Haik ketema council office

Haik ketema council office ምክር ቤቶች የህዝብ ሉአላዊነት መገለጫ መድረኮች ናቸው

የሐይቅ ከተማ ምክር ቤት የ2019 በጀት አመትረቂቅ በጀት መርምሮ 435 ሚሊዮን 217 ብር አጸደቀ ።መስከረም 25/2019 ዓ.ምበጉባኤው የሐይቅ ከተማ ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት እቅድ...
07/10/2026

የሐይቅ ከተማ ምክር ቤት የ2019 በጀት አመትረቂቅ በጀት መርምሮ 435 ሚሊዮን 217 ብር አጸደቀ ።
መስከረም 25/2019 ዓ.ም
በጉባኤው የሐይቅ ከተማ ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት እቅድ፣ የአስፈፃሚዉ እቅድ እና የማስፈጸሚያ ረቂቅ በጀት ቀርቦ በምክር ቤቱ ጸድቋል ፡፡
የ2019 በጀት ዓመት እቅዱ የከተማዋን አሻጋሪ እድገት ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ከማሳደግ ጀምሮ የመሠረተ ልማት፣ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ በገቢ ፣በገበያ ማረጋጋት፣የከተማ ውበትና ጽዳት እንዲሁም ሌሎች የልማት ዘርፎችን በተቀናጀ መልኩ ለማስኬድ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ መሆኑ በምክር ቤት አባሉ ተመላክቷል።
የሐይቅ ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ አቶ ከድር መሃመድ ባለፈው በጀት አመት የ5 አመት አሻጋሪ እቅድ ታቅዶ ወደ ስራ በመግባት እጅግ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ መሆኑን አንስተው ፤ በተያዘው በጀት አመትም ሰፊና አሳታፊ የሆኑ የከተማዋን እድገት ሊያረጋግጡ የሚችሉ የልማት ስራዎች ለመስራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
የታቀዱትን የስራ አቅዶች በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም ገቢ መሰብሰብ ዋነኛው ተግባር በመሆኑ ለተፈጻሚነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በርብረብና በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ሲሉ አቶ ከድር አክለዋል።
አያይዘውም ከተማን ለማሳደግ የሚያስችል ገቢ ለማመንጨት የሀብት ፈጠራ ስራ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ በመሆኑ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር በማሸጋገርና ባለሀብቶችን በመሳብ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንትን በከፍተኛ ትኩረት አጠናክሮ መስራትና የከተማውን እድገት ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።
አቶ ከድር በማጠቃለያቸው የ2019 በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅዱ በምክር ቤቱ በጥልቀት በመመርመር ተግባራዊ ሲሆን፣ የሐይቅ ከተማን የበለጠ የተሻለች፣ የተደራጀችና ለነዋሪዎቿ የተሻለ የኑሮ አካባቢ የምትሆንበትን የልማት መሠረት ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም በመደበኛ በጀት ለስራ ማስኬጃ 34 ሚሊዮን 836ሺህ 598ብር እና ለደመወዝ 117ሚሊዮን 573ሺህ 606 ብር በድምሩ 152ሚሊዮን 410ሺህ 204ብር እንዲሁም ለከተማ አስተዳደሩ የልማት ስራዎች ማስፈጸሚያ የሚሆን የካፒታል በጀት 282ሚሊዮን 590 ሺህ 013ብር ሲሆን ምክር ቤቱ የቀረበውን ረቂቅ በጀት መርምሮ 435ሚሊዮን 217ብር በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

01/10/2026

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!

‎አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ኾነው በድጋሜ ተሾሙ።

01/10/2026

አቶ አማረ ሰጤ የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ኾነው ተመረጡ።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን መሥራች ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ አቶ አማረ ሰጤን በድጋሜ የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።

01/10/2026

አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሰየሙ
*************

7ተኛ ዙር 1ኛ ዓመት መሥራች እና 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ያለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሰይሟል፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ

01/10/2026
01/10/2026
28/09/2026
28/09/2026

እንኳን ለደመራና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ/የተከበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋየ/

መስከረም 16/01/2019 ዓ.ም የአማራ ብሄራዊ ክልል ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋየ ለየደመራናመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

አፈጉባኤዋ በመልዕክታቸው :-
መስቀል የፍቅር፣የይቅርታ፣የአንድነት ምልክት ነው ። መስቀል የጥል ግድግዳ የተሰበረበትና ጥላቻ በፍቅር መለያየት በአንድነት ተስፋ ማጣት በዘላቂ ድል የተተካበት በዓል ነው።
መስቀልን ለማግኘት የተደረገው ጥረት የሚያስተምረን አላማን ለማሳካት ያለመታከት መጣርን፣በትጋት መስራትንና በፅናት መከተልን ነው። ውጤታማነት የድካምናየፅናት ውጤት ናት ።

ስለሆነም መላው ህዝባችን ደመራውን በፍቅር፣ ውጤታማነትን በጥረት በማብራት መስቀል የደመራ ብርሃን ብቻ ሳይሆን፣ በልባችን የምናበራው የተስፋና የሰላም ብርሃን መሆን አለበት።
በአሉን ስናከብር እንደተለመደሁ ሁሉ የተቸገሩ ወንድም እህቶችን በማገዝ በመደገፍ በአብሮነት በደስታ እንድታሳልፍ እመኛለሁ።
በድጋሜ መልካም በዓል
የምክር ቤታችን ተጨማሪ መረጃዎችን ከታች በተቀመጡት ሊንኮች ይከታተሉ
Telegram: - https://t.me/anrscouncil
Tiktok :- http://www.tiktok.com/anrscouncilofficial
Youtube :- www.youtube.com/anrscouncilofficial
X :- www.x.com/mikerbet123

ቀን 14/01/2019የሀይቅ ከተማ ምክር ቤት 2019 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ አካሄደጽ/ ቤቱ 2018 በጀት አመት እቅድን ከጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ጋር ከገመገመ በኋላ የ2019 በጀት አመት የ...
24/09/2026

ቀን 14/01/2019
የሀይቅ ከተማ ምክር ቤት 2019 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ አካሄደ
ጽ/ ቤቱ 2018 በጀት አመት እቅድን ከጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ጋር ከገመገመ በኋላ የ2019 በጀት አመት የመንግስትና የፓርቲ እቅድ ትውውቅ አድርጓል፤፤ የጽ/ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ግርማ ሞገስ በእቅድ ትውውቁ ላይ እንደገለጹት በበጀት አመቱ የታቀዱ ተግባራትን በስኬት ለመፈፀም ሀሉም ባለሙያ በጊዜ የለንም መንፈስ እና በእውቀት ላይ በመመስረት ሊሰራና የተሻለ አፈፃፀም ሊያስመዘግብ ይገባል ብለዋል፡፡

Address

Ethiopia Amhara Region
Haik

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haik ketema council office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share