11/09/2026
"በአዲሱ ዓመት—ታማኝነትንና ግልጽነትን በማጠናከር ሙስናን በጋራ እንከላከል!"
**** ***** ****** *****
(የጋም.ሥ.ፀ.ኮ1/1/19 ዓም ጋምቤላ)
ለመላው የጋምቤላ ክልል ሕዝብ፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች እና ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሕዝቦች በሙሉ፦
በመጀመሪያ እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም፣በጤና፣ በፍቅር እና በሕይወት አደረሳችሁ!
ያለፈው ዓመት የሥራ አፈጻጸማችንን በመገምገም፣ በ2019 ዓ.ም በክልላችን ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት፣ ከሙስና የጠራ የአሠራር ሥርዓት ለመገንባት በቁርጠኝነት የምንነሳበት አዲስ ምዕራፍ መሆን አለበት እላለሁ።
በዚህ በአዲሱ 2019 ዓ.ም በክልላችን የሥነ-ምግባር እሴቶችን ይበልጥ ለማስረጽ፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ብልሹ አሠራሮችን በቆራጥነት ለማረም በጋራ የምንሠራበት አዲስ ምዕራፍ እንዲሆንልን ኮሚሽኑ ይመኛል። የክልላችን ዘላቂ ልማትና የሕዝባችን ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው እያንዳንዱ አመራርና ሠራተኛ በየተሰማራንበት የሥራ መስክ በታማኝነት፣በተጠያቂነት እና በሀገራዊ ኃላፊነት ስሜት እና ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ንቁ ተሳትፎና ታማኝነት ሕዝብን ስናገለግል ነው።
አዲሱ ዓመት የ2019 ዓ.ም የሰላም፣ የጤና፣የብልጽግና የፍቅር እና የሥነ-ምግባር ግንባታ ዓመት ይሁንልን!