13/10/2026
አስደሳች ዜና !!!
የፈለገ ህይወት አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ከCure Blindness ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በቀጣይ ከህዳር1-ህዳር 6/2019 ዓ/ም ድረስ ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ይሰጣል።
በዚህ መሰረት የቅድመ ልየታ ስራው
1. በአዴት ሞጣ ከጥቅምት 14 -15/2019 ዓ/ም
2.መራዊ ወረታ እና አንበሳሜ ጤና ጣቢያ ከጥቅምት 21-22/2019 ዓ/ም
3.ባህርዳር ፈለገ ህይወት አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ከጥቅምት 23-30/2019 ከየትኛውም አካባቢ ለሚመጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የልየታ ስራ ይሰራል።
ስለሆነም በርካታ ወገኖቻችን የአይን ብርሀናቸው እንዲመለስ ለማድረግ በዚህ ልምድ ባላቸው እንቁ ባለሙያወች ቡድን በሚሳተፉበት ነፃ የአይን ዘመቻ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እናድርግ።
መረጃውን ለሁሉም ወገኖቻችን እንዲደርስ በማድረግ የድርሻችን እናግዝ።