19/02/2026
የቡታጅራ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የብልፅግና ሕብረት አባላት የ2018 ዓም የግማሽ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ ተካሄደ።
ቀን 12/06/2018ዓም_ቡታጅራ!!
በመድረኩ የወጣቶች ክንፍ የብልፅግና ሕብረት የ6ወር ዕቅድ አፈፃፀም እና ቀሪ 6 ወራት ዕቅድ ዝግጅት ለአባላት ቀርቦ ውይይት ከተገመገመ በኃላ ከህብረቶች አመራሮች ማብራርያ ተሰቶባቸው ፀደቋል እንዲሁም ምርጫ ምልክት ይፋ ማድረግ፣የጥያቄና መልስ ውድድር በመጨረሻም ለአባላት ወጣት አቤል የቀሽት ንብ ማነብ ማህበር ስራ አስኪያጅ ተሞኩሮውን አካፋሏል።
የቡታጅራ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ቶፊቅ ሀሰን በመድረኩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ ፣ዴሞክራሲያዊ፣ታዓማኒና ቅቡልናት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የወጣቶች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ገልፀዋል ።
በ2018 በጀት ዓመት በከተማዋ ወጣቶች ፓለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ሰፊ ስራ ሲሰሩ መቆየቱን ተናግረዋል ።
ኃላፊው አክለው አጠቃላይ በዘርፉ የተሰሩ ስራዎች በተሳለጠ መልኩ በማደራጀት ህብረብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲጎለብት የሚያስችል ስራዎችን በመስራት ጠንካራ የወጣት ክንፍን በመገንባት ወደ ተግባር በመግባት ውጤታማ መሆን የተቻለበት መሆኑን አብራርተዋል ።
በመድረኩ የቡታጅራ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ ወ/ት ሰብለ ተክሌ የተገኙ ሲሆን አጠቃላይ ተግባራትን አቀናጅቶ በመስራት የታችኛው መዋቅር ለውጥ በሚያመጣ መንገድ ድጋፍ በማድረግ የወጣት አደረጃጀት ስራዎች በውጤት መከናወናቸውን ገልፀው የሚስተዋሉ ውስንነቶች ቀጣይ እያረሙ መስራት ይገባል ብለዋል።
የቡታጅራ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምንተስኖት እንዳለ የብልጽግና ወጣቶች ክንፍ አባላት የሰላምና ፀጥታ ግንባታ ስራዎችን ወጣቶች በባለቤትነት ሊያግዙ እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን ለህዝባችን የሚጠቅም ስራ ተቀናጅተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።በምረጫው የተቀመጡ ግቦችን በአፅንኦት ልንሰራባቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመድረኩ ሰነዱን ያቀረቡት የቡታጅራ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙባረክ ጀማል ለ7ተኛው ዙር ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የመወዳደርያ ምልክት የሆነውን" የስንዴ ነዶ" የማስተዋወቅ ስራ ለአባላት የገለፁ ሲሆን "የስንዴ ነዶ" የመደመር ፣የአንድነት እና የትብብር ተምሳሌት መሆኑ በመድረኩ ገልፀዋል።
በመድረኩ ተገኝቶ ልምዱን ያካፈለው የቀሽት ንብ ማነብ ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ ወጣት አቤል ከ5ሺ ብር ባልበለጠ ካፒታል ጀመሮ ወደ 23 ሚሊየን ብር ካፒታሉን በማሳደግ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን በመግለፅ በዚህ ዘርፍ ላይ ገና ያልተሰራበትና ወጣቶች ወደዚህ ዘርፍ ሲቀላቀሉ ከስልጠና ጀምሮ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንና ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እና በዘርፉ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን አቅድ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ