Bahir Dar City Adminstration Zonal Health Department

Bahir Dar City Adminstration Zonal Health Department Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bahir Dar City Adminstration Zonal Health Department, Government Organization, Amhara Regione, Bahir Dar.

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከክልሉ ጤና ቢሮ ዕውቅና ተሰጠው✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️ጥቅምት 1/2019 ዓ.ምየአማራ ...
12/10/2026

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከክልሉ ጤና ቢሮ ዕውቅና ተሰጠው
✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️
ጥቅምት 1/2019 ዓ.ም
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በ2018/2019 ዓ.ም የዜጎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ከሰኔ 21/2018 ዓ.ም. እስከ መስከረም 20/2019 ዓ.ም. ድረስ “በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ቃል ሲያካሂድ ቆይቷል።
በዚህ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በነበረው ንቁ ተሳትፎና ባበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።
ይህ ዕውቅና የመምሪያውን የበጎ ፈቃድ ተሳትፎ፣ የማኅበረሰብ የጤና አገልግሎት ቁርጠኝነትና በጋራ በመሥራት ለማኅበረሰቡ የጤና ፍላጎቶች ምላሽ ለመስጠት ያደረገውን ያላሰለሰ ጥረት የሚያመለክት ነው።
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማኅበረሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር፣ የመረዳዳትና የአብሮነት ባህልን በማሳደግ እንዲሁም የጤና አገልግሎቶችን ለማኅበረሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ጉልህ ሚና አለው። እንዲሁም ዜጎችን በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማሳተፍ; የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ; የአገልግሎትንና የተቋማትን ወጭ ማዳን ዋና ግቡ ነው።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያም በቀጣይ የበጋ የበጎ ፈቃድና የማኅበረሰብ ተሳትፎ ሥራዎችን በማጠናከር ለማኅበረሰቡ የተሻለ፣ ጥራት ያለውና ተደራሽ የጤና አገልግሎት ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳድጋል።

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ
ጥቅምት 01/2019 ዓ.ም

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ተግባራት ተከናውነዋል። ክቡር አቶ ጎሹ እንዳላማው የባሕርዳር ከተማ ከንቲባ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም (ባሕር ዳር ከተማ ኮሙ...
11/10/2026

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ተግባራት ተከናውነዋል። ክቡር አቶ ጎሹ እንዳላማው የባሕርዳር ከተማ ከንቲባ

ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም (ባሕር ዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን)፦ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የ2018 ዓ.ም የክረምት የዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የ2019 በጀት ዓመት የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ።

በዕለቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው እንደገለፁት፤ የለውጡ መንግስት በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።

በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቆየውን የመረዳዳትና የመተጋገዝ ማህበራዊ አብሮነት የሚያጠናክር ተግባር በመሆኑ በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል ያሉት ክቡር ከንቲባው፤ በክረምቱ ወራት በአቅመ ደካሞች ቤት ጥገና፣ በአዲስ ቤት ግንባታ፣ በችግኝ ተከላ፣ በደም ልገሳ እንዲሁም በማጠናከሪያ ትምህርት በሌሎችም የብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር እሳቤዎች ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል።

በቀጣይም በከተማዋ ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በዘላቂነት የሚቀርፉ ተግባራትን በመፈፀም የዜጎችን ችግር ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የባሕር ዳር ከተማ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለ ዘውዱ በበኩላቸው፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበረሰባችንን የመረዳዳት ባሕልና እሴት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከረ የመጣ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።

እንደከተማ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ በተከናወኑ አመርቂ ተግባራትም ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስትን ወጪ ማዳን መቻሉን ኃላፊዋ አስታውቀዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አፈፃፀም ሪፖርትን በመድረኩ ላይ ያቀረቡት የመምሪያው የወጣቶች ተሳትፎና አደረጃጀት ባለሙያ አቶ ሳህሉ ታገለ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ካለፉት ዓመታት በተሻለና በተቀናጀ ሁኔታ መከናወኑን አብራርተዋል።

በመጨረሻም በክረምት የዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው መምሪያዎች፣ ክፍለ ከተሞች እና ግለሰቦች እውቅና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የባሕርዳር ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ገጽ ይወዳጁ:-
Facebook
https://www.facebook.com/BahirdarcityGovenmentalCommunicationAffairsoffice
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCNoAcvzPiExah4lyaAb6_BQ
Telegram
https://t.me/Bahirdarcitycommunication
Twitter
https://x.com/BahirdarO8493?s=35
Tiktok
https://www.tiktok.com/

11/10/2026

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ የተከበሩ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የ2018 ዓ/ም የዜጎች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠናቀቂያ እና የ2019 ዓ/ም የበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ካስተላለፉት መልዕክት በጥቂቱ፦

** የበጎ ፈቃድ ስራ ማለት ያለውን ማካፈል ብቻ ሳይሆን፣ ጊዜን፣ እውቀትን እና ጉልበትን ለዜጎችና ለሀገር ግንባታ ማዋል ጭምር ነው። በጋራ ጥረታችን ትላልቅ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን መሻገር እንችላለን።

** አንድ ማህበረሰብ ሊያድግ እና ሊበለጽግ የሚችለው በመንግሥት እና በመደበኛ የሥራ መዋቅር ብቻ ሳይሆን፣ በእያንዳንዳችን ቅን ልቦና እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጭምር ነው።

** በጎ ፈቃደኝነት የጊዜ፣ የዕውቀት እና የጉልበት ስጦታ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የሰው ልጅ ለወገኑ ያለው ፍቅር ማሳያ እና የደግነት መግለጫ ነው።

** ሀገር የምትገነባውና ማህበረሰባችን የሚለወጠው ዜጎች ለወገናቸው ሲደርሱና እርስ በርስ ሲደጋገፉ ነው።

** የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰባችንን ትስስር የሚያጠናክር፣ ችግሮችን በህብረት እንድንፈታ የሚያስችለን ታላቅ እሴታችን ነው።

** ዛሬም እንደ ትናንቱ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን ለመደገፍ፣ አካባቢያችንን ለመንከባከብ እና አብሮነታችንን ለማጠናከር የበጎ ፈቃድ ማዕበልን መቀላቀል የሁላችንም ኃላፊነት ነው።

** ዛሬ የተሰበሰብነው ስለ መደበኛ የሥራችን ብቻ ለመወያየት አይደለም፤ ይልቁንም ከሥራችን ባሻገር ለማህበረሰባችን በበጎ ፈቃደኝነት ስለምናበረክተው አሻራ ለመነጋገር ነው።

** እኛም በቢሯችን ደረጃ ያለንን እውቀት፣ ልምድ እና ጉልበት በማስተባበር ለማህበረሰባችን አወንታዊ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ ኃላፊነት እና ወደ ስራ ገብተናል ።

** በመሆኑም በሚቀጥሉት የበጋ ወራቶች በሚካሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር ላይ ሁላችሁም በንቃት እንድትሳተፉ እና ሙያዊ እንዲሁም ግላዊ አስተዋጽኦችሁን እንድታበረክቱ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

** አንድ ሆነን የምናደርገው ትንሽ በጎ ሥራ፣ የብዙዎችን ሕይወት መቀየር እና የተሻለች ነገን መገንባት ይችላል!

** በጎ ፈቃደኝነት ለራስ እርካታ፣ ለወገን ድጋፍ ነው! ዛሬውኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተካፋይ በመሆን ማህበራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ የተከበሩ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የ2018 ዓ/ም የዜጎች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠና...
11/10/2026

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ የተከበሩ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የ2018 ዓ/ም የዜጎች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠናቀቂያ እና የ2019 ዓ/ም የበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ተቸኝተው ካስተላለፉት መልዕክት በጥቂቱ፦

** የበጎ ፈቃድ ስራ ማለት ያለውን ማካፈል ብቻ ሳይሆን፣ ጊዜን፣ እውቀትን እና ጉልበትን ለዜጎችና ለሀገር ግንባታ ማዋል ጭምር ነው። በጋራ ጥረታችን ትላልቅ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን መሻገር እንችላለን።

** አንድ ማህበረሰብ ሊያድግ እና ሊበለጽግ የሚችለው በመንግሥት እና በመደበኛ የሥራ መዋቅር ብቻ ሳይሆን፣ በእያንዳንዳችን ቅን ልቦና እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጭምር ነው።

** በጎ ፈቃደኝነት የጊዜ፣ የዕውቀት እና የጉልበት ስጦታ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የሰው ልጅ ለወገኑ ያለው ፍቅር ማሳያ እና የደግነት መግለጫ ነው።

** ሀገር የምትገነባውና ማህበረሰባችን የሚለወጠው ዜጎች ለወገናቸው ሲደርሱና እርስ በርስ ሲደጋገፉ ነው።

** የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰባችንን ትስስር የሚያጠናክር፣ ችግሮችን በህብረት እንድንፈታ የሚያስችለን ታላቅ እሴታችን ነው።

** ዛሬም እንደ ትናንቱ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን ለመደገፍ፣ አካባቢያችንን ለመንከባከብ እና አብሮነታችንን ለማጠናከር የበጎ ፈቃድ ማዕበልን መቀላቀል የሁላችንም ኃላፊነት ነው።

** ዛሬ የተሰበሰብነው ስለ መደበኛ የሥራችን ብቻ ለመወያየት አይደለም፤ ይልቁንም ከሥራችን ባሻገር ለማህበረሰባችን በበጎ ፈቃደኝነት ስለምናበረክተው አሻራ ለመነጋገር ነው።

** እኛም በቢሯችን ደረጃ ያለንን እውቀት፣ ልምድ እና ጉልበት በማስተባበር ለማህበረሰባችን አወንታዊ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ ኃላፊነት እና ወደ ስራ ገብተናል ።

** በመሆኑም በሚቀጥሉት የበጋ ወራቶች በሚካሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር ላይ ሁላችሁም በንቃት እንድትሳተፉ እና ሙያዊ እንዲሁም ግላዊ አስተዋጽኦችሁን እንድታበረክቱ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

** አንድ ሆነን የምናደርገው ትንሽ በጎ ሥራ፣ የብዙዎችን ሕይወት መቀየር እና የተሻለች ነገን መገንባት ይችላል!

** በጎ ፈቃደኝነት ለራስ እርካታ፣ ለወገን ድጋፍ ነው! ዛሬውኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተካፋይ በመሆን ማህበራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ!

01/10/2026
በባህርዳር ከተማ የሚከበረውን የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ቀንን አስመልክቶ ዛሬ የጤና ተቋማት ጉብኝት መርሀ-ግብር ተካሂዷል‎‎ከጤና ሚኒስትርና ከተለያዩ ክልሎች ፕሮግራሙን ለመታደም የመጡ የስ...
01/10/2026

በባህርዳር ከተማ የሚከበረውን የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ቀንን አስመልክቶ ዛሬ የጤና ተቋማት ጉብኝት መርሀ-ግብር ተካሂዷል
‎
‎ከጤና ሚኒስትርና ከተለያዩ ክልሎች ፕሮግራሙን ለመታደም የመጡ የስነተዋልዶ ቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት እየሰጡ ያለውን የባህርዳር ጤና ጣቢያ ጉብኚት አካሂደዋል
‎
‎ በአጠቃላይም የተከናወነ ያሉት ሥራዎች የላቀ አገልግሎት በመስጠት የማኅበረሰቡን የጤና ፍላጎት ለማሳለጥ ጉልህ ሚና እንዳለውም በጉብኚቱ የተገኙት ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።
‎
‎ጎብኝዎችም በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት የእናቶችን ፣ የወጣቶችንና ህፃናትን ውስብስብ የጤና ችግር ለመቅረፍ ከተማ አስተዳደሩ እስከታችኛው የጤና መዋቅር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
‎
‎አክለውም የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና ለማስጠበቅ ፣ የእናቶችንና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተረድቶ በተጎበኙ ተቋማት የተሰራው ስራ በተሞክሮ ሊወሰድ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
‎
‎

24/09/2026

Address

Amhara Regione
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bahir Dar City Adminstration Zonal Health Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share