Gimbo Woreda Communication Affairs

Call

Gimbo Woreda Communication Affairs Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gimbo Woreda Communication Affairs, Government Organization, adis ababa, Gimbo.
(2)

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ...
05/10/2026

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።


ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ**********************የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 7ኛው ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመንግሥት መ...
05/10/2026

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ
**********************

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 7ኛው ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመንግሥት መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

በዚህ የ7ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ጉባኤ የመንግሥት መመሥረቻ ስብሰባ ላይ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

! ! !

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በእጩነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረቡ  !  !  !
05/10/2026

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በእጩነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረቡ

! ! !

አቶ አልማው ዘውዴ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ ተሾሙአቶ አልማው ዘውዴ በኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አስተምህሮ ኮሚቴ ጸ...
05/10/2026

አቶ አልማው ዘውዴ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ ተሾሙ

አቶ አልማው ዘውዴ በኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አስተምህሮ ኮሚቴ ጸሐፊ ሆነው ተሹመዋል።

አቶ አሕመድ ሽዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ቃለ መሐላ ፈፀሙ EBC
05/10/2026

አቶ አሕመድ ሽዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ቃለ መሐላ ፈፀሙ

EBC

የጊምቦ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት ፓርቲ ኮሚቴ በወረዳው እየተከናወኑ በሚገኙ ወቅታዊ የፓርቲና የመንግሥት ተግባራት ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎች ላይ ዉይይት አካሄደ ። የቀበሌዎች ...
05/10/2026

የጊምቦ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፓርቲ ኮሚቴ በወረዳው እየተከናወኑ በሚገኙ ወቅታዊ የፓርቲና የመንግሥት ተግባራት ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎች ላይ ዉይይት አካሄደ ።

የቀበሌዎች የሥራ ዕቅድ አፈጻጸምና የአባላት መዋጮ አሰባሰብና ልዩ ልዩ ልማታዊና አስተዳደራዊ ተግባራት ላይ ሰፊ ዉይይቴ አካህዷል ።

የቀበሌዎች የፓርቲ አደረጃጀት ዕቅድ አፈጻጸም በየቀበሌው የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ያሉበት ደረጃ የተገመገመ ሲሆን የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ክፍተቶችን በመሙላት ዕቅዶችን በወቅቱ ማጠናቀቅ እንደሚገባ ተመላክቷል።

የአባላት መዋጮና የፋይናንስ ጥንካሬ የፓርቲውን የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር የአባላት መዋጮ አሰባሰብ ሂደት የተገመገመ ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ አባላትና አመራሮች መዋጮቸውን በወቅቱና በሙሉነት እንዲወጡ ተገልጸዋል ።

ወቅታዊ የልማትና የመንግሥት ተግባራት በወረዳው የሚከናወኑ የግብርና፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ልማት ሥራዎች አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን፣ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ውጤታማነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባ ታምኖበታል።

በዉይይቱ ማጠቃለያም የተያዙ ዕቅዶችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማጠናቀቅ የአመራሩንና የአባሉን ቅንጅታዊ አሠራር አጠናክሮ ለመቀጠል የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል ሲል የዘገበው የጊምቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ሁሉንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ  በትኩረት እየተሰራ  ነው፦  አቶ መቅደስ ማም።ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ /ም  ጠቋሚ ዕቅድ ውይ...
05/10/2026

ሁሉንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው፦ አቶ መቅደስ ማም።

ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ /ም ጠቋሚ ዕቅድ ውይይት መድረክ ማካሄድ ጀምሯል ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የመምሪያ ኃላፊ አቶ መቅደስ ማሞ እንዳሉት ጠንካራ የፋይናንስ ሰራር ሥርዓት በመዘርጋት የህብረተሰቡን ሁሉንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው።

እንደ አቶ መቅደስ ማብራሪያ የፋይናንስ መምሪያ ከመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ተቋማት መካከል አንዱ በመሆኑ የአሰራር ሥርዓት በማዘመን የላቀ ውጤት እንዲያመጣ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።

ይህም በላቀ ቁርጠኝነትና በውጤታማ የሪፎርም ሥራዎች ተደግፎ ያለውን ሀብት በተገቢና በቁጠባ ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ተጠናክሮ ይቀጥላ ብለዋል ።

የፋይንስ ሥርዓቱ የሪፎርም ሥራዎችን መሰረት አድርጎ በዕቅድ እንዲመራ ልዪ ክትትልና ድጋፍ ሥርዓት እንደሚዘረጋም አቶ መቅደስ አመላክተዋል ።

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅት ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አሻግሬ አደመ እንዳሉት የፋይናንስ መድረክ ሀገራችን ኢትዮጵያ አዲስ መንግስት ምሥረታ በሚታደርግበት ወቅት መሆኑ መድረኩን ልዩ ያደርጋል ብለዋል ።

መድረኩ የተመዘገቡ አበረታቾ ውጤቶች ተጠናክሮ የሚቀቀጥሉበና ከአሰራር ሥር ዓት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉት ጉድለቶችን ለማረም የሚያስችል አቅም የሚፈጥር መድረክ ነውም ብለዋል ።

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የልማት ዕቅድ ዝግጅት ክትትል ሥራ አስተባባሪ አቶ ሙላቱ ገ/ስላሴ የ2018 ዓ/ም በጀት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ነው ።

መምሪያው የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ጠቋም ዕቅድ ሌሎች የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችና ልዩ ልዩ መርሀ-ግብር ላይ የጋራ ሀሳብ ተይዞ እንዲሚቋጭ ከወጣ ፕሮግራም ተገልጸዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል ።

ጠንካራ መሠረት የያዘውን የክልሉን የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ግኝኑነት ሥራዎችን በበለጠ ለማጠናከር እንደሚተጉ ወ/ሮ ሀሲያ አሊ ገለጹበደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉ...
03/10/2026

ጠንካራ መሠረት የያዘውን የክልሉን የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ግኝኑነት ሥራዎችን በበለጠ ለማጠናከር እንደሚተጉ ወ/ሮ ሀሲያ አሊ ገለጹ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሆነው አዲስ የተሾሙት ወ/ሮ ሀሲያ አሊ ከቀድሞ የቢሮው ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ ጋር የሥራ ርክክብ አደረጉ።

የሥራ ርክክቡ የተካሄደው የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው 7ኛ ዙር መስራች ጉባኤ ወ/ሮ ሀሲያ አሊን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም አቶ የሺዋስ ዓለሙን ደግሞ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አድርጎ መሾማቸውን ተከትሎ ነው።

አቶ የሺዋስ ዓለሙ ክልሉ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት አምስት ዓመታት የክልሉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በኃላፊነት መርተዋል።

በስራ ርክክቡ ወቅት የቀድሞ የቢሮው ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ የቢሮውን አደረጃጀት፣ ስትራቴጂካዊ ግቦች፣ የመረጃ ሥርጭት አቅጣጫዎች፣ በሂደት ላይ ያሉ ተግባራትና ቀጣይ የሥራ እቅዶች አስመልክቶ ለአዲሷ ኃላፊ ገለጻ አድርገዋል።

አቶ የሺዋስ ዓለሙ በዚሁም እንደገለጹት፣ ቢሮው ከፌዴራል መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጀምሮ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በተቋማዊ ትስስርና በጋራ ዕቅድ የሚመራ መሆኑን ገልጸው የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ሥራዎችም በተደራጀ አሠራር ላይ መመሥረታቸውን ጠቅሰዋል።

ኃላፊው ለአዲሷ የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀሲያ አሊ በአዲሱ የሥራ ኃላፊነታቸው ስኬታማ የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በርክክቡ ወቅት አዲስ የተሾሙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀሲያ አሊ የመንግሥትና የፓርቲውን ተልዕኮ በብቃት በመወጣት በቢሮው የተገነባውን ጠንካራ መሠረት በማስቀጠል የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ሥራዎችን በበለጠ ለማጠናከር ትኩረት እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።

በተለይም ከቢሮው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የተሻለ የሥራ ትስስርና ተግባቦት በመፍጠር በቅንጅት መሥራት፣ ፈጠራንና ፍጥነትን ማዕከል ያደረገ የኮሙኒኬሽን አሠራር ማጠናከር እንዲሁም ፈጣን፣ ትክክለኛና ታማኝ የመንግሥት መረጃዎችን ለሕዝብ በወቅቱ ማድረስ ትኩረት የሚሰጡባቸው ዋና የሥራ አቅጣጫዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሥራ ርክክቡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ዶክተር መስፍን ወዳጆን ጨምሮ የቢሮ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል ሲል የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

የእንስሳት ዝርያ በማሻሻል የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ተባለ።በጊምቦ ወረዳ ተጋና ሾቻ ቀበሌዎች የ2019  የስንክሮናይዜሽን ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።የ...
02/10/2026

የእንስሳት ዝርያ በማሻሻል የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ተባለ።

በጊምቦ ወረዳ ተጋና ሾቻ ቀበሌዎች የ2019 የስንክሮናይዜሽን ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የወረዳው ግብርና ደን አካባቢ ጥብቃና ህብረት ስራ ጽ/ቤት የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ከስርዓተ ምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) በጀት ድጋፍ የስንክሮናይዜሽን ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል።

የእንስሳት ዝርያን በማሻሻል የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሲሉ የወረዳው ግብርና ደን አካባቢ ጥብቃና ህብረት ስራ ጽ/ቤት የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስመሩ ቦጋለ ተናግረዋል።

እንደ ጊምቦ ወረዳ በእንስሳት ዘርፍ በአራቱም ድቀላ 1ሺ 825 ላሞችን በማዳቀል 1ሺ 290 ጥጆችን ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

እንደ አጠቃላይ በስንክሮናይዜሽን 4 መቶ ላሞችን ለማዳቀል የታቀደ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በመጀመሪያው ዙር ዘመቻ 2 መቶ ላሞችን ለማዳቀል ቃቅዶ እየተሰራ እንደሆነም አቶ መስመሩ ቦጋለ አመላክተዋል።

አቶ መስመሩ አያይዘውም ከአራቱ የድቀላ አይነቶች መካከል አንዱ የሆነውንና ዛሬ ላይ ከተጀመረው የስንክሮናይዜሽን ዘመቻ ከ2 ቱም ቀበሌዎች 2 መቶ ላሞችን ለማዳቀል መታቀዱን አስታውቀዋል።

የፓርቲ ኢንሼቲቭ በሆነው በሌማት ትሩፋት ሥራ የተጋና ሾቻ ቀበሌ ውጤታማ በመሆኑ ይህ የስንክሮናይዜሽን ማስጀመሪያ ዘመቻ መደረጉንም አስታውቋል።

ስለ እንስሳቶች ድቀላ አስፈላጊነት እንዲሁም መወሰድ ስላለባቸው ጥንቃቀዎች ዙሪያ የወረዳው የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ የዝርያ ማሻሻያ ሥራ ሂደት ተወካይ ባለሙያ አቶ አለማየሁ ደፋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለአርሶ አደሩ ሰጥተዋልተ።

ይህ ዘመቻ ውጤታማ እንዲሆን የስርዓተ ምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም የሆነው (FSRP) በጀት በመመደብ ከወላይታ ዞን ዘር እንዲመጣ በማድረግ ለተባበረው ፕሮግራም፣ ለዞንና ለወረዳ መንግሥት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዘመቻው ወቅትም የወረዳው ግብርና ደን አካባቢ ጥብቃ ህብረት ስራ ጽ/ቤት የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ መስመሩ ቦጋለን ጨምሮ ሌሎች የዞንና የወረዳ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በአቤል ተስፋዬ

መስከረም 22/2019 ዓ.ም

የጊምቦ ወረዳ መን/ኮሚ/ጉዳ/ጽ/ቤት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/gimbogovtcommunicationaffairs
የቲክቶክ ቻናላችን
https://tiktok.com/
ይቀላቀሉ::

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ እንዳሻው ከበደ፣ የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ  ሆነው ተሹሟል።
02/10/2026

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ እንዳሻው ከበደ፣ የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹሟል።

Address

Adis Ababa
Gimbo

Telephone

+251905651100

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gimbo Woreda Communication Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share