Gambella Police Commission

Website

Gambella Police Commission በጀግንነት መጠበቅ፣ በሰብዓዊነት ማገልገል!

19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን የፊታችን ሰኞ ዕለት ይከበራል*******19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባት እና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ፕሬ...
10/10/2026

19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን የፊታችን ሰኞ ዕለት ይከበራል
*******
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባት እና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት ይከበራል።

ቀኑ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር ምክር ቤቱ አስታውቋል።

የብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሠንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 (እንደተሻሻለው) አንቀጽ 2 መሠረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ይደነግጋል።

ይህ በዓል ኢትዮጵያውያን የሀገርን ዳር ድንበር እና ክብሯን ለማስጠበቅ ደም እና ላባቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ያስከበሩት ሠንደቅ ዓላማ በጋራ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሠንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር የመስጠት እና የማክበር ኃላፊነት እና ግዴታ አለበት።

ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ በዋናነት የኢትዮጵያውያን የማንነት መገለጫ እና ዓርማ ነው። ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን የሚከበርበት ዋና ዓላማ ለሠንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት ዜጎች የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያጠናክሩበት እና በሀገራዊ አንድነት እና ኅብረ ብሔራዊነት መግባባትን የሚፈጥሩበት ሀገራዊ በዓል በመሆኑ ነው።

ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን መከበር ከጀመረ እነሆ 18 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪነት እና አስተባባሪነት በመላ ሀገራችን ወቅታዊ ሀገራዊ እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በድምቀት እና በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ይከበራል።

በዚህም መሠረት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ዕለቱን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን መልዕክት በማስተላለፍ በንግግር ከከፈቱ በኋላ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አማካኝነት በቀጥታ ስርጭት በመላው ሀገራችን ዜጎች በሠንደቅ ዓላማው ፊት ቃለ መሐላ የሚፈጸምበት ሥነ ሥርዓት ይፈጸማል።

ከዚያም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ እና ክብር ዘብ ታጅበው በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት አማካኝነት ሠንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ይከናወናል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት፣ ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዐርበኞች ማኅበር እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

ይህ በዓል በመላው ሀገራችን በሚገኙ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች በተመሳሳይ ሰዓት በድምቀት እንደሚከበር ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የጋምቤላ ፖሊስ ኮሚሽን የማኔጅመንት ኮሚቴ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አሳለፈ​ጋምቤላ — የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የማኔጅመንት ኮሚቴ ከመስከረም 29 እስከ መስ...
10/10/2026

የጋምቤላ ፖሊስ ኮሚሽን የማኔጅመንት ኮሚቴ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አሳለፈ

​ጋምቤላ — የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የማኔጅመንት ኮሚቴ ከመስከረም 29 እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ፣ በተለያዩ የመዋቅር፣ የሰው ኃይል፣ የንብረትና የሕግ ማስከበር አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት በመወያየት በርካታ መሠረታዊ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

​በሁለት ቀናት የተጠናከረ ውይይት በተካሄደው በዚህ የማኔጅመንት ኮሚቴ ስብሰባ፣ የኮሚሽኑን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻልና የወንጀል መከላከል አቅምን ለማጠናከር የሚያስችሉ የሚከተሉት ዋና ዋና ውሳኔዎች ተወስደዋል፦

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን ለመድፈን በተወሰኑ ክፍት መደቦች ላይ አዳዲስ የምደባ ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ የኮሚሽኑን ንብረትና ሀብት በጥንቃቄና በቁጠባ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችሉ ውሳኔዎች ተላልፈዋል።

የወንጀል ጉዳዮችን በፍጥነትና በብቃት መርምሮ ለፍትሕ ለማቅረብ ያስችል ዘንድ የተደራጀ የፈጣን ችሎት (Speedy Trial) ምርመራ ቡድን እንዲቋቋም ተወስኗል።

የክልሉን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስጠበቅ የወንጀል መከላከል ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን፤ የህብረተሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት (Community Policing) አሠራርን ይበልጥ ወደ ህብረተሰቡ ለማውረድና የሕዝብ ተሳታፊነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ውሳኔዎች አስተላፈዋል።

​ይህ የማኔጅመንት ኮሚቴው ውሳኔ የኮሚሽኑን ውስጣዊ አሠራር ከማጠናከሩ ባሻገር፣ በክልሉ አስተማማኝ ሰላምና የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

በጋምቤላ ከተማ በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ዙሪያ በአምስቱም ቀበሌዎች ውይይት ተካሄደ ።  ጋምቤላ  (መስከረም 27/2019)-- በጋምቤላ ከተማ ያለውን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በአምስቱ...
08/10/2026

በጋምቤላ ከተማ በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ዙሪያ በአምስቱም ቀበሌዎች ውይይት ተካሄደ ።

ጋምቤላ (መስከረም 27/2019)-- በጋምቤላ ከተማ ያለውን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በአምስቱም ቀበሌዎች ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል ።

በውይይቱም ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የከተማው ነዋሪዎች የድርሻቸውን መወጣት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል ።

ጋምቤላ ከተማ ከግጭት አዙሪት ወጥታ እንደ ሌሎች ከተሞች በመሰረተ ልማትና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋ የተሻለች ሆና ለነዋሪዎች ምቹና በነጻነት የሚንቀሳቀሱባት ለማድረግ ይቻል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተጠቁሟል ።

የከተማው ህብረተሰብ ወቅታዊ ሁኔታውን ተገንዝቦ ሰላምና ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራና ያለ ህብረተሰብ ተሳትፎ ሰላም ሊረጋገጥ ስለማይችል ከመንግስት የጸጥታ አካላት ጎን ተሰልፎ የራሱን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ጥሪ ቀርቧል ።

ከጋም/ከ/መን/ኮሙ/ጉ/ጽ/ቤት

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ከፖሊስ አመራሮችና አባላት ጋር የትውውቅ መድረክ አካሄዱ​ጋምቤላ (መስከረም 27/2019 ዓ/ም)--- የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን...
07/10/2026

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ከፖሊስ አመራሮችና አባላት ጋር የትውውቅ መድረክ አካሄዱ

​ጋምቤላ (መስከረም 27/2019 ዓ/ም)--- የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ኡጁሉ ኡዶል እና ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ጋትሉዋክ ጋች በደረጃው ከሚገኙ የፖሊስ አመራሮች እና የኦፕሬሽን አባላት ጋር የትውውቅ ፕሮግራም እና የሥራ መመሪያ መድረክ አድርገዋል።

​በመድረኩ ላይ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችሉ ቁልፍ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

​የፖሊስ ሥራዎች ሁልጊዜ በዕቅድ መመራት እንዳለባቸውና በሙያዊ መንገድ መከናወን እንደሚገባቸው ተገልጿል። ፖሊስ የሕግ የበላይነትን የማክበር እና የማስከበር ቀዳሚ ኃላፊነቱን በከፍተኛ ዲስፕሊንና ሥነ-ምግባር ሊወጣ ይገባል።

​በተጨማሪም ወንጀልን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ በቅንጅት መስራት፤ ወንጀል ተፈፅሞ ከተገኘ ደግሞ አፋጣኝ ማጣራት በማድረግ ወንጀለኞችን ለሕግ ማቅረብ ይገባል። የሰው ኃይል አቅምን በሚገባ አውቆ በአግባቡ መምራት እና በአባላት መካከል ግልጸኝነትንና ጠንካራ መተማመን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።

​በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የኮሚሽኑ አመራሮችና አባላት እንዳሉት፤ ከዛሬ ጀምሮ ሁሉም የፖሊስ አባላት በአንድ መንፈስና በጋራ ተነሳሽነት ወደ ሥራ በመግባት የክልሉን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ እንዳለባቸው አበክረው አሳስበዋል።

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ከማኔጅመንት አባላት ጋር ትውውቅ አደረጉ​ጋምቤላ (መስከረም 25/2019 ዓ.ም) — የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር...
05/10/2026

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ከማኔጅመንት አባላት ጋር ትውውቅ አደረጉ

​ጋምቤላ (መስከረም 25/2019 ዓ.ም) — የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ኡጁሉ ኡዶል እና ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ጋትሉዋክ ጋች ከኮሚሽኑ የማኔጅመንት አባላት ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

በትውውቅ መድረኩ ላይም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እና የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ሰፊ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች፥ ተቋሙ ሕዝብን በታማኝነትና በገለልተኝነት የሚያገለግል፣ ሰላምና ጸጥታን በማስፈን ረገድ ግንባር ቀደም ሚናውን አጠናክሮ የሚቀጥልበትን አሰራር መዘርጋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

​ክቡር ኮሚሽነር አቶ ኡጁሉ ኡዶል በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የክልሉን ሕዝብ ደህንነትና ሰላም በማስጠበቅ ረገድ የፖሊስ ሰራዊቱ አርአያ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

በሰራዊቱ ውስጥ ጠንካራ የዲሲፕሊንና የአሰራር ተጠያቂነት ስርዓት እንዲሰፍን የማኔጅመንቱ አባላት ተቀናጅተው ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ተቋማዊ አላማዎችን ከግብ ለማድረስ ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

​ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ጋትሉዋክ ጋች በበኩላቸው፥ ስራዎች በቅንጅትና በፈጣን ምላሽ ሰጪነት መመራት እንዳለባቸው ጠቁመው፣ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ የማጎልበት ሥራዎች ትኩረት እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።

በመጨረሻም​ የማኔጅመንት አባላቱ በበኩላቸው፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው፣ የተቋሙን አሰራር ለማሻሻልና ሰላምን አስተማማኝ ለማድረግ በጋራ እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል።

የጋምቤላ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መግለጫ​በማኅበራዊ ድረ-ገጾች ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል!​በጋምቤላ ክልል የሚኖረውን ሕዝብ ሰላምና አ...
05/10/2026

የጋምቤላ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መግለጫ

​በማኅበራዊ ድረ-ገጾች ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል!

​በጋምቤላ ክልል የሚኖረውን ሕዝብ ሰላምና አብሮነት ለማወክ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ-ገጾች ሀሰተኛና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ከእኩይ ድርጊታቸው በአስቸኳይ እንዲቆጠቡ የክልሉ መንግሥት ያሳስባል።

​ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ዋና ዓላማ ለዘመናት በፍቅርና በፍጹም አብሮነት የኖረውን የጋምቤላ ሕዝብ ሰላም ማደፍረስና ወንድማማችነቱን ማወክ እንደሆነ ጠቁሟል።

​ባለፉት ሁለት ቀናት የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለክልሎች አጀንዳ በሚያስረክብበት ወቅት የጋምቤላ ክልል አጀንዳ ርክክብ አልተደረገም ተብሎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሙሉ በሙሉ ሀሰተኛ መሆኑን ጽሕፈት ቤቱ አረጋግጧል።

​በርክክቡ ወቅት በሥራ መደራረብ ምክንያት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ በቦታው ለመድረስ መዘገየታቸውን የጠቆመው መግለጫው፤ በዕለቱ ርክክብ ባይደረግም በትላንትናው ዕለት በቀን 24/1/2019ዓ.ም አጀንዳው በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ከአቶ አገኘው ተሻገር በኩል ለጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ በይፋ መረከቡን አስታውቋል።

​ይህን እውነት ወደ ጎን በመተው በርክክቡ ወቅት የተነሳው ፎቶ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተቀናበረ ነው በሚል ሀሰተኛ መረጃ ማናፈስና ሕዝቡን ማደናገር በፍጹም ትክክል አለመሆኑ ተመላክቷል።

በሀገራዊ የምክክር ሂደት ከክልሉ የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በስፋት በመሳተፍ ዋና ዋና አጀንዳዎች ተለይተው ውይይት መካሄዱ ይታወሳል።

በዚሁ መሠረት የጋምቤላ ክልልም የክልሉን ተጨባጭ ሁኔታና የህዝቡን ጥያቄዎች የሚያንፀባርቁ አጀንዳዎችን ለይቶ ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አቅርቦ አጀንዳዎቹም በትላንትናው እለት ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ተረክበዋል።

​በመጨረሻም፣ በክልሉ ሰላም ላይ ስጋት በሚፈጥሩ፣ ሕዝብን ከሕዝብ በሚያጣሉና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ሕዝብን በሚያናውጡ አካላት ላይ መንግሥት የማያወላውል እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

የክልሉ ሕዝብ አላስፈላጊ ውዥንብር የሚፈጥሩ አካላትን አጀንዳ በመረዳት ባልተረጋገጡ የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃዎች ሳይናወጥ፣ እውነተኛና ትክክለኛ መረጃዎችን ከመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ብቻ እንዲከታተልና ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የክልሉን ዘላቂ ሰላም እንዲያስጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።

በጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አዲስ የተሾሙ አመራሮች የሥራ ርክክብ አደረጉ​ጋምቤላ (መስከሰም  24  ቀን 2026) — የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አዲስ የተሾሙትን የኮሚሽኑ መሪዎች እና ...
04/10/2026

በጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አዲስ የተሾሙ አመራሮች የሥራ ርክክብ አደረጉ

​ጋምቤላ (መስከሰም 24 ቀን 2026) — የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አዲስ የተሾሙትን የኮሚሽኑ መሪዎች እና የቀድሞ አመራሮች ያካተተ ይፋዊ የሥራ ርክክብ ሥነ ሥርዓት ማካሄዱን አስታወቀ።

​በዚሁ መሠረት ክቡር አቶ ኡጁሉ ኡዶል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር እንዲሁም ክቡር አቶ ጋትሉዋክ ጋች የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር በመሆን መሾማቸው ታውቋል።

​የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ማኔጅመንት ኮሚቴ በተገኘበት በተከናወነው የርክክብ ሥነ ሥርዓት፤ የቀድሞው ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዶሮ ካሩ እና ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ቾት ኒት ኃላፊነታቸውን ለአዲሶቹ መሪዎች አስረክበዋል።

በዕለቱ የኮሚሽኑን ባለፈው ጊዜያት ዕቅድ መሠረት የተከናወኑ መልካም ሥራዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጅምር ሥራዎች በዝርዝር መነሻ ተደርገው ገለጻ ተደርጎባቸዋል።

የተገኙ ውጤቶችን የበለጠ ለማስቀጠል እና ክፍተቶችን በጋራ ለመሙላት የኮሚሽኑ ማኔጅመንት ኮሚቴ ለአዲሱ አመራር ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ አረጋግጧል።

​አዲሶቹ የኮሚሽኑ አመራሮች የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ከማስከበር ባለፈ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ከኅብረተሰቡ ጋር ያለውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ጠንክረው እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ አስቸኳይ የሥራ ማሳሰቢያ ​በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ ገበታቸው ርቀው የሚገኙ የክልሉ አድማ ብተና ፖሊስ አባላት በሙሉ፤ ኮሚሽኑ የሚከተለውን ጥብቅ መመሪያ አስተ...
04/10/2026

ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ አስቸኳይ የሥራ ማሳሰቢያ

​በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ ገበታቸው ርቀው የሚገኙ የክልሉ አድማ ብተና ፖሊስ አባላት በሙሉ፤ ኮሚሽኑ የሚከተለውን ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል።

​ከዛሬ ከመስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ድረስ ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ እያንዳንዱ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት በየምድብ የሥራ ቦታቸው በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን ።

በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የተንቀሳቀሱት አባላትም በአቅራቢያችሁ ለሚገኙ ለወረዳዎች አስተዳደር የፓሊስ መዋቅር በአፋጣኝ ሪፖርት እንድታደርጉ ሆኖ ​በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ በሥራ ገበታቸው ላይ ተገኝተው ሪፖርት በማያደርጉ አባላት ላይ ኮሚሽኑ ተገቢውን ጥብቅ አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አበክሮ ያስገነዝባል። ለዚህም ተግባር ተፈጻሚነት እንዲሆን በየደረጃው የተመደቡ የአድማ ብተና እና የመደበኛ ፓሊስ አመራሮች ተገቢውን እንዲያደረጉ ጭምር በጥብቅ እናሳስባለን።

​የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን

መስከረም 24/2019 ዓ.ም

03/10/2026
የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን የመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት​የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዶሮ ካሩ ...
26/09/2026

የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን የመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

​የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዶሮ ካሩ የመስቀል በዓልን አስመልክተው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታ ገልጸው፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

​በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅር ባይነት እና የአብሮነት መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ሕዝቦች ያለውን አንድነት እና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ሕብረተሰቡ በዓሉን በሰላም፣ በድምቀት እና ያለምንም ስጋት ማክበር እንዲችል የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን የደህንነት እና የጥንቃቄ ሥራዎች ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

በዓሉ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ መላው የክልሉ ሕዝብ ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሕግን እና ደንብን ተከትሎ ማክበር እንዳለበት አሳስበዋል።

​ኮሚሽነሩ መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓልን በሰላም፣ በጤና እና በደስታ እንዲያሳልፉ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

Address

Gambella Police Commission
Gambela
P.O.BOX24

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gambella Police Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share