Ethio animal health network

Ethio animal health network የባለሙያወችን ክህሎትና ግንዛቤን ለመፍጠር ለማሻሻል እንዲሁም የሚወጡ አዳዲስ የቅጥር ማስታወቂያወችን ተደራሽ ለማድረግ የተከፈተ ነው።

የተሻሻለው አዲሱ የደንብ ልብስ መመሪያ የእ/ጤና ባለሙያወች
01/10/2026

የተሻሻለው አዲሱ የደንብ ልብስ መመሪያ የእ/ጤና ባለሙያወች

30/09/2026

ሰላም እንዴት ናችሁ በአማራ ክልል የደንብ ልብስ መመሪያ በአዲስ መልክ ታች ወረዳ ድረስ እንደወረደ መረጃ ደርሶናል። በቅርቡ post እንደምናደርግላችሁ እናሳውቃለን በክልሉ ያላችሁ ባለሙያወች መረጃወችን ብታካፍሉን መልካም ነው።

የዩንቨርሲቲዎች የቅበላ መቁረጫ ነጥብ ከታች በተቀመጠው መልኩ ይፋ ሆኗል
14/09/2026

የዩንቨርሲቲዎች የቅበላ መቁረጫ ነጥብ ከታች በተቀመጠው መልኩ ይፋ ሆኗል

የከፍተኛ ተቋማት ካላንደር ከታች በምታዩት መልኩ ፕሮግራም ተሰርቶለታል
11/09/2026

የከፍተኛ ተቋማት ካላንደር ከታች በምታዩት መልኩ ፕሮግራም ተሰርቶለታል

vaccancy at dilla university
02/09/2026

vaccancy at dilla university

Annual conference of EVA
12/08/2026

Annual conference of EVA

09/08/2026

ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የ vet ቤተሰቦች ክረምት እንዴት ነው ያው በነዚህ ወራት ብዙም ስራ አይኖርም። የእ/ጤና ባለሙያወች ከሚለፍት ስራ አንፃር በተለይ ወረዳና ቀበሌ አካባቢ የሚከፈላቸው ክፍያ ተመጣጣኝ ነው ትላላችሁ ? መፍትሄውስ? ሀሳባችሁን አጋሩን

የእንስሳት ሀኪሙ ዶክተር ካሳሁን የሙያና የርኅራኄ ውሳኔ!ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም፤ በባንጃ ወረዳ ቅዳማጃ ከተማ የሚገኙት የእንስሳት ሐኪም ዶክተር ካሳሁን ልብሳቸውን ቀይረው ወደ እንጅባ...
01/08/2026

የእንስሳት ሀኪሙ ዶክተር ካሳሁን የሙያና የርኅራኄ ውሳኔ!

ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም፤ በባንጃ ወረዳ ቅዳማጃ ከተማ የሚገኙት የእንስሳት ሐኪም ዶክተር ካሳሁን ልብሳቸውን ቀይረው ወደ እንጅባራ ለማቅናት በዝግጅት ላይ ነበሩ። የዕለቱ መርሃ ግብራቸው በዞኑ አጠቃላይ የሥራ ግምገማ ስብሰባ ላይ በመገኘት የሚያልፍ ነበር።

ነገር ግን ቦርሳቸውን አዘጋጅተው ከበሩ ሲደርሱ፣ በክሊኒኩ ደጅ ድንገት የቆመችው አይሱዙ መኪና የዕለቱን ውሏቸውን ሙሉ በሙሉ ቀየረችው። መኪናዋ ከጓንጓ ወረዳ ስጋዲ ቀበሌ ለሰዓታት ተጉዛ የደረሰች ሲሆን፣ በመኪናው ላይ ተጭና የመጣችው ደግሞ በከባድ የወሊድ ምጥ ስትሰቃይ የቆየች ላም ነበረች።

የላሟ ባለቤቶች የነበራቸው ተስፋ መቁረጥና ጭንቀት በዓይኖቻቸው ላይ በግልጽ ይታይ ነበር፤ ሐኪሙን የተመለከቱበት መንገድም "እባክዎን ታደጉን" የሚል አቅም ያጣ ጥሪ ነበረው።በዚያች ቅጽበት ዶክተር ካሳሁን በሁለት ውሳኔዎች መካከል ቆሙ ፤በአንድ በኩል የሚጠብቃቸው አስተዳደራዊ የስብሰባ ግዴታ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በፊታቸው የተደቀነ አስቸኳይ የሕይወት አድን ጥሪ።

ነገር ግን ሐኪሙ ለረጅም ጊዜ አልተወዛወዙም። "የዚችን ላም ሕይወት ማዳን ማለት የዚህን አርሶ አደር ቤተሰብ ኑሮ መታደግ፣ የሕዝብንም ተስፋ ማቀለም ነው" በሚል ጽኑ ሙያዊና ሰብአዊ ውሳኔ የስብሰባ ጉዟቸውን ሰርዘው ወዲያውኑ የስራ አልባሳታቸውን ቀየሩ የላሟን ህይወት ወደመታደግ ገቡ።

የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራው እንደጠቆመው ላሟ ምጥ ከተያዘች ከ12 ሰዓታት በላይ አልፎታል። ጽንሱ በማህፀን ውስጥ የተሳሳተ አቀማመጥ በመያዙ (Dystocia) ምክንያት ሕይወቷ በአደገኛ ሁኔታ ላይ ወድቆ ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ የጥጃው ሕይወት አልፎ የነበረ ቢሆንም፣ የላሟን ሕይወት ለማዳን ግን አንድ መንገድ ብቻ ነበራቸው ፤አስቸኳይ የቀዶ ህክምና (Caesarean Section) ማድረግ።

ዶክተር ካሳሁን በሰከነ ሙያዊ ብቃት፣ በከፍተኛ ጥንቃቄና በርህራሄ የቀዶ ጥገና ሕክምናውን አከናወኑ። ጥጃውን ማጣት አንጀት የሚበላ ቢሆንም፣ የላሟን ሕይወት ግን ከተደቀነባት የሞት አደጋ ማዳን ተቻለ። አሁን ላይ ላሟ በጥሩ ጤንነት ላይ ትገኛለች።

ዶክተር ካሳሁን ያንን ውጥረት የሞላበት ውሎ ሲያስታውሱ፡ "በዞኑ አጠቃላይ የሥራ ግምገማ ላይ መገኘት ባለመቻሌ ቅር ቢለኝም፣ በተግባር ግን ከዚያ የሚበልጥ አርኪ ሥራ ሠርቻለሁ። የእንስሳት ሕክምና ትዕግስትን፣ ጉልበትንና ጊዜን የሚጠይቅ የርህራሄ ሙያ ነው" ይላሉ።

አክለውም ፣ የእንስሳት ሀብት የሀገራችንና የሕዝባችን የኢኮኖሚ አከርካሪ በመሆኑ ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ያሳስባሉ።በመጨረሻም ለዚህ ደረጃ እንድደርስ መሠረት ሆነኛል ላሉት ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና ፋከልቲ፣ እንዲሁም ዘወትር ላልተለየቸው ድጋፍ ለአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት መምሪያ የከበረ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ (ማለዳ መረጃ)

30/07/2026

ለኢትዮጵያ እንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (EVA)
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፦ የአባላቱና የምሩቃኑ የሥራ አጥነት ስቃይና በደል እያየለ በመምጣቱ ማኅበሩ ድምፅ እንዲሆንልንና ከተጠያቂ አካላት ጋር እንዲያነጋግረን መጠየቅ

ለተከበሩ ለሚመለከታችሁ የማኅበሩ ፕረዝደንትና ስራ አስፈፃሚ አካላት፤

የኢትዮጵያ እንስሳት ሐኪሞች ማኅበር የሙያውን ክብር የመጠበቅና የባለሙያዎችን መብትና ጥቅም የማስከበር ሕጋዊና ሞራላዊ ኃላፊነት አለበት። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሙያው ተተኪና ተስፋ የሆንን በርካታ ምሩቃን በሥራ አጥነት አለንጋ እየተገረፍንና በከፍተኛ ማኅበራዊ ሥቃይ ውስጥ እየኖርን፣ ማኅበሩ ይህንን በደል በዝምታ መመልከቱ በእጅጉ አሳዝኖናል።

ከፍተኛውን የሕይወትና የገንዘብ መስዋዕትነት ከፍለን፣ አስቸጋሪውን የሕክምና ትምህርት ጨርሰን ስንወጣ የገጠመን የሥራ ስምሪት መዘጋት፣ ሙያችንን እንድንጠላና በተማርንበት ሀገር ላይ እንድንደናገጥ አድርጎናል። በየቀኑ በሥራ አጥነት የምናሳልፈው ሕይወት የስነ-ልቦና ጤናችንን እያናጋው፣ ወደ ተስፋ መቁረጥና ወደ ተለያዩ ሱሶች እየመራን ይገኛል። የሙያው ክብር የሚጠበቀው በመጀመሪያ ባለሙያው ሥራ አግኝቶ በክብር መኖር ሲችል ነው።

ማኅበሩ የእኛን ስቃይና በደል እንደ ራሱ ጉዳይ አድርጎ በመውሰድ፣ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ከግብርና ሚኒስቴርና ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ጋር ጠንካራ የሙግትና የውይይት መድረኮችን መፍጠር ነበረበት። የወጣቱ ባለሙያ መደቆስ የራሱ የማኅበሩም መዳከምና የሙያው መሞት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ስለሆነም፣ ማኅበሩ በአስቸኳይ የዚህን የተማረ የሰው ኃይል የሥራ እጥነት ችግር አጀንዳ አድርጎ በመያዝ፣ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር የውይይት መድረክ በማዘጋጀት፣ ድምጻችንን እንዲያሰማልንና ፍትሕ እንድናገኝ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ከምስጋና ጋር!

ምንጭ (ከባለሙያወች የተወሰደ)

10/07/2026

"የዲግሪ ማስረጃ ማረጋገጫና የመውጫ ፈተና አዲስ መመሪያ (ከ2010 - 2015 ዓ.ም)"

ይህ መመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ በማንኛውም የመንግስት እና የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ከመስከረም 2010 ዓ.ም እስከ 2015 ዓ.ም የተመረቁ ተመራቂዎችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን፥ ዝርዝር አፈጻጸሙ እንደሚከተለው ነው፦

1. የመውጫ ፈተና ሳይወስዱ ለተመረቁ (የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ)
ማንነታቸው፦ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ ዲግሪ (BA/BSc)፣ የሁለተኛ ዲግሪ (MA/MSc) እንዲሁም የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) የያዙ ተመራቂዎች።

የማረጋገጫ መስፈርት፦ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት፥ ባሉበት የትምህርት ደረጃ (ለBA፣ MA እና PhD) የተዘጋጀውን ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ ብቻ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል፡፡

2. ከዲፕሎማ/ቲቪቲ (TVET) ተነስተው የመጀመሪያ ዲግሪ ለሰሩ ተመራቂዎች
ይህ ክፍል በቀድሞው ዲፕሎማ (12+2)፣ በ10+3 ወይም በቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 (Level 4) ስልጠና አጠናቀው፥ ትክክለኛነቱ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ (ETA) ወይም በፌደራል/ክልል ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ የተረጋገጠ ኦሪጅናል ማስረጃ እና ትራንስክሪፕት ያላቸውን ያጠቃልላል።

እነዚህ ተመራቂዎች የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC) ሳይኖራቸው የመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው ከተመረቁ ማስረጃቸው የሚረጋገጠው በሚከተለው ሁኔታ ነው፦

የመግቢያ መስፈርት ማሟያ ሁኔታዎች፦

ለዲግሪ መግቢያ መስፈርት የተቀመጠውን የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC) ፈተና ሳይወስዱ ዲግሪ ተምረው የተመረቁትን፣ ወይም

ለዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC) ፈተና የወሰዱ ተመራቂዎችን ያጠቃልላል፡፡

የማረጋገጫ መስፈርት፦ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ይህ መመሪያ እስከተሻሻለበት ጊዜ ድረስ የተመረቁ እና የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፉ ከሆነ ብቻ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል።

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio animal health network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share