East Gojjam Zone Land Department

East Gojjam Zone Land Department Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from East Gojjam Zone Land Department, Government Organization, Amhara Region, Debra Markos.

06/10/2026
06/10/2026
06/10/2026
የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ መሬት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገት ዘላቂ ልማት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ።በምስራቅ ጎጃ...
06/10/2026

የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ መሬት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገት ዘላቂ ልማት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን መሬት መምሪያ የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ መሬት ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ ትውውቅ ከወረዳናቀበሌ መሬት ባለሙያዎቸ እና በወረዳው ካሉ ታዳጊ፣ንዑስና መሪ መዘጋጃ ስራ አስኪያጆችና የመሬት ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷል ።

የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ መሬት ጽ/ቤት ኀላፊ በአቶ ጌትነት ግዛዉ የ2018 ዓ.ም የተከናወኑ የስራ እቅዶች፣ የተገኙ ውጤቶች ፣ የተስተዋሉ ክፍተቶችና በቀጣይ መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች በስፋት አንስተው ውይይት የተደረገባቸው ከመሆኑም በተጨማሪ የ2019 ዓ.ም እቅድ ኦረንቴሽን ሰጥተው በእቅዱ መሰረት ውጤታማ ስራ ለማከናወን የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የዛሬው መድረክ በዋናነት የተከናወኑትን ስራዎችና በእዚያ ውስጥ የተገኙ ጥሩ ተሞክሮዎችና ያጋጠሙትን ክፍተቶች በመለየት በቀጣይ ደግሞ ለሚኖር ተልዕኮ ከወዲሁ ለመዘጋጀት ያለመ ነው ብለዋ።

መሬት ጽ/ቤት ለወረዳችን ብሎም ለማህበረሰባችን በርካታ ስራዎችን በመስራትና ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ከመሆኑም በተጨማሪ ተቋማትን የሚያስተሳስርና የሚያገናኝ በመሆኑ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ በማስቀጠልና ክፍተቶችን በመለየትና ስራዎችን በባለቤትነት በመያዝና እርስ በእርስ በመተጋገዝ የተሻሉ ስራዎችን በመስራት ህዝባችንና ወረዳችን ተጠቃሚ ማድረግ አለብን ነው ያአሉት ተሳታፊዎቹ ።

ችግሮችን ለመቅረፍ ጥብቅ ቁጥጥርና ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባና አሰራሮችን በድጅታል ቴክኖሎጂ የማዘመን ስራዎች እንደሚሰሩ ጠቁመው የህዝብ አገልግሎት ማጠናከርና የህዝብን ጥያቄ በተገቢው መንገድ መመለስ ትኩረት ተሰጥቷቸው የሚሰራባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል ።

በቀረበው ሪፖርት ላይ መድረኩን የመሩት የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ መሬት ጽ/ቤት ኀላፊ አቶ ጌትነት ግዛዉ እና የእነብሴ ሳር ምድር ዋና አስተዳዳሪ በጋራ በመሆን ነው ።

በመጨረሻም የወረዳችን የመሬት ስራዎችን በትብብር እንደሚሰሩ ባለሙያዎቹ በመግባባት፣ የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠው በ2018 በጀት ዓመት ጥሩ አፈጻጸም ላሳዩ ባለሙያዎች የማበረታቻ የምስክር ወረቀት ተበርክቶ መድረኩ ተጠናቋል።

“እቅድን መናበብ፣ ከፈፃሚ ጋር መግባባት እና በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መፈፀም ይገባል ተባለ፡፡”አቶ አወቀ ሲሳይየአብክመ መሬት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር==============...
06/10/2026

“እቅድን መናበብ፣ ከፈፃሚ ጋር መግባባት እና በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መፈፀም ይገባል ተባለ፡፡”

አቶ አወቀ ሲሳይ
የአብክመ መሬት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር
===========================================
የአብክመ መሬት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አወቀ ሲሳይ በደ/ጎ/ዞን መሬት መምሪያ በመገኘት የአካል ድጋፍ እና የቢሮ ጉበኝት ያደረጉ ሲሆን በድጋፉ ወቅት ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፡-

እንደ መምሪያ ተግባሮች ሲፈፀሙ በተቀመጠው KPI መሰረት ማከናወን እና የእርካታ መለኪያዎችን መስራት በማድረግ ግቦች መከናወን እንዳለባቸው በተጨማሪም የመማማር እና እድገት የልማት ቡድን እንዲሁም አጠቃላይ የቁልፍ ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በመቀጠልም የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል ከተሰሩ ስራች ውስጥ እንደ ክልል አዲሱን አዋጅ መሰረት በማድረግ በክልሉ ለሚገኙ ዳኞች ስልጠና ተሰጥቷል ያሉ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ አዋጁን ተከትሎ የተዘጋጀው ደንብና መመሪያ ለማስፀደቅ ዝግጅታቸውን የጨረሱ መሆኑን አንስተዋል በመጨረሻም ከማኔጅመንት አካላት የተነሳላቸውን ጥያቄ መላሽ ሰጥተዋል፡፡

የመሬት መምሪያ ሀላፊዋ ወ/ሮ ፀሀይ ቸኮል የተደረገልን ድጋፍ የሚያነቃቃ እና ለቀጣይ ስራዎቻችን ግብዓቶችን ያገኘንበት በመሆኑ ይሄን መሰረት አድርገን ወደ ተግባር እንገባለን በማለት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
ምንጭ:- South Gonder Zone Land Department /ደ/ጎ/አስ/ዞን መሬት መምሪያ

በጋራ ለጋራ ስኬት
26/01/2019 ዓ.ም

የሲቪልና ቤተሰብ አገልግሎት የምዝገባ ስራን ከማንዋል አሰራር ወደ ዲጅታል  ስርዓት ለማሸጋገር በትኩረት እየተሰራ ነው።*****መስከረም 26/2019 ዓ.ም (ምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙ...
06/10/2026

የሲቪልና ቤተሰብ አገልግሎት የምዝገባ ስራን ከማንዋል አሰራር ወደ ዲጅታል ስርዓት ለማሸጋገር በትኩረት እየተሰራ ነው።
*****
መስከረም 26/2019 ዓ.ም (ምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ): በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ የዲጅታል አሰራር ስርዓት በሁሉም ቀበሌዎች እውን ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በስልጠና መድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበበ ጓዱ እንደገለጹት የሲቪልና ቤተሰብ አገልግሎት የምዝገባ ስራን ወደ ዲጅታል ስርዓት ለማሸጋገር በክልሉ ከ2016 በጀት ዓመት ጀምሮ በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

በዞኑ በ2018 በጀት ዓመት በ7 ከተማ አስተዳደሮች 41 ቀበሌዎች ላይ የዲጅታል ምዝገባ ስራን ተግባራዊ በመደረጉ ውጤት መመዝገቡን የተናገሩት ምክትል አስተዳዳሪው ተግባሩን በቅንጅት በመሰራቱ የመጣ ውጤት መሆኑን አስገንዝበዋል።

በ2019 በጀት ዓመት ወደ ዲጅታል ምዝገባ ያልገቡ 17 የገጠር ወረዳዎችና በ1 ከተማ አስተዳደር በ435 ቀበሌዎች ወደ ዲጅታል ለማስገባት የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን የገለጹት አቶ አበበ ጓዱ በዞኑ የዲጅታል ስርዓት በብቃት ሲፈጸም የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል ብለዋል፤ይህንንም እውን ለማድረግ ክልሉ 435 ታብሌቶች፣ፖወር ባንኮችና አሰልጣኞችን የመመደብ ሰራ የሰራ ሲሆን እስካሁን 388ቱን የማስረከብ ስራ መሰራቱን አብራርተዋል።

ለተግባሩ ተፈጻሚነት የመስሪያ ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ከማድረግ ጀምሮ በአግባቡ ሰራላይ እንዲውሉ በቅንጅት መምራትና መከታተል እንደሚገባ አቶ አበበ ጓዱ አሳስበዋል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን አሶተዳደር የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ አይተነው ወርቅነህ የተለመደውን የማኑዋልን አሰራር በማስወገድ ዲጅታል አሰራርን ለማዘመን ዓላማ ያደረገ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ አይተነነው አያይዘውም በ2018 በጀት ዓመት በ7 ከተማ በ41 ቀበሌ በዲጅታል ምዝገባ ሙከራ ውጤታማ በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ወደ ዲጅታል ምዝገባ ያልገቡ 435 የቀበሌ መዝጋቢዎችን ወደ ተግባር ለማስገባት በ 2 ዙር ስልጠና በማመቻቸት የቀበሌ የጤና ባለሙያዎች፣የቀበሌ ስራ አስኪያጆችንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ስልጠና እየተሰጡ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

የምዝገባ ስርዓት ወደ ቴክኖሎጅ ማሸጋገር ብቻ ውጤታማ እንደማያደርግ የተናገሩት አቶ አይተነው ወርቅነህ ሰልጣኙ በትኩረት በመከታተል እውቀቱና ክህሎቱን ማሳደግ፣እንዲሁም በየደረጃው የሚገኝ አመራር ተግባሩን በመደገፍና በማስተባበር ውጤታማ የምዝገባ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በ2019 በጀት ዓመት ከ76 ሽህ 835 በላይ ኩነቶችን ለመመዝገብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አቶ አይተነው ወርቅነህ ጨምረው ገልጸዋል።

የመሬት ካሳ የማግኘት መብት!*********ከህጋዊ ይዞታው በልማት ምክንያት የተነሳ ሰውን መልሶ ሟቋቋም የመንግስት ግዴታ ነው። የተነሺውም መብት ነው።በመሆኑም ከጉዳዩ ጋር የሚያያዙ ዋና ዋና...
06/10/2026

የመሬት ካሳ የማግኘት መብት!
*********
ከህጋዊ ይዞታው በልማት ምክንያት የተነሳ ሰውን መልሶ ሟቋቋም የመንግስት ግዴታ ነው። የተነሺውም መብት ነው።
በመሆኑም ከጉዳዩ ጋር የሚያያዙ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ሰፍረዋል።

(1) ካሳ የማግኘት መብት:-

በአዲሱ አዋጅ ቁጥር 1161/11 አንቀፅ 8(1)(ሰ) ስር የልማት ተነሺውን ማስነሳት የሚቻለው ለተነሺው ካሳ ከተፈለ እና ምትክ ቦታ ወይም ቤት ከሰጠ በኋላ መሆን እንዳለበት አዋጁ ይደነግጋል፡፡በመሆኑም ሰዎች በይዞታቸው ካሳም ሳይከፈላቸው ምትክ ቦታም ሳይሰጣቸው እንዲነሱ ተደርጎ የመብት ጥሰት እየደረሰባቸው የነበሩ ባለይዞታዎች በጣም ብዙ የነበሩ በመሆኑ ይህ አዋጅ ህዝቡ ውስጥ የነበረው ችግር ለመፍታት ተነሺዎች ከመነሳታቸው በፊት አስቀድመው ካሳ እና ምትክ ቦታ ማግኘት እንዳለባቸው መደንገጉ በሕግ ደረጃም ቢሆን ጥሩ የሚባል ነው፡፡

(2) ካሳ በወቅቱ ካልተከፈላቸው መልሶ የመያዝ መብት

ተነሺዎች የካሳ ግምት በጹሑፍ እንዲያውቁ ከተደረገ ቀን ጀምሮ በሶስት ወር ውስጥ ካሳ ካልተከፈላቸው በመሬት ይዞታቸው ከቋሚ ተክልና ግንባታ በስተቀር ሌሎች ስራዎች መስራት ይችላሉ በማለት ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ካሳ ካልተከፈው በፕላን የሚፈቀድ እና ቀጣይ የቦታውን የልማት ወጪ በመንግስት ላይ የማያበዛ በመሬቱ ላይ ማንኛውም ስራ መስራት ይችላል በማለት ይደነግጋል።

ቢሆንም ግን ይህ ድንጋጌ እጅግ አሻሚ ነው ምክንያቱም መንግስት ካሳ ካልከፈለ በፕላን መሰረት ባለይዞታ ማንኛውንም ዓይነት ስራ መስራት እንደሚችል ከተደነገገ በኋላ በመንግስት የልማት ወጪ የማያበዛ ስራ ማለቱ ምን ማለት ነው? እጅግ በጣም ግልጽ ነት የጎደለው ነው፡፡

(3) ተመጣጣኝ ካሳ ክፍያና ምትክ ቦታ

አዲሱ አዋጅ በመሬቱ ላይ ለተፈራ ንብረት፣ ቋሚ ማሻሻያ ባለይዞታው ንብረቱን ማዘዋወር የሚችል ከሆነ የማዘዋወሪያ ወጪ ወይም የትራንስፖርት/የማጓጓዣ ወጪ ከመክፈሉ በተጨማሪ ከገጠር መሬት ይዞታ ለሚነሳ የመሬት በላይዞታ ተነሺ ከተወሰደበት መሬት ተመጣጣኝ የሆነ ምትክ መሬት እና መሬት ይዞታው ከመልቀቅ በፊት ባሉ ሶስት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ምርት ያመረተበትን ምርት በወቅታዊ ዋጋ ተሰልቶ በ15 ተባዝቶ ይከፈላል በማለት ይደነግጋል፡፡

(4) የልማት ተነሽ ድጋፍ

በአዋጁ አንቀጽ 2(4) የልማት ተነሽ ድጋፍ የመሬት ባለይዞታ ከመሬቱ በጊዜያዊም ሆነ በቋሚነት ሲነሳ ከአዲሱ አከባቢ ጋር መላመድ እንዲችል ከንብረት እና ከልማት ተነሽ ካሳ በተጨማሪ በዓይነት ወይም በገንዘብ የሚሰጥ ድጋፍ ነው፡፡ it is promising move አዲስ እና በጣም ጥሩ የሚባል ነው ነገር ግን ይህ ነገር የሚወሰነው በክልሎች መመሪያ ነው፣ መች ይሁን የሚወጣው? ባይወጣስ?

መልሶ ማቋቋም ፡- በአዋጅ አንቀጽ 16 የክልል መንግስት ወይም የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ አስተዳደር ለካሳ ክፍያ እና ለመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ያቋቁማል በማለት ይደነግጋል፡፡ መልሶ ማቋቋም ማለት በተወሰደው መሬት ምክንያት የሚያገኙት ጥቅም ለሚቋረጥባቸው ተነሺዎች ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲያገኙ የሚያስችል የሚሰጥ ድጋፍ ነው ።

አቶ መኮንን ደባሱ እጅጉ የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ አማካሪ ሆነው ተሾመዋል ።
05/10/2026

አቶ መኮንን ደባሱ እጅጉ የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ አማካሪ ሆነው ተሾመዋል ።

05/10/2026

አቶ መኮንን ሙሉዓዳም ተገኘ የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት ዋና አማካሪ ሆነዉ ተሾመዋል።

ከምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማገኘት አማራጭ የመረጃ መረቦችን በመወዳጀት ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ :-
‎ፌስቡክ
‎https://www.facebook.com/EastGojjamCommunicationsOfficial
‎ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCyq4rgufD2TbpsN2zUEZp3Q
‎ቴሌግራም https://t.me/eastgojjamcommunication
‎ቲውተር https://twitter.com/home?lang=en-gb
‎ኢንስታግራም https://www.instagram.com/eastgojjamcommunication3
‎ቲክቶክ
‎tiktok.com/
‎ዋትስአፕ
‎https://whatsapp.com/channel/0029Vb85jBYEKyZCWOQ0fh1

አቶ መልካሙ ሽባባው ሽፈራው የደብረማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ኾነው ተሾሙ። የደብረማርቆስ ከተማ ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን...
05/10/2026

አቶ መልካሙ ሽባባው ሽፈራው የደብረማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ኾነው ተሾሙ።

የደብረማርቆስ ከተማ ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን አቶ መልካሙ ሽባባው ሽፈራውን የደብረማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

‎🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

Address

Amhara Region
Debra Markos

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone Land Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share