East Gojjam Zone Disaster Risk Management Office

East Gojjam Zone Disaster Risk Management Office ለአደጋ የማይበገር እና የምግብ ዋስትናው የተረጋገጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር ተግተን እንሰራለን!

‎🌾"እንደ ዘንድሮ ሰብል በቅሎ አያውቅም" አርሶ አደር‎‎በአማራ ክልል በ2018/19 የምርት ዘመን የተከናወኑ የግብርና ተግባራት፣ የቀረቡ ግብዓቶች እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውጤት አሳይተው ...
10/10/2026

‎🌾"እንደ ዘንድሮ ሰብል በቅሎ አያውቅም" አርሶ አደር
‎
‎በአማራ ክልል በ2018/19 የምርት ዘመን የተከናወኑ የግብርና ተግባራት፣ የቀረቡ ግብዓቶች እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውጤት አሳይተው የሰብል ቁመናው እጅግ ተስፋ ሰጭ ደረጃ ላይ ይገኛል።
‎
‎በምሥራቅ ጎጃም ዞን ባሶ ሊበን ወረዳ ነዋሪ የኾኑት አርሶ አደር ዓለማየሁ ፈቃዱ «እንደ ዘንድሮ ሰብል በቅሎ አያውቅም» ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አርሶ አደሩ እንደገለጹት ከኾነ ይህ ውጤት የተገኘው ከእርሻ ዝግጅት እስከ አረም ማረም ያሉ ሥራዎችን በጥራት ከመሥራት ባለፈ የተሻሻሉ የግብርና ግብዓቶችን በአግባቡ በመጠቀማቸው ነው።
‎
‎በአካባቢው ከጤፍ በተጨማሪ ስንዴ፣ ባቄላ እና ገብስ በስፋት የሚመረት ሲኾን በተለይም የጤፍ እና የስንዴ ማሳዎች ቁመና እና የፍሬ ሂደት አጥጋቢ በመኾኑ ከባለፈው ዓመት የተሻለ ከፍተኛ ምርት እንደሚጠብቁ አብራርተዋል።
‎
‎የምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ጥላሁን ንጋቱ በዞኑ በምርት ዘመኑ 687 ሺህ 500 ሄክታር መሬት በሰብል በመሸፈን 27 ነጥብ 06 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
‎
‎በዞኑ ስንዴ፣ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ቦሎቄ እና የቢራ ገብስን ጨምሮ 7 ዋና ዋና ሰብሎች 81 በመቶ የሚኾነውን የመሬት ሽፋን ይዘዋል ነው ያሉት።
‎
‎ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ የቀረበ ሲኾን የምርጥ ዘር አቅርቦትም ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል።
‎
‎በበኩታ ገጠም (ክላስተር) እርሻ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከ26 ሺህ 300 ሄክታር በላይ መሬት በትራክተር መታረሱንም አመላክተዋል።
‎
‎ተባይ እና በሽታ እንዳይከሰት ሰብሉን በየጊዜው የማሰስ እና የመከላከል ሥራዎች በቅንጅት ስለመከናወኑም ነው ያብራሩት።
‎
‎በሌላ በኩል የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት እና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ.ር) እንደገለጹት በምርት ዘመኑ በክልል ደረጃ ከ5 ሚሊዮን 5 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር በመሸፈን 205 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሠብሠብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱንም አስገንዝበዋል።
‎
‎ዶክተር ማንደፍሮ አዳዲስ የሰብል ሳይንሳዊ አሠራሮች፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት፣ የኩታ ገጠም እርሻ እና የቅርብ ክትትል በመደረጉ አብዛኛው ሰብል በአሁኑ ወቅት በአበባ እና ፍሬ በመሙላት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።
‎
‎በምርት ዘመኑ የሚጠበቀውን የተትረፈረፈ ምርት በመሠብሠብ የክልሉን እና የሀገርን ኢኮኖሚ ከመገንባት ባለፈ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የሰብል ቁመና ላይ እንደሚገኝም ተመላክቷል ሲል የዘገበው አሚኮ።

‎
‎

10/10/2026
10/10/2026
10/10/2026
10/10/2026
10/10/2026
በምስራቅ ጎጃም ዞን በ6ወረዳዎች  የማህበረሰቡን የአደጋ መቋቋም አቅም ለማሳደግ ያለመ የተግባር ስልጠና ተሰጠ፡፡  መስከረም 29/1/2019 ምስራቅ ጎጃም ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ተጠሪ...
09/10/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን በ6ወረዳዎች የማህበረሰቡን የአደጋ መቋቋም አቅም ለማሳደግ ያለመ የተግባር ስልጠና ተሰጠ፡፡
መስከረም 29/1/2019 ምስራቅ ጎጃም ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ተጠሪ ጽ/ቤት

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ በአውሮፓ ህብረት የበጀት ድጋፍ ከሚተገበረው «ያልተማከለ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ሥራ አመራርን ማጠናከር» ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በምስራቅ ጎጃም ዞን ለ6 ወረዳዎች አደጋ ስጋት ቅነሳ ዕቅድ፣ ከተፈጥሮ አደጋ ጋር ተላምዶ መኖር እና በመጠባበቂያ ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ ለወረዳ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተግባር ስልጠና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናው ላይ ከአዋበል፤ደባይጥላትግን፤ደብረ ኤልያስ፤ስናን፤ቢቡኝ፤ደባይ ጥላትግን ወረዳዎች የተወጣጡ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ትግበራ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት ምስራቅ ጎጃም ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሸመ መኮነን እንደገለፁት፣ የስልጠናውን ማስጀመር አስመልክተው በ5ቱ ፍኖተ ካርታዎች ገለፃ በማድረግ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በምናካሂደው የተቀናጀ እንቅስቃሴ አንድ አካል በመሆኑ ቀድመን ልንሰራቸው የሚገቡ በመሆናቸው ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ተፅዕኖዎች ለመቋቋም አደጋ ከደረሰ በኋላ ከሚደረግ ምላሽ ይልቅ አደጋ ከመከሰቱ በፊት ወደሚከናወን ቅድመ ጥንቃቄ ማዘንበል ወሳኝ ነውብለዋል። ኃላፊው አክለውም «አደጋዎችን በዘላቂነት ለመከላከልና የማህበረሰባችንን የመቋቋም አቅም ለማሳደግ በወረዳ ደረጃ ያሉ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያዎችን እና የባለድርሻ አካላትን አቅም ማጎልበት መሠረታዊ ጉዳይ ነው» ብለዋል።

በተቋሙ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ቡድን መሪ አቶ ነፃነት አሰፋ የዕለቱ የስልጠና ማነዋሎች ላይ ትኩረት በሚሰጣቸው ተጣጥሞ መኖር እቅድ ዝግጅት፤የመጠባበቂ እቅድ አዘገጃጀት፤የአደጋ ስጋት አመራር ፖሊሲዎችና የእቅድ አዘገጃጀት ዘዴዎች ን አስመልክቶ በተዘጋጁት የስልጠና ማንዋሎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ
አቶ ጥላሁን አምበሉ የክልሉ አደጋ ስጋት የቅድሚያ ማስጠንቀቂ ቡድን ተወካይ በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲና ስትራቴጂ ዙሪያ አጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲና ስትራቴጂ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት በቅድመ መከላከል፣ በስጋት ቅነሳ እና በራስ አቅም ምላሽ በመስጠት ላይ አተኩሮ እየተተገበረ እንደሚገኝ አቶ ጥላሁን ገልጸው፣ አያይዘው ቀደም ሲል የነበረውን አደጋ ከተከሰተ በኋላ ድጋፍ የማቅረብ አካሄድ በመቀየር፤ ወቅታዊው ፖሊሲ የአደጋ ስጋት ቅነሳን በሁሉም የልማት ዕቅዶች ውስጥ ማካተት፣ ዘመናዊ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት መዘርጋት እና የማህበረሰቡን የመቋቋም አቅም መገንባት ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል ሲሉ አስረድተዋል። በተጨማሪም ብሔራዊ የመጠባበቂያ ክምችትና ፈንድ በማጠናከር አደጋዎችን በራስ አቅም በመቋቋም የተረጅነት አስተሳሰብን ለማስወገድ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በአውሮፓ ህብረት የበጀት ድጋፍ የሚተገበረው «ያልተማከለ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራ አመራርን ማጠናከር» አቶ ታሪኩ ምናሉ በበኩላቸው፣ የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ዓላማና ዋና ዋና ተግባራትን በማብራራት አደጋዎችን ተላምዶ የመኖር እና የመጠባበቂያ ዕቅዶችን (Contingency Plans) በጥራት የማዘጋጀት ልምድ ማህበረሰቡ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ውድመት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንስ ጠቁመው፤ ስልጠናው የወረዳዎችን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ የተቀናጀ ዕቅድ ለማውጣት የሚረዳ ተግባራዊ እውቀት ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል።

በኮሚሽኑ የዘርፉ ባለሙያዎች በአቶ ጥላሁን አምበሉ ፤ በአቶ ታሪኩ ምናሉ እና በአቶ ደርበው አየለ አማካይነት የተሰጠው ይህ የዕቅድ ዝግጅት ስልጠና፣ በወረዳ ደረጃ የማህበረሰቡን የአደጋ መቋቋም አቅም ለማሳደግ ያለመ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘና የተግባር ልምምዶችን ያካተተ በመሆኑ የሰልጣኞችን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያረጋገጠ ነበር።

የሚዘጋጀው ዕቅድ ለአንድ ዓመት እና ለ5 ዓመታት የሚተገበር ዘርፈ-ብዙ የልማት ስትራቴጂ ሲሆን፤ ከልማታዊ ሴፍቲኔት፣ ከመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር፣ ከማህበራዊ ጥበቃ እንዲሁም ከአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጋር የተቀናጀ እንቅስቃሴን ታላሚ ያደረገ ነው። ይህ ቅንጅታዊ አሰራር ከወረዳው አጠቃላይ የልማት ዕቅድ ጋር በማቀናጀት ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በመተባበር የሚተገበር በመሆኑ፣ የማህበረሰቡን የኑሮ መሠረት ለማሻሻልና የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል።

በመጨረሻም የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሸመ መኮነን በመዝጊያ ንግግራቸው ይህ የተቀናጀ ስራ ከአደጋ ተጋላጭነት ነፃ የሆነ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር ለወደፊቱ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ሀገርና ህዝብ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የራሱን የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክት ገልፀው፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና የልማት አጋሮች የተዘረጋውን አሰራርና ዕድል በቅንጅት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ና ወደ ቀበሌ ወርደን ስንተገብር የሚያጋጥሚ ችግሮችን ተቋቁመን ለህብረተሰቡ ለውጥ ተግተው መስራት

Address

Debra Markos

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone Disaster Risk Management Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share