Goshu Endalamaw Wondimagegn

Goshu Endalamaw Wondimagegn Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Goshu Endalamaw Wondimagegn, Government Official, Bahir Dar.
(1)

10/10/2026
ታላቋን ሀገር ኢትዮጵያ ክብሯን ጠብቃ በተጀመረው የለውጥ ጎዳና ወደ ከፍታዋ እና የብልፅግና ማማ እድትደርስ ለመምራት ለተጣለባችሁ ኃላፊነት እና እድል እንኳን ደስ አላችሁ!መልካም የስራ ዘመን...
08/10/2026

ታላቋን ሀገር ኢትዮጵያ ክብሯን ጠብቃ በተጀመረው የለውጥ ጎዳና ወደ ከፍታዋ እና የብልፅግና ማማ እድትደርስ ለመምራት ለተጣለባችሁ ኃላፊነት እና እድል እንኳን ደስ አላችሁ!
መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ!!!

08/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት አቅርበዋል።

#የመደመርመንግሥት

04/10/2026
29/09/2026
29/09/2026

ከተማችን ባህር ዳር ሰላማዊነቷን ጠበቃ ልማቷን በማፋጠን በየጊዜው ልዩ ልዩ ክልላዊ ፣ ሃገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች።
ውቢቷ ባህር ዳር በዛሬው እለትም የፊፋና የካፍን ደረጃ አሟልቶ በተሰራው የባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲዮም በኢትዮጵያ እና በሴኔጋል ብሄራዊ ቡድኖች መካከል የተካሄደውን የእግር ኳስ ጨዋታ በተሳካ ሁኔታ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ አስተናግዳለች ። በእለቱ የተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቅንጅት ለሰራችሁ በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በተለይም ለዝግጅት ኮሚቴዎች ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፣ የፌደራል ፣ የክልል እና የከተማችን የጸጥታ መዋቅር አባላት ፣ የኢትዮጵያ እና ለሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ፣ ለተከበረው የከተማችን ህዝብ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ። በተለይም ከተማውን ከልብ የሚወደውና ስፖርት አፍቃሪው የባህር ዳር ከተማ ወጣት ጨዋታውን በጨዋነት ከመደገፍ በተጨማሪ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁት ኃላፊነት የተሞላት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ከተማችን በቀጣይም ተመሳሳይ ሃገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን ለማዘጋጀት የምታደርገውን ጥረት አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ።

26/09/2026

እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ!

የመስቀል በዓል ተስፋና ብርሃን የታየበት፣ እውነት የተገለጠበት፣ የሕብረት እና የትብብር ምልክት ነው።

የመስቀል በዓል ልዩነቶችን በይቅርታ ተሻግረን በአብሮነት የምናከብረው የአንድነታችን ማሳያ ነው። ተራርቀው የቆዩ ወዳጅ ዘመዶች የሚገናኙበት ክብረ በዓል ነው።

የመስቀል ብርሃን የተገለጠው በሦስት መቶ መታት ጽናት እና በወራቶች ያልተቋረጠ ትግስትና ትጋት ነው። ይሄውም ራዕያችን እውን የሚሆነው ለእውነት በጽናትና በትግስት ጥረት ማድረግ ስንችል መሆኑን ያስረዳናል። ዛሬም ለጋራ ሰላማችን፣ ለሀገራችን ልማትና ብልፅግና በትብብር መትጋት ይኖርብናል።

ስለሆነም የደመራና መስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ሕዝባችን ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪየን እያቀረብኩ፤ በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንልን እመኛለሁ።

መልካም በዓል!

26/09/2026

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!

የመስቀል በዓል መስቀሉ ለ300 ዓመታት ከተደበቀበት የወጣበት በዓል ነው፡፡ መልካም የምሥራች የተነገረበትና ብርሃን የተገለጠበት በዓል ነው፡፡ በአንድ ዘመን የተሳሳቱ ሰዎች የፈጠሩትን ጥፋት፤ በሌላ ዘመን የተነሡ ተቆርቋሪ ሰዎች አስተካክለውታል፡፡ ልክ እኛ የባሕር በርን ለማስተካከል እንደምንሠራው፡፡

አስቸጋሪ የክረምት ወር አልፎ የመጸው ወር በሚብትበት ጊዜ የሚከበረው መስቀል የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ነው፡፡ በአንድ በኩል ችቦዎች ተደምረው ደመራውን ይገነባሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ያሉ ሁሉ በተመሳሳይ ቀን፣ በተመሳሳይ አከባበር፤ እንደየብሔረሰቡ ባህል ተደምረው በዓሉን ያከብራሉ፡፡

“የጎመን ምንቸት ውጣ፣ የገንፎ ምንቸት ግባ” እንደሚባለው ሁሉ፣2019 ዓመት፣ አስቀድሞ መውጣት የጀመረው የኢትዮጵያ የችግርና የፈተና ምንቸት ተጠቃልሎ የሚወጣበትና የብልጽግና ምንቸት በየቤታችን የሚገባበት ዓመት እንደሚሆን አምናለሁ፡፡
መልካም የደመራና የመስቀል በዓል ይሁን፡፡

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goshu Endalamaw Wondimagegn posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share