ/ቤት...
02/09/2026

27፣12፣2018 ዓ.ም
ባህርዳር
የአብክመ ፕላን ኢንሰቲተዩት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም የእውቅና መድረክ እና የ2019 በጀት ዓመት የ2ወራት እቅድ አፈፃፀም የዞን አስተዳደር ፅ/ቤት እና የሪጆ-ፖሊታን ከተሞች አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣የተቋሙ አመራሮች፣ የቅ/ፅ/ቤት ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት ተጀምሯል።
እንዲሁም የተቋሙን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን ደንብና ልዩ ልዩ መመሪያዎች ከዞን እና ከከተሞች ለመጡ የአስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊዎች በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር በዶ/ር ምትኩ አለማየሁ ቀርቦ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

01/09/2026
የዞኖች፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና የከተማ አስተዳደር ጽ/ቤቶች አመራሮችና ሙያተኞች በፕላን ኢንስቲትዩት የሕግ ማዕቀፎች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና በ3 ማዕከሎች እየተሰጠ ይገኛል።በአማራ ክል...
18/08/2026

የዞኖች፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና የከተማ አስተዳደር ጽ/ቤቶች አመራሮችና ሙያተኞች በፕላን ኢንስቲትዩት የሕግ ማዕቀፎች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና በ3 ማዕከሎች እየተሰጠ ይገኛል።

በአማራ ክልል የፕላን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ምትኩ አለማየሁ(ዶ/ር) እንደገለጹት የተቋሙን የ2018 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ኦረንቴሽን መነሻ በማድረግ በደብረ ማርቆስ፣ በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች ሰፊ ዉይይት በማድረግ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል እንዲሁም ዉስንነት የታየባቸውን ተግባራት አሁን በያዝነው የዝግጅት ምዕራፍ በማረም ወደ ተሻለ አፈጻጸም መሻገር እንደሚገባ ገልጸዋል።

በ3ቱም የዉይይት ማዕከል በፕላን ደንቡ፣ በስፓሻልፕላን ዝግጅት የአሰራር ማንዋል፣ በሶሽዮ ኢኮኖሚ ጥናት፣ በወጭ መሸፈኛ ረቂቅ መመሪያና ተያያዥ ጉዳዮች ሰነዶችን በማቅረበ አመራሮችና ሙያተኞች በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ መደረጉን ዶ/ር ምትኩ ገልጸዋል።

የፕላን ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብርሃም አለማየሁ የስልጠና ሰነዱን ሲያቀርቡ እንደገለጹት የፕላን ዝግጅት ጤናማና ዘላቂ የከተማና የገጠር ማዕከላት ዕድገት እንዲኖር ማድረግ፣ የተረጋጋና የተመጣጠነ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መፍጠር እና ሕዝብን ያሳተፈ የመሬት አጠቃቀም ሥርዓት ለመዘርጋት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ባለሙያ አቶ አዲሱ አወቀ የካርታና የፕላን ዝግጅት ተግባራት መሠረታዊ ካርታዎችን በሳተላይት ኢሜጅና በመሬት ላይ ቅየሳ ማዘጋጀት፣ የከተማ መዋቅራዊ ፕላንና የስትራቴጂክ ፕላን ማዕቀፎችን መቅረጽ እንዲሁም ሕንፃዎችና የልማት ሥራዎች ከዕቅዱ ውጭ እንዳይከናወኑ መቆጣጠር ነው ብለዋል፡፡
የፕላንና የካርታ ዝግጅት እንዲሁም የሶሽዮ ኢኮኖሚ ሥራዎች በመሬት አጠቃቀም፣ በዕድገት አቅጣጫና በሕዝብ ተሳትፎ ላይ ተመስርቶ የከተሞችንና የገጠር ቀበሌ ማዕከላትን ልማት ለመምራት የሚያስችል መሆኑን አቶ አዲሱ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

አመራሮችና ሙያተኞች እንደገለጹት ከላይ እስከ ታች ያለዉን የኢንስቲትዩቱን አፈጻጸም የላቀ ለማድረግ የድጋፍና ክትትል ስራ ማጠናከር፣ የቅንጅት ስራን ማዳበር፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና በየደረጃው ለሚገኙ ሙያተኞችና አመራሮች መስጠት፣ የሪፖርት ግንኙነትና ግብረ መልስ ማጠናከርና የልምድ ልዉዉጥ ስራዎችን ማካሄድ የመሳሰሉት ሃሳቦች ተነስተዉ በዶ/ር ምትኩ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫዎችና የሥራ መመሪያም ተሰጧል።

በአማራ ክልል የፕላን ኢንስቲትዩት ከሚያከናዉናቸዉ  አበይት ተግባራት ባሻገር በክረምት በጎ ፈቃድ ማኅበራዊ ኅላፊነቱን ለመወጣት ያለዉን ድጋፍ  ለመግለጽ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለተለያ...
17/08/2026

በአማራ ክልል የፕላን ኢንስቲትዩት ከሚያከናዉናቸዉ አበይት ተግባራት ባሻገር በክረምት በጎ ፈቃድ ማኅበራዊ ኅላፊነቱን ለመወጣት ያለዉን ድጋፍ ለመግለጽ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ ክፍለ ከተሞች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ ዜጎች አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ በማሰብ ለ50 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ አስረክቧል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ምትኩ አለማየሁ በትምህርት ቁሳቁስ ርክክብ ወቅት እንደገለጹት ተቋሙ ማኅበራዊ ኅላፊነቱን ለመወጣት በክረምት ስራ ከያዛቸው ዕቅዶች አንዱ የትምህርት ቁሳቁስ ለመግዛት የሚቸገሩ ወላጆችን ለመደገፍ በማሰብ በባህር ዳር ከተማ ለጣና ክፍለ ከተማ፣ ለሽምብጥ ቀበሌና ለአማራ ሴቶች ፌዴሬሽን ያስረከቡ ሲሆን በየክፍለ ከተማዉና ቀበሌ ለተለዩ ተማሪዎች ደብተርና እስክርቢቶ የሚሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ተተኪ ትዉልድ ለመፍጠር ትምህርት ወሳኝ ድርሻ ያለዉ በመሆኑ አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች ለመደገፍ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በየደረጃው የሚገኙ የኢንስቲትዩቱ ቅርንጫፎች መሰል ተግባራትን በማከናወን ማኅበራዊ ኅላፊነታቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በመቀጠልም ኢንስቲቲዩቱ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና ለከተማ አስተዳደሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና የሰጠ ሲሆን የከተማ ፕላን ለዘመናዊነት፣ ለኢኮኖሚ ሽግግርና ለነዋሪዎች የተሻለ ህይወት መፈጠር ያለውን ወሳኝ ሚና በማንሳት፤ ከተሞች የሚያዘጋጁት የ25 ዓመት ዕቅድ በማስረጃ የተደገፈ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። ፕላን የመሬት አጠቃቀምን፣ መሰረተ ልማትንና አረንጓዴ ልማትን የሚወስን ህግ መሆኑን ገልጸው፣ ተቋሙም "ስልጡን ፕላን ለተሻለ ህይወት" በሚል መሪ ቃል ፕላንን ለሰው ልጅ ጥቅም በማዋል ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ከተሞች የ85 በመቶ የሀገር ኢኮኖሚ ምንጭ በመሆናቸው እንደ ህጻን ልጅ እንክብካቤ እንደሚሹና በፕላን ካልተመሩ የህገ-ወጥ ድርጊት ማዕከል ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። በአንጻሩ ዘመናዊ ከተማ ማለት ነዋሪዎች ከ15 ደቂቃ ባልበለጠ ርቀት አገልግሎት የሚያገኙባት፣ ዲጂታል አሰራር የሰፈነባትና የመሬት መብት የተረጋገጠባት መሆኗን አብራርተዋል። ኢንስቲትዩቱ በአዋጅ ቁጥር 300/2017 የተቋቋመ ተቆጣጣሪ አካል (Regulatory Body) እንጂ ኦፕሬሽናል አለመሆኑን በማስገንዘብ፤ ዋና ተግባሩ ፕላን ማዘጋጀት፣ መተግበሩን መቆጣጠር፣ ኦዲት ማድረግና የፕላን ጥሰት ሲገኝ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢንስቲቲዩቱ የዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የሽዋስ ግርማ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
በመድረኩ በርካታ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧል።
በቀጣይ ቀናትም የተለያዩ ሰነዶች ቀርበዉ ዉይይት የሚደረግና የስራ መመሪያ የሚሰጥ ይሆናል።

17/08/2026
16/08/2026
12/08/2026

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Planning Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your organization to be the top-listed government service?

Share