East Gojjam Zone Water And Energy Department

Website

East Gojjam Zone Water And Energy Department (የምስራቅ ጎጃም ዞነ ውሃና ኢነርጂ መምሪያ)

01/10/2026
01/10/2026

I got over 50 reactions on my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉

የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ዳኝነት ፈንታ መኮነንን (ዶ/ር)  ከመስከረም 21/2019 ጀምሮ በድጋሜ የአብክመ የውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ እንዲሆኑ በድጋሜ ሹመት ሰጥተዋ...
01/10/2026

የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ዳኝነት ፈንታ መኮነንን (ዶ/ር) ከመስከረም 21/2019 ጀምሮ በድጋሜ የአብክመ የውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ እንዲሆኑ በድጋሜ ሹመት ሰጥተዋል።
የምስራቅ ጎጃምና ዞንና ውሃና ኢነርጅ መምሪያ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልዎ ይመኛል!

‎የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የአሻጋሪ ዕድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር...
18/09/2026

‎የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የአሻጋሪ ዕድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ።
‎
‎
‎መምሪያው ባሳለፍነው 2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ የአሻጋሪ ዕድገትና ዘላቂ ልማት ግብ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ከወረዳ ውሃና ኢነርጂ ጽ/ቤት ሃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት ፣ ጋር በደብረማርቆስ ከተማ አካሄደ ።
‎የምስራቅ ጎጃምና ዞንና ውሃና ኢነርጅ መምሪያ
‎ መስከረም8/2019 ዓ.ም ደብረማርቆስ
‎
‎በውይቱ ተገኝተው ውይይቱን የመሩት የመምሪያ ሃላፊው አቶ ፍሬው ካሤ እንደገለጹት በበጀት አመቱ መምሪያው እና ከላይ እስከታች ያለው መዋቅር ማህበረሠቡን በማሳተፍ እና በማስተባበር ባደረገው ከፍቸኛ እርብርብ ዝቅተኛ የነበረውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ለማሳደግ ከፍ ያለ እቅድ በማቀድ እና በመተግበር፣ ካቀደውም እቅድ 207% በመፈጸም 48.7 % የነበረውን የዞኑ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ወደ 57.66% ከፍ ማድረጉን እንዲሁም በኢነርጅው ዘርፍ በኩል ከፍ ያለ ውጤት የተመዘገበ መሆኑ ገልጸዋል።
‎በበጀት አመቱ የተበላሹ የውሃ ተቋማትን ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተሄደበት እርቀትም ትልቅ ግምት የሚሰጠው ተግባር እንደነበርና ለረጅም ጊዜ ተበላሽተው የቆዩ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር የነበሩ የውሃ ተቋማትን በመጠገን ወደስራ የገቡበት መንገድ አበረታች እንደነበርም አብራርተዋል ።
‎
‎ይህ እንዳለ ቢሆንም ዛሬም ከዞኑ ጠቅላላ ህዝብ ከ43% በላይ ገና አልደረስንለትም። በዘርፉ ያልተመለሱ የማህበረሠብ ጥያቄዎች በጣም ብዙና ለብዙ አመታት የቆዩ ናቸው ፤ ተበላሽተው ያልተጠገኑ ተጠይቀው ያልተጠኑ ፣ጥናት ተደርጎ ያልተቆፈሩ፣ ተቆፍረው ግንባታ ያልተደረገላቸው፣ግንባታ ተጀምሮ የተቋረጡ የውሃ ተቋማት ብዙ ናቸውና ከቢሮው እስከ ወረዳ ያለው መዋቅር፣የግሉ ሴክተር እና ህዝቡ በትብብር ሊረባረቡ እንደሚገባ በመድረኩን የመሩት የመምሪያ ሃላፊው አቶ ፍሬው ካሤ አጥኖት ሰጥቸው አስረድተዋል።
‎በኢነርጅ ዘርፍም የማህበረሰቡን ግንዛቤ የማሣደግና በተለይም የባዮጋዝ ቴክኒዮሎጅን የማላመድ እና ፍላጎትና የማሳደግ የባለሙያውን ሃቅም የመገንባት የጥራት መጓደሉን ማስተካከላይ ጋና ብዙዎች ሊሠራ እንደሚገባ መምሪያ ሃላፊው አክለው ገልጸዋል።
‎
‎የ2019 የእድገትና አሻጋሪ ልማት አቅድ ቀርቦ ውይተ ተደርጎበታል።እቅዱ በ2022 እና በ2045 ክልሉ ሊደረሰበት ያሰበውን ግብ፣እንዲሁም የህዝባችንን ፍላግት እና ሀቅም ከግምት ያስገባ መሆኑ ተመላክቷል። እቅዱ የጋራ ተደርጎ የበለጠ ለመስራት ስምምነት ተደርሶበታል ።
‎
‎በመጨረሻም በ2018 የበጀት አመት የታቀደው ትልቅ እቅድ እንዲሳካ ጉልህ ሚና ለነበራቸው አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል ።
‎
‎መመረጃው የምስራቅ ጎጃምና ዞንና ውሃና ኢነርጅ መምሪያ ነው
‎ https://www.facebook.com/share/p/1DhordYSeZ/

🌹🌹እንቁ ጣጣሽ🌹🌹የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ እና በ25ቱ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች  የምትገኙ አመራሮች ፣ባለሙያዎችና ሠራተኞች  ከሁሉ አስቀድሜ እንኳን ለአዲሱ አመት ...
10/09/2026

🌹🌹እንቁ ጣጣሽ🌹🌹

የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ እና በ25ቱ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የምትገኙ አመራሮች ፣ባለሙያዎችና ሠራተኞች ከሁሉ አስቀድሜ እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ 🌹🌹🌹
‎
‎​በውስብስብ ችግሮች ውስጥ አልፈን
‎ለማኅበረሰባችን የንጹህ መጠጥ ውሃ እና የኃይል አቅርቦት ተደራሽነትን እውን ለማድረግ ቀን ከሌሊት ለምትደክሙ የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ እና የወረዳእና ከተማ የሥራ ባልደረቦቼ፤
‎​እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሰን!
‎​ባለፉት ዓመታት በዞናችን የተከናወኑ በርካታ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክቶችን እና የሃዬል አማራጭ አቅርቦት ሥራዎችን በቁርጠኝነት ለውጤት ያበቃችሁት ጥረት ላቅ ያለ ግምት የሚሰጠው ነው። በጋራ ባሳየነው ጠንካራ የትብብር መንፈስና የስራ ባህል በርካታ ፈተናዎችን አልፈናል፤ ማህበረሰባችንንም ተጠቃሚ ማድረግ ችለናል። ይህንንም
‎​በአዲሱ ዓመት 2019 ዓ.ም በዕቅድ የያዝናቸውን የልማት ሥራዎች በላቀ ፍጥነትና ጥራት የምናጸናበት፣ የድልና የስኬት ዓመት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ። ለእናንተና ለቤተሰቦቻችሁ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ ።
ፍሬው ካሤ
‎ ​
‎ መልካም አዲስ ዓመት!

በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳድሮች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸውየአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና ...
02/09/2026

በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳድሮች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸው

የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ ተጠናቀቀ።

በመድረኩ ማጠቃለያ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በሠላም፣ በልማት በመልካም አስተዳደር መስኮች የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖች እና ከተማ አስተዳድሮች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በዚህም የምስራቅ ጎጃም እስተዳደር ዞን ፈተናን ወደ ድል በመየር ባደረገው ጥረት የአመቱ 3ኛ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ በአብክመ ውሃ እና ኢነርጅ ቢሮ  ከተለያዩ  ዳሬክተሮች በተውጣጣ ቡድን ድጋፍ ተደረገለት።ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ደብረማርቆስ የቢሮው ከፍተኛ ባለሙ...
30/07/2026

የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ በአብክመ ውሃ እና ኢነርጅ ቢሮ ከተለያዩ ዳሬክተሮች በተውጣጣ ቡድን ድጋፍ ተደረገለት።

ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ደብረማርቆስ

የቢሮው ከፍተኛ ባለሙያዎች እና ዳሬክተሮች የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፍሬው ካሤን ጨምሮ የዞን ማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን የዞኑን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2019 በጀት አመት እቅድ ዝግጅትየክረምት ሥራዎች እቅድ አፈጻጸም ፣ የዜጎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና በክልሉ በኤል-ኒኖ የሚከሰት የዝናብ እጥረት ተጋላጭ ለሆኑ አካባቢዎችንና የማህበረሰብ ክፍሎች የሚወሠዱ እርምጃዎች ላይ ሰፊው ግምገማና ውይይት ተካሄደ።

የሙያተኞች ቡድን ከመምሪያው ያገኜውን ግበዓት በመያዝ የከዞን አስተባባሪ ኮሚቴ አባልና የምስራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ ከሆኑት ከአቶ ተስፋየ በላይ ጋር በዘርፉ እስትራቴጅክ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

19/07/2026
17/07/2026

Address

Debra Markos

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone Water And Energy Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share