President Mrs Alemitu omod

President Mrs Alemitu omod የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል ፕሬዚዳንት
President of the Gambella People's Regional State

በወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ከጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ :- በጋምቤላ ከተማ በተከሰተ የጸጥታ መደፍረስ ለዜጎች ሞትና መፈናቀል እንዲሁም የንብረት መውደም ምክንያት እንደነበ...
24/10/2026

በወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ከጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ :-

በጋምቤላ ከተማ በተከሰተ የጸጥታ መደፍረስ ለዜጎች ሞትና መፈናቀል እንዲሁም የንብረት መውደም ምክንያት እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከተማዋ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንድትመለስ የተለያዩ ሰራዎች ሲስራ ቆይቷል ።

ከተማ አሰተዳደሩ ከጸጥታ አካላትና ከከተማው ህብረተሰብ ጋር በመሆን ግጭቱን ለማስቆም የሄደበት ርቀት ውጤት አስገኝቶ ከተማዋ በአሁኑ ሰዓት ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሳለች ።

በመሆኑም የከተማችን ነዋሪዎች ጋምቤላ ከተማ ወደ ተሟላ ሰላም እየተመለሰች ስለሆነ ያለምንም የጸጥታ ስጋት መደበኛ ስራችሁን በተለመደው መልኩ እንድታከናውኑ ከተማ አስተዳደሩ ያሳውቃል ።

በጸጥታ ስጋት ምክንያት ከቤት ንብረታችሁ የተፈናቀላችሁ ወገኖቻችን አሁን ላይ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ስላለ ወደ ቀያችሁ ተመልሳችሁ የወንድማማችነት እና እህታማማችነት መንፈስ ማስቀጠልና አብሮ የመኖር ዕሴታችሁን ማዳበር እንዳለባቸሁ ጥሪ ያቀርባል ።

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ ነጋዴዎች በአጠቃላይ የንግድ ስራ ላይ የተሰማራችሁ ነዋሪዎች ያጋጠመን ችግር ጊዚያዊ ነበር ። በአሁኑ ሰዓት የሚያሰጋ የጸጥታ ችግር ባለመኖሩ እንደወትሮው ሁሉ መደበኛ ስራችሁን ከማከናወን ባለፈ የነዋሪዎችን ማህበራዊ መስተጋብር በሚያስቀጥል መልኩ በኃላፊነት መንፈስ መስራት እንዳለባችሁ መግለጽ ይወዳል ።

ከተማ አስተዳደሩ የጋምቤላ ከተማ ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ በመሠረተ ልማትና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማት ስራዎች ላይ አበክሮ ይሰራል ።

የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር
ጥቅምት 14/2019 ዓ/ም
ጋምቤላ

በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የፀረ-ሰላም ሀይሎችን ሴራ የሚያወግዝ እና ሰላምን ለማፅናት ያለመ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ሰልፈኞቹ የሰላምን አስፈላጊነት የሚሰብኩ መፈክሮችን ...
23/10/2026

በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የፀረ-ሰላም ሀይሎችን ሴራ የሚያወግዝ እና ሰላምን ለማፅናት ያለመ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

ሰልፈኞቹ የሰላምን አስፈላጊነት የሚሰብኩ መፈክሮችን በማሰማት ህዝባዊ አንድነታቸውን እና ለሰላም ያላቸውን ጽኑ አቋም አሳይተዋል።

​በሰልፉ ላይ የተገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በፀረ-ሰላም ሀይሎች ህዝብን ለመበታተን እና የልማት ስራዎችን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ጥረቶች ተቀባይነት እንደሌላቸው ገልጸዋል።

ሰላም የልማት እና የዕድገት መሰረት በመሆኑ ህዝቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ሰላሙን በንቃት መጠበቅ እንዳለበት ተመላክቷል።

20/10/2026

የጋምቤላ ከተማ የፀጥታ ሁኔታ ወደ መረጋጋት መመለሱን ተከትሎ ሰላምን የማስጠበቅና ለህብረተሰቡ ደህንነት የጋራ ኃላፊነት የመወጣት አስፈላጊነት ላይ የነዋሪዎች አስተያየት

በጋምቤላ ከተማ በነበረው የፀጥታ ችግር ዙሪያ ህዝባዊ የውይይት መድረኮች ተጀመሩ​በጋምቤላ ከተማ ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የተፈጠረውን ሁኔታ ለማረጋጋት እና ዘላቂ ሰላ...
20/10/2026

በጋምቤላ ከተማ በነበረው የፀጥታ ችግር ዙሪያ ህዝባዊ የውይይት መድረኮች ተጀመሩ

​በጋምቤላ ከተማ ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የተፈጠረውን ሁኔታ ለማረጋጋት እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ያለመ ህዝባዊ የውይይት መድረክ በአምስቱም ቀበሌዎች መካሄድ ተጀምሯል።

​በህዝባዊ መድረኮች የከተማው ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሸማግሌዎች እና የአካባቢው አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የውይይቱ ዋና ዓላማ በከተማዋ የተከሰተውን የፀጥታ መዛባት መንስኤዎች በመለየት፣ በህብረተሰቡ መካከል አብሮነትንና ወንድማማችነትን ማጠናከር እንዲሁም አስተማማኝ ሰላም ማስፈን የሚያስችሉ መፍትሔዎችን በጋራ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተገልጿል።

​በተጨማሪም የከተማውን ሰላምና ደህንነት ዘላቂ ለማድረግ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ያለው ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባና ለሰላም መደፍረስ ምክንያት የሚሆኑ ሁኔታዎችን በጋራ ለመከላከል እንደሆነም ተመላክቷል።

በክልሉ የተቋቋመው የፀጥታ ግብረ ሀይል ለህዝቡ ያቀረበዉ ጥሪጥቅምት 9/2019 ዓ.ምበጋምቤላ ከተማ በቅርቡ የተከሰተውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ፣ መንግሥት ከፀጥታ አካላትና ከሕዝቡ ጋር በተ...
19/10/2026

በክልሉ የተቋቋመው የፀጥታ ግብረ ሀይል ለህዝቡ ያቀረበዉ ጥሪ

ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም

በጋምቤላ ከተማ በቅርቡ የተከሰተውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ፣ መንግሥት ከፀጥታ አካላትና ከሕዝቡ ጋር በተቀናጀ መልኩ ባደረገው ጥረት አንጻራዊ ሰላም መመለሱን የፀጥታ ግብረ ኃይል አስታወቀ።

ግብረ ኃይሉ በከተማው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ በከተማው አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የፌዴራልና የክልሉ የፀጥታ አካላት በቅንጅት እየሠሩ መሆኑን ገልጿል።

በከተማው የሰላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱንና የአገልግሎት አሰጣጡም እየተሻሻለ መሆኑን የጠቆመው ግብረ ኃይሉ፣ ሕብረተሰቡ በፍርሃትና በስጋት ሳይገደብ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

በፀጥታ ችግሩ ምክንያት መኖሪያ አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ ወገኖችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጿል።

የመመለስ ሂደቱ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን መላው ሕብረተሰብ የሚጠበቅበትን ትብብር እንዲያደርግ አሳስቧል።

በተጨማሪም በችግሩ ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለው ገና ያልተመለሱ ወገኖች፣ በከተማው እየተሻሻለ የመጣውን የሰላም ሁኔታ በመገንዘብ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

የተመለሱ ወገኖች ስጋት እንዳለ የሚናፈሱ አሉባልታና ሀሰተኛ መረጃዎችን ባለመቀበል በቤታቸው ያለስጋት መኖር የሚችሉ መሆኑን ግብር-ሀይሉ ያሳስባል።

በሌላ በኩል፣ የፀጥታ ችግሩን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የዝርፊያ ሙከራዎችን የሚያደርጉ አካላት መኖራቸውን ግብረ ኃይሉ ጠቁሟል።

የፀጥታ አካላትም በሕገ ወጥ ድርጊቶቹ የተሰማሩ አካላትን በቁጥጥር ሥር ከማዋል ባለፈ፣ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ሕጋዊ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን አስታውቋል።

ሕብረተሰቡ በአካባቢው የሚያያቸውን አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችና ሌሎች ሕገ ወጥ ድርጊቶች በተመለከተ ለቅርብ የፀጥታ አካላት ወይም ለሚመለከታቸው አካላት በአፋጣኝ ጥቆማ በመስጠት የሰላምና ፀጥታ ሥራውን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርቧል።

ሰላምን ማስጠበቅ የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ፣ የመንግሥትንና የፀጥታ አካላትን ጥረት በመደገፍ የከተማውን ሰላም ማጠናከርና ዘላቂ ማድረግ ከሁሉም ዜጎች የሚጠበቅ የጋራ ተግባር ነው።

የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽንለጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ!በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ መደፍረስ የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረትና ቁርጠኝ...
17/10/2026

የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን

ለጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ!

በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ መደፍረስ የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረትና ቁርጠኝነት መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በከተማዋና በአካባቢዋ ሰላምና መረጋጋት እየሰፈነ ይገኛል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንም የተገኘው መረጋጋት ዘላቂ እንዲሆን እየተሠራ መሆኑን በመግለጽ፣ ማኅበረሰቡ ከስጋትና ከሐሰተኛ መረጃዎች ተጽዕኖ ራሱን በመጠበቅ በሰላም እንዲቆይ ያሳስባል።

በመሆኑም ተፈናቅለው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሄዱ ወገኖች የደኅንነታቸው ሁኔታ በተገቢው ሁኔታ መረጋገጡን በመረዳት ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ኮሚሽኑ ጥሪ ያቀርባል።

ለዚህም የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች ያስተላልፋል።

ሕዝቡ ወደ ቀዬው እንዳይመለስ ሊያደርጉ የሚችሉ ሐሰተኛ መረጃዎችንና ሕገወጥ ቅስቀሳዎችን እንዲጠነቀቅ፣ ያልተረጋገጡ መረጃዎችንም ከማሰራጨት እንዲቆጠብ ኮሚሽኑ ያሳስባል።

የሕዝቡን ወደ ቀዬው የመመለስ ሂደት የሚያደናቅፉና ማኅበረሰቡን ለስጋት የሚዳርጉ ድርጊቶች ላይ የተሰማሩ አካላት መኖራቸውን ተገንዝበናል።

በመሆኑም በተለይም አንዳንድ የመንግሥት ተሽከርካሪዎችና አሽከርካሪዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን ስጋት አለ በሚል ከከተማው ወደ ገጠራማና ወረዳ አካባቢዎች የማጓጓዝ ስራዎችን እየሰሩ በመሆኑ፤ ከድርጊታቸው በአፋጣኝ እንዲቆጠቡ እና ያለህጋዊ እውቅና እና የስራ ስምረት ያለአግባብ በህገ ወጥ መንገድ ተንቀሳቀሰው በሚገኙ ተሽካርካሪዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ኮሚሽኑ በጥብቅ ያስጠነቅቃል።

የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች የማኅበረሰብ ተወካዮች ሰላምን ለማስፈን፣ መረጋጋትን ለማጠናከርና የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እያደረጉ ያሉትን ጥረት እንዲያጠናክሩ ኮሚሽኑ ጥሪ ያቀርባል።

የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሰላምን በማስፈን፣ የሕዝብን ደኅንነት በመጠበቅና የተገኘውን መረጋጋት በማጽናት ረገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ኮሚሽኑ ያሳስባል።

በአጠቃላይ፣ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ሰላም በመንግሥት የፀጥታ አካላት ጥረት ብቻ ሳይሆን፣ በመላው ማኅበረሰብ ትብብርና ኃላፊነት የሚረጋገጥ መሆኑን ኮሚሽኑ ያስገነዝባል።

ስለሆነም ሁሉም የሰላምን ዋጋ በመረዳት፣ ከማንኛውም ሕገወጥ ድርጊት በመቆጠብና ለሰላም መስፈን በጋራ በመሥራት የከተማዋን መረጋጋት እንዲያጠናክሩ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀርባል።

የጋምቤላ ከተማን ሰላም ወደ መደበኛ  ለመመለስ ከሃይማኖት አባቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።በጋምቤላ ከተማ በሰሞኑ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የተፈጠረውን አለመረጋጋት ...
16/10/2026

የጋምቤላ ከተማን ሰላም ወደ መደበኛ ለመመለስ ከሃይማኖት አባቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።

በጋምቤላ ከተማ በሰሞኑ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የተፈጠረውን አለመረጋጋት በመግታት፣ ከተማዋ ወደነበረችበት መደበኛ ሰላምና ወንድማማችነት እንድትመለስ ለማድረግ ከሃይማኖት ተቋማት አባቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

​በቅርቡ በደረሰው የፀጥታ ችግር የሰው ህይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህንን አሳዛኝ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመቀየር አካባቢውን ወደ ዘላቂ ሰላም ማሸጋገር እንደሚገባ በውይይቱ ወቅት ተመላክቷል።

​የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ እንደገለፁት፣ የጋምቤላ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ በፍቅርና በወንድማማችነት አብሮ የኖረ ህዝብ በመሆኑ፣ ይህንኑ የመቻቻልና የእህትማማችነት እሴት ጠብቆ ማስቀጠል የሁላችንም ታሪካዊ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

የሃይማኖት አባቶች ህዝቡን በምክርና በጸሎት በማስተሳሰር በኩል ያላቸው ሚና የጎላ በመሆኑ፣ አሁንም ህዝቡን ወደ ሰላምና አንድነት በመመለስ ረገድ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ወጣቱ ስሜቱን በመግታትና ነገሮችን በሰከነ መንፈስ በማስተዋል የሰላም ዘበኛ ሊሆን እንደሚገባው አሳስበዋል።

በመሆኑም የሃይማኖት አባቶች ወጣቱን በስነ-ምግባር በመቅረፅና የሰላምን ዋጋ በማስተማር፣ አላስፈላጊ ከሆኑ ድርጊቶች እንዲቆጠብ የማድረግ ታላቅ አደራ እንዳለባቸውም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

​የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን በበኩላቸው፣ በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው ለመመለስና መልሶ ለማቋቋም አስፈላጊውን ጥረት እንደሚደረግ አስረድተዋል።

የተፈናቀሉትን ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብና ዋስትና በመስጠት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀያቸው መመለስ የሁሉም ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ አስረድተዋል።

ይህንን ተፈናቃዮችን ወደ መደበኛ ህይወታቸው የመመለስ ሂደት ስኬታማ ለማድረግ ከመንግስት ጎን ለጎን የሃይማኖት አባቶችና የመላው የክልሉ ህዝብ ትብብርና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

​በብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አሽኔ አስቲን እንዳሉት፣ ሰላም የሁሉም ልማትና እድገት መሰረት በመሆኑ ማንኛውም ልዩነት በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት አለበት ብለዋል።

ለሰላም መደፍረስ ምክንያት የሆኑ አስተሳሰቦችን በጋራ መታገል እና ስለ ሰላም መስበክ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

​የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የህዝብ ድልድይ በመሆን ወጣቱን በበጎ መንገድ የመምራትና የመምከር ሀላፊነታቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በጋራ በመቆም የተጎዱትን በመደገፍና የተፈናቀሉትን በመመለስ የጋምቤላን የቀደመ ሰላምና ፍቅር ለመመለስ እንተባበር ብለዋል።

​የተሳተፉት የሃይማኖት አባቶች የተጣለባቸውን ታሪካዊ አደራ በመቀበል፣ ወጣቱን የማስተማርና ምእመናንን ለሰላምና ለፍቅር የመቀስቀስ ስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የጥላቻና የልዩነት ንግግሮችን ወደ ጎን በመተው፣ አካባቢውን በጋራ የመጠበቅና የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው በመመለሱ ሂደት ህዝቡ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል።

በጋምቤላ ከተማ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የሀይማኖት አባቶች ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከሃይማኖት አባቶች ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል።​የጋምቤ...
16/10/2026

በጋምቤላ ከተማ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የሀይማኖት አባቶች ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከሃይማኖት አባቶች ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል።

​የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በሰሞኑ በከተማዋ በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ሳቢያ የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።

የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ አቶ ቱት ጆክ በከተማው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የማህበረሰቡ ዕለታዊ እንቅስቃሴ ወደ ቀድሞ ሁኔታው እንዲመለስ የሁሉም ወገኖች ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

ከንቲባው ከሀይማኖት አባቶች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ በከተማው የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በአጭር ጊዜ ተረጋግቶ ህዝቡ ወደ መደበኛ ህይወቱ እንዲመለስ የሁሉም አካላት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በተለይም የሀይማኖት መሪዎች በሰላም ግንባታ፣ በማህበረሰብ መስተጋብርና በሰዎች መካከል የመተማመን ስሜት በመፍጠር ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሀይማኖት አባቶች ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለይቅርታና ለአንድነት የሚያበረታቱ መልዕክቶችን ለምዕመናንና ለመላው ማህበረሰብ በማስተላለፍ በከተማው የተፈጠረው ውጥረት እንዲቀንስና ሰላማዊ የአብሮነት ሁኔታ እንዲፈጠር የበኩላቸውን እንዲወጡ ከንቲባው አሳስበዋል።

በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል መግባባትን ማጠናከርና የጥላቻ ንግግሮችን በማስወገድ የጋራ ሰላምን ማስጠበቅ ከሁሉም ወገኖች የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑንም አመልክተዋል።

የጋምቤላ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ ቄስ ኝጎዎ ኡሞድ በበኩላቸው ወጣቶች ከማንኛውም የግጭት ተግባር በመራቅ፣ የተሳሳተ መረጃን ከማሰራጨት በመቆጠብ፣ የሰላምና የመቻቻል መልዕክቶችን በማስተላለፍ እንዲሁም ለህግና ለህዝብ ደህንነት በማሰብ በተግባር እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የከተማው ሰላም መረጋገጥ የነዋሪዎችን ደህንነት ከመጠበቅ ባለፈ የንግድ፣ የትምህርት፣ የትራንስፖርትና ሌሎች የማህበረሰብ አገልግሎቶች ያለ ስጋት እንዲቀጥሉ መሠረት እንደሚሆን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፣ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖች ደህንነታቸው በአግባቡ ተጠብቆ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ተገቢው ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት አስፈላጊነቱ ተጠቁሟል።

የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ደህንነታቸው፣ የመኖሪያ ሁኔታቸውና መሠረታዊ ፍላጎቶቻቸው በተገቢው መንገድ መታየት እንዳለባቸውም የሰላም ግንባታው አካል መሆኑን ተገልጿል።

በከተማው የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ተረጋግቶ ነዋሪዎች ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እንዲመለሱ፣ የተቋረጡ አገልግሎቶች እንዲቀጥሉና የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የመንግሥት አካላት፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ ወጣቶችና መላው ማህበረሰብ በቅንጅት መሥራት ወሳኝ ነው።

ሰላምን ማስፈን የአንድ አካል ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ወገኖች የጋራ ጥረትና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን ተገልጿል።

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና የአድማ ብተና አመራሮች የፖሊስ መኮንኖችን ሥነ-ምግባር በተመለከተ ጥልቅ ውይይት አካሄዱ።ጋምቤላ (ጥቅምት 3/2019 ዓ/ም)...
13/10/2026

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና የአድማ ብተና አመራሮች የፖሊስ መኮንኖችን ሥነ-ምግባር በተመለከተ ጥልቅ ውይይት አካሄዱ።

ጋምቤላ (ጥቅምት 3/2019 ዓ/ም) - ​በመድረኩ ላይ በፖሊስ የሥነ-ምግባር ዋና ዋና መርሆዎች፣ እነዚህን መርሆዎች በዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ተግባራዊ በሆነ መንገድ ማዋል በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም መርሆዎቹ በሚጣሱበት ወቅት በሚከሰቱ ተቋማዊና ማህበራዊ ችግሮች ላይ ያተኮረ የውይይት ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ስብሰባ ተካሂዷል።

​ተሳታፊ አመራሮቹ በውይይቱ ወቅት የፖሊስ መኮንኖች የሥነ-ምግባር መርሆዎችን በአግባቡ በመተግበር፣ በክልሉ የህግ የበላይነትን ለማስከበር፣ የፍትህ ሥርዓቱን ለማጠናከር እና ህዝባዊ አገልግሎትን በተሻለ ደረጃ ለማቅረብ የሚያስችል አስፈላጊ ትምህርትና አቅም መቅሰማቸውን ገልጸዋል።የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና የአድማ ብተና አመራሮች የፖሊስ መኮንኖችን ሥነ-ምግባር በተመለከተ ጥልቅ ውይይት አካሄዱ።

ጋምቤላ (ጥቅምት 3/2019 ዓ/ም) - ​በመድረኩ ላይ በፖሊስ የሥነ-ምግባር ዋና ዋና መርሆዎች፣ እነዚህን መርሆዎች በዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ተግባራዊ በሆነ መንገድ ማዋል በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም መርሆዎቹ በሚጣሱበት ወቅት በሚከሰቱ ተቋማዊና ማህበራዊ ችግሮች ላይ ያተኮረ የውይይት ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ስብሰባ ተካሂዷል።

​ተሳታፊ አመራሮቹ በውይይቱ ወቅት የፖሊስ መኮንኖች የሥነ-ምግባር መርሆዎችን በአግባቡ በመተግበር፣ በክልሉ የህግ የበላይነትን ለማስከበር፣ የፍትህ ሥርዓቱን ለማጠናከር እና ህዝባዊ አገልግሎትን በተሻለ ደረጃ ለማቅረብ የሚያስችል አስፈላጊ ትምህርትና አቅም መቅሰማቸውን ገልጸዋል።

(ጥቅምት 03/2019)የአኝዋሃ ብሄ/ዞን  አዲስ ለተሾሙት ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦጁሉ አባዶ ኩዎት የስራ ርክክብ ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት አድርገዋል።
13/10/2026

(ጥቅምት 03/2019)

የአኝዋሃ ብሄ/ዞን አዲስ ለተሾሙት ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦጁሉ አባዶ ኩዎት የስራ ርክክብ ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት አድርገዋል።

Address

Gambela

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when President Mrs Alemitu omod posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share