Dire Dawa Police

Call Website Contact the organization

Dire Dawa Police የድሬዳዋ ፖሊስ ራዕይ::
👉በ2022 በኢትዮጵያ በላቀ ሙያዊ ብቃት ቀዳሚ የፖሊስ ተቋም ሆኖ ማየት::

This is the official page of the Dire Dawa Police Department
ይህ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ኦፊሻል የፌስብ ቡክ ገፅ ነው።

የዛሬው ወጣት፤ የግል ስኬቱን ከሀገር ዕድገት ጋር የሚያጣመር የነገዋ ድሬደዋና ኢትዮጵያ ተስፋ ነው!" — ክቡር አቶ አብዱላሂ አደምየድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ
02/11/2026

የዛሬው ወጣት፤ የግል ስኬቱን ከሀገር ዕድገት ጋር የሚያጣመር የነገዋ ድሬደዋና ኢትዮጵያ ተስፋ ነው!"

— ክቡር አቶ አብዱላሂ አደም
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አብዱላሂ አደም "የዛሬ ወጣት የነገ ድሬዳዋ ባለቤትና የኢትዮጵያ ተስፋ" በሚል መሪ ቃል ከአስተዳደሩ ወጣቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።​በመድረኩ ላይ የተገኙ...
02/11/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አብዱላሂ አደም "የዛሬ ወጣት የነገ ድሬዳዋ ባለቤትና የኢትዮጵያ ተስፋ" በሚል መሪ ቃል ከአስተዳደሩ ወጣቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት ክቡር ከንቲባው እንደገለፁት፤ ውይይቱ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ወጣቱን ባሳተፈ መልኩ የተከናወኑ ጠንካራ ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል ያለመ ነው ብለዋል።

​በውይይቱ ላይ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት በም/ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ተጠሪ ክቡር አቶ አብዱልጀዋድ መሀመድ፤ ወጣቱ የአስተዳደሩን ሰላም የማፅናት፣ ራሱን ከሱስና ከአላስፈላጊ ልማዶች የማራቅ እንዲሁም በሙያ በመበቃት ኢኮኖሚያዊ ነፃነቱን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት አሲምረውበታል።

​በመድረኩ ላይ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ፣የድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ሻኪር አህመድን፣ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ አብዱላሂ አደም "የዛሬው ወጣት፤ ለነገ የድሬዳዋ ባለቤትና የኢትዮጵያ ተስፋ" በሚል ርዕስ ከወጣቶች ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።​በምክክር መድረኩም ወጣ...
02/11/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ አብዱላሂ አደም "የዛሬው ወጣት፤ ለነገ የድሬዳዋ ባለቤትና የኢትዮጵያ ተስፋ" በሚል ርዕስ ከወጣቶች ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።

​በምክክር መድረኩም ወጣቱ የታሪክ ግንዛቤውን በማዳበርና ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር በመቃኘት ለአገር ልማትና እድገት የሚጠበቅበትን ሚና በግንባር ቀደምትነት እንዲወጣ ጥሪ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

"ወንጀለኛ የትም መደበቅ አይችልም!"– ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤልየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል የዓለም አቀፍ የተጓዦች ትስስር ቴክኖ...
01/11/2026

"ወንጀለኛ የትም መደበቅ አይችልም!"
– ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ

ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል የዓለም አቀፍ የተጓዦች ትስስር ቴክኖሎጂን ልትተገብር ነው

ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከልና ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጡ ለማድረግ ዓለም አቀፍ የተጓዦች ትስስር ቴክኖሎጂን ልትተገብር መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለጹ።

በኢንተርፖል የለማው ይሄው ዓለም አቀፍ የተጓዦች ትስስር ቴክኖሎጂ ስርዓት ሽብርተኝነትና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ሰርተው የተደበቁ ወንጀለኞች ህግን ተከትሎ ለአባል ሀገራት ተላልፈው እንዲሰጡ ማድረግ የሚያስችል ነው።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቀጣናው በገነባው ጠንካራ የወንጀል መከላከል አቅምና ከኢንተርፖል ጋር ባለው የተቀናጀ ትብብር ለአባል ሀገራት የሕግ አስከባሪዎች ደረጃውን የጠበቀና ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት ከሚታወቀው የኢንተርፖል ግሎባል አካዳሚ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ክቡር ኮሚሽነር ጀኔራል ለኢዜአ እንዳሉት፤ ዓለም አቀፍ ወንጀሎች በቴክኖሎጂ የታገዙና ውስብስብ የሆኑበት ዘመን ተፈጥሯል።

እነዚህን ውስብስብ ዓለም አቀፋዊ ወንጀሎች ለመቆጣጠርና ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ አቅም መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

በዚህም ኢንተርፖል ድንበር ዘለል ወንጀሎችን መከላከልና ወንጀል ሰርተው የተደበቁ አካላት ተላልፈው የሚሰጡበት ዓለም አቀፍ የተጓዦች ትስስር ቴክኖሎጂ ሥርዓት ማልማቱን ገልጸዋል።

ቴክኖሎጂው በሽብርተኝነት ወይም በሌላ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል የሚፈለጉ አካላትን በየትኛውም ሀገር ላይ በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀለኞችን ባሉበት ቦታ ለመያዝ ከኢሚግሬሽንና አየር መንገድ ጋር በሚኖረው ቅንጅት ላይ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ቴክኖሎጂው ወንጀለኛ የትም ቦታ መደበቅ እንዳይችል የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው፤ ገቢራዊ ለማድረግ በሂደት ላይ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እንዲጠናከር በማድረጋቸው ከኢንተርፖል ጋር ጥብቅ ትብብር መፍጠር ማስቻሉን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በሰራው የተቀናጀ ዘመቻ አንድ ወንጀለኛ ተይዞ ለኢትዮጵያ ተላልፎ እንዲሰጥና ለህግ እንዲቀርብ ተደርጓል ብለዋል።

ኢትዮጵያም በተለያዩ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች የሚፈለጉ አካላትን ሕግና ሥርዓት በመከተል ለሀገራት ተላልፈው እንዲሰጡ ማድረጓን ገልጸዋል።

ቴክኖሎጂው በቀን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በመከታተል ወንጀለኞችን በቀላሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በደረቅ ወደብና በሌሎች የትራንስፖርት ዘርፎች የሚስተዋሉ የሽብር እንቅስቃሴዎችና ወንጀሎችን ተከታትሎ መያዝ ያስችላል፤ በቅርቡም ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

✍️ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ ፤ታላቅ ርዕይ

"ሕዝብን ማገልገልና መጠበቅ ታላቅ ጸጋና ክብር ነው። ይህንን ታላቅ አደራ በታማኝነትና በቅንነት መወጣት ደግሞ የከበረ ሰብዕና እና የሞራል ልዕልና መገለጫ ነው!"​— ኮሚሽነር አለሙ መግራየድ...
01/11/2026

"ሕዝብን ማገልገልና መጠበቅ ታላቅ ጸጋና ክብር ነው። ይህንን ታላቅ አደራ በታማኝነትና በቅንነት መወጣት ደግሞ የከበረ ሰብዕና እና የሞራል ልዕልና መገለጫ ነው!"

​— ኮሚሽነር አለሙ መግራ
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ

"ወታደራዊ ሳይንስ፣ ልምድ እና ሕይወት የሰውን ልጅ ዓላማና ሰብእና በመቅረጽ ረገድ ተወዳዳሪ የለውም" - ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
31/10/2026

"ወታደራዊ ሳይንስ፣ ልምድ እና ሕይወት የሰውን ልጅ ዓላማና ሰብእና በመቅረጽ ረገድ ተወዳዳሪ የለውም"

- ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዘረፋና ከባድ የአካል ጉዳት ወንጀል ፈጽሞ በሌለበት 20 ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደበት ተከሳሽ በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ ማረሚያ ቤት ተላከተከሳሹ በወቅቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ የሕግ ሂደቱ...
31/10/2026

ዘረፋና ከባድ የአካል ጉዳት ወንጀል ፈጽሞ በሌለበት 20 ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደበት ተከሳሽ በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ ማረሚያ ቤት ተላከ

ተከሳሹ በወቅቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ የሕግ ሂደቱን በዋስትና ከእስር ቤት ውጭ እንዲከታተል የተፈቀደለት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

በድሬዳዋ ከተማ ዘረፋና ከባድ የአካል ጉዳት ወንጀል ፈጽሞ በሌለበት 20 ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደበትና ሲፈለግ የቆየ ግለሰብ፣ ለዓመታት በተደረገ የተቀናጀ የፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ ማረሚያ ቤት መላኩን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

በወቅቱ ምርመራውን የመሩት የወንጀል ምርመራ ቡድን መሪ ኢንስፔክተር ዘማች ያሬድ እንደገለጹት፣ ወንጀሉ የተፈጸመው ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ በድሬዳዋ ከተማ ጀሎ በሊና ገጠር ቀበሌ፣ ዳሎል በተባለው ነዳጅ ማደያ ውስጥ ነው ብለዋል።

ተከሳሹ ኡስማን ሙሳ በነዳጅ ማደያው የገንዘብ ያዥነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞችን ለመዝረፍ በማሰብ ወደ ማደያው በመግባት፣ በተበዳዮቹ ዓይን ላይ ሚጥሚጣ በመርጨት የገንዘብ ቦርሳቸውን ለመንጠቅ ሞክሯል ብለዋል።

በዚህም ወቅት በያዘው ስለት አንደኛውን ተበዳይ በደረትና በአንገት አካባቢ በመውጋት ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ድርጊቱን ለማስቆም ጣልቃ የገባውን ሌላኛውን ሠራተኛም በስለት እጁን አቁስሏል።
ከወንጀሉ በኋላ በአካባቢው ማኅበረሰብ ፈጣን ትብብር ተከሳሹ በቁጥጥር ሥር ውሎ በሕግ አግባብ ክስ እንዲመሠረትበት መደረጉን ፖሊስ አስታውሷል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ የእስረኞችና ወንጀለኞች ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ኢሳይያስ ኩመላ ለድሬ ፖሊስ ሚዲያ እንደገለጹት፣ ተከሳሹ የዋስትና መብቱን ተጠቅሞ ጉዳዩን ከእስር ቤት ውጭ ሆኖ እንዲከታተል በፍርድ ቤት ተፈቅዶለት ነበር። ሆኖም በተያዘለት ቀጠሮ በፍርድ ቤት ባለመቅረቡና አድራሻውን እየቀየረ በመሰወሩ ምክንያት ሲፈለግ ቆይቷል ብለዋል።

ፖሊስ ማኅበረሰቡንና የሚሊሻ አካላትን በማስተባበር ባደረገው የተቀናጀ ክትትል ተከሳሹን ከሁለት ዓመታት በኋላ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ኮማንደር ኢሳይያስ ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በተከሳሹ በሌለበት የሰጠውን የ20 ዓመት ጽኑ እስራት ውሳኔ እንዲፈጽም ወደ ማረሚያ ቤት ተልኳል።

ተከሳሹ በቁጥጥር ሥር ውሎ የሕግ ቅጣቱን ለመፈጸም መቻሉ እፎይታ እንደፈጠረባቸው የገለጹት የግል ተበዳዮች፣ በሂደቱ ለተከናወነው ሥራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
=================
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
#በፌስቡክ:-👇
📌በአማረኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100071007202116

📌በኦሮምኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100068806916386

📌ስፖርት :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100063887688997

📌ዩትዩብ፦https://youtube.com/?feature=shared

📌በቴሌግራም ቻናላችን
👉https://t.me/direpoli

📌ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/?_t=8fY2fIbUgSs&_r=1

፡፡


ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

30/10/2026

30/10/2026

#ድሬዳዋ ሰላሟን በነዋሪዎቿ አንደበት!!!

Address

Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Police posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dire Dawa Police:

Shortcuts

Share