02/10/2026
ሐዘን መግለጫ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 22/2019 ዓ.ም
ተማሪ ዳዊት ብርሃኑ ደስታ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውቲንግ እና ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ፣ የኢንፎርሜሽን ሳይንስ ት/ክፍል የ 4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረ ሲሆን፣ ተማሪውን በሞት በማጣታችን የተሰማን ጥልቅ ሐዘን እንገልጻለን።
ተማሪ ዳዊት ብርሃኑ በቀን 04/06/1994 ዓ.ም ተወልዶ ባደረበት የልብ ሕመም ምክንያት ሕክምና ላይ ቢቆይም በቀን 21/01/2019 ዓ.ም ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል::
ዳዊት በትምህርቱ የላቀ ችሎታ የነበረው፣ በመልካም ባህሪውና በጓደኞቹ ዘንድ ተወዳጅ ወጣት ነበር። በወጣትነቱ በድንገት ሕይወቱን ማጣቱ ለቤተሰቡ፣ ለጓደኞቹ፣ ለመምህራን እና ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ከባድ ሐዘን ነው::
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪ ዳዊት ብርሃኑ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና ጓደኞች መጽናናትን ይመኛል።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ