Harari public procurement and property disposal service office

Harari public procurement and property disposal service office

Share

Vision :To be an outstanding and preferred procurement and property disposal rendering service in Et

Main objectives of the office
The Public Procurement and Property Disposal Service office have the following objectives:
 To enable the timely supply of goods and services, which are commonly used by public bodies as well as goods and services which have national and regional strategic significance in the desired quality and at prices attributable to economic of scale resulting from bulk purchas

25/05/2026

የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ፅ/ቤት የ2018 በጀት አመት የአረፋ በኣልን ምክኒያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ሰራተኞቹ የማእድ ማጋራት ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ
ሰራተኞቹ ድጋፉን በወሰዱበት ወቅት እንደገለፁት ድጋፉ የወቅቱን የኑሮ ወድነት ችግርን የቀረፈ ብቻም ሳይሆን የስራ ተነሳሽነትን /ምርታማነትን እንደሚጨምር በማንሳት ተቋሟቸውን ከልባቸው አመስግነዋል
ዘጋቢ
የተቋሙ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር
17/9/2018

Photos from Harari public procurement and property disposal service office's post 18/05/2026

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት የበጀት እና የፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በዛሬው እለት የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ፅ/ቤትን የ9 ወር የስራ አፈፃፀምን እና የአገልግሎት አሰጣጥ/ የመልካም አሰተዳደር አፈፃፀምን መገምገማቸው ተገለፀ
የተከበሩ የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በአካል በተቋሙ በመገኘት የስራ አፈፃፀሙን የገመገሙ ሲሆን የተቋሙ ኃላፊ አቶ አብዱልባሲጥ አቡበከር የተቋሙን የ 9 ወር አፈፃፀም ሪፖርት እና የመልካም አስተዳደር ሪፖርት አቅርበዋል
የበጀት እና የፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ ወ/ሮ ፈትሂያ ሳኒ በበኩላቸው በቀረበው ሪፖርት ለይ አባለቱ ጥያቄና ሀሳብ እንዲያነሱ እድል በመሰጠት ያወያዩ ሲሆን የተከበሩ እና ሁሉም የቋሚ ኮሚቴ አባላት በበኩላቸው ጠንከር ያለ የድጋፍ እና የትችት ጥያቄዎችና ሀሳቦችን በማንሳት መልስ እና ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ተደርገዋል
በተለይም የተከበሩ ወ/ሮ አሚና አብዱከሪም ለተቋሙ ግብኣት የሚሆን ጠለቅ ያለ እና ሰፋ ያለ ጉዳዮችን አቅርበዋል
የተቃሙ ኃላፊ በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ ውስጥ አባላቱን በማመስገን አብዛኛውን እንደ ግብኣት የቀረቡልንን ተቀብለን የምን ተገብረው ነው ብለዋል
የተከበሩ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ፈትሂያ ሳኒ በሰጡት ማጠቃለያ እና አቅጣጫ መሠረት የተቋሙን የ9ወር አፈፃፀም ከ 90 ፐርሰንት በላይ መሆኑን : የተቋሙ የህፃናት ማቆያ አገልግሎት መጀመሩን እና የማኔጅመንት አባላት የኮርኒያ ተዋፅኦ ሀምሳ ሀምሳ ፐርሰንት መሆኑን በአድናቆት አንስተዋል
በሌላ በኩል በየቦታው እና በየጋራዡ ለብልሽት እና ኢኮኖሚክ ኪሳራ በመዳረግ ላይ የሚገኙትን የመንግስት ንብረቶችን በሽያጭ ጨረታ በማስወገድ የመንግስትን ገቢን ለማሳደግ ከዚህ የበለጠ ልትሰሩ ይገባል በሚል አፅንኦት ከሰጡ ቡኃላ አጠናቀዋል
ዘጋቢ
የተቋሙ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር
10/9/2018

14/05/2026

https://www.facebook.com/share/p/1CozxQQRob/

በጽንፈኞች የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚደፈርስ ሰላምም ሆነ የሚሸረሸር የህዝቦች አብሮነት የለም!- የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

ጽንፈኞች በሚነዙት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚደፈርስ ሰላምም ሆነ የሚሸረሸር የህዝቦች አብሮነት እንደማይኖር ሊገነዘቡት ይገባል ሲል የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገለፀ።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ እንዳሉት የክልሉ መንግስት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ፍህሃዊነትን ያረጋገጡ በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

በተለይም በልማቱ የተገኙ ስኬቶች ህዝቡ ለዘመናት ሲያነሳቸው የቆዩ ጥያቄዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ህዝቡም የክልሉ መንግስት እያስመዘገባቸው የሚገኙ ስኬቶች ራሱ እየመሰከረ ባለበት ወቅት አንዳንዳ ''እኛ እናውቅልሃለን'' የሚሉ ጽንፈኞች የሀሰት ፕሮፖጋንዳቸው በመንዛት ለማደናገር እየተውተረተሩ ይገኛሉ ብለዋል።

መቃወም እንጀራቸው ያደረጉ እነኚህ ጽንፈኞች የህዝብን ሳይሆን የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚፈልጉ አካላት መሆናቸው ህዝቡ በሚገባ እንደተገነዘበ ሊያውቁት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ከእነዚህ አካላት ምኞትም በተዋለዱና በተጋመዱ ህዝቦች መካከል ቅራኔ እንዲፈጠርና ሰላም እንዲደፈርስ በማድረግ አላማቸውን ማሳካት መሆኑ መረዳት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ስለሆነም ለህዝብ ጥቅም የቆሙ በማስመሰል በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ የጥላቻ እና ከእውነት የራቁ መረጃዎችን እያሰራጩ የሚገኙ አካላትን አላማ መገንዘብ ለህግ እንዲቀርቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

Photos from Harari public procurement and property disposal service office's post 14/05/2026

የሐረሪ ክልል የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ፅ/ቤት የ 2018 በጀት አመት የ 9 ወር አፈፃፀም ግምገማ ማካሄዳቸው ተገለፀ
የተቋሙን የ 2018 በጀት አመት የ 9 ወር አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ዘከሪያስ ዩሱፍ ሲሆኑ ተቋሙ በበጀት አመቱ በእያንዳንዱ የስራ ሂደት የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡን አቅርበዋል
በተለይም ለሁሉም የክልሉ መንግስት መስራቤቶች ጊዜውን የጠበቀ የግዥ ሂደት በመፈፀሞ አቅርቦታቸውን አጠናቆ እስከ ክፍያ ሰርአት መከታተል ድረስ ከእቅድ በላይ መሰራቱን በተጨባጭ ዝርዝር ዳታ ና መረጃ አቅርበዋል
አክለውም በክልሉ የመንግስት ተቋሞች እና በወረዳዎች ውስጥ ያለ አገልግሎት ተቀምጠው ለብልሽት እና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እየተዳረጉ የሚገኙትን የመንግስት ንብረቶችን በሽያጭ ጨረታ በማስወገድ አንፃር የተሻለ ውጤት መመዝገቡን በንፅፅር በማሳየት አቅርበዋል
ለተገኘው ውጤትም ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞቾ እና አመራሮች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል በማለት አመስግነዋል
ሰራተኞች በበኩላቸው ባደረጉት ውይይት እና ግምገማ መሰረት አሁን የታየውን ጥንካሬዎች በማስቀጠል እና ድክመቶችን በማረም ወደፊት ከዚህ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅብናል በማለት ከመግባባት ላይ ተደርሰዋል
በመጨረሻም ከሰራተኞቹ ለተነሳው ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ከመድረክ ላይ ተመልሶ ማጠቃለያ ከተሰጠ ቡኃላ ተጠናቀቀ
ዘጋቢ
የተቋሙ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር

Photos from Harari public procurement and property disposal service office's post 14/05/2026

የሐረሪ ክልል የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ጽ/ቤት በዛሬው እለት በፀደቀው የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም ፖሊሲ ዙሪያ ለ ሰራተኞቹ ስልጠና መስጠቱ ተገለፀ
የተሰጡት ስልጠናዎች በ አራት/4 ሰነዶች ላይ ሲሆን እነሱም :-
1/ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም ፖሊሲ
2/ የመንግስት ሰራተኞች ብቃት ምዘና ሰርአት አመራር
3/ ነፃ ገለልተኛ እና አካታች የሰራተኞች ሰምሪት
4/ የስራ አፈፃፀም አመራር ለውጦች እና እድገቶች በሚሉ ሰነዶች ላይ ነበር
በስልጠናው መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ኃላፊ ተወካይ እንደገለፁት የፀደቀው የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም ፖሊሲው ከዚህ በፊት ከነበረው ምን ለየት ያደርገዋል ?
በዋናነት ምን አላማ ሊያሳካ ነው ?
ምን አይነት ችግሮችን ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል ?
የትግበራ አሰገዳጅነት አስመልክቶስ በመንግስት የተቀመጠው አቅጣጫዎች ምን ምን ድናቸው ? የሚሉትን ዝርዝር መረጃዎች እና ተግባራትን ከስልጠና ሰነዶቹ ማግኘት እንደሚቻል አንስተው የስልጠናውን መድረክ በንግግር ከፍተዋል
በመቀጠል አቶ ዩሱፍ አብደላ የስልጠና ሰነዶቹን አቅርበው ሰልጣኞቹ ሰፊ ውይይት እንዲያረጉበት ተደርገዋል
ሰልጣኞቹ በበኩላቸው ሰፊ ሀሳብ እና ጥያቄዎችን በማንሳት ተወያይተዋል
በተለይም ከዚህ በፊት ቡዙ የሪፎርም ሰራዎች ከጥናት በዘለለ ሙሉ ለሙሉ ሲተገበሩ አይታወቅም ነበር አሁን ግን መንግስታችን ባሳየው የትግበራ ቆራጥነት በፖሊሲ ደረጃ ፀድቆ ወደ ትግበራ መግባት መቻል የሚደነቅ ነው ሲሉ አንስተዋል አክለውም ለትግበራው ወጤታማነት መረባረብ ይጠበቅብናል በማለት አንስተዋል
በመጨረሻም አቶ ዚያድ አርጋው እና አቶ ዩሱፍ አብደላ ከሰራተኞቹ ለተነሳው ጥያቄዎች እና ሐሳቦች በቂ መልስ እና ማብራሪያ ከ ማቅረብ በተጨማሪ አራቱም የስልጠና ሰነዶች በተቋሙ የቴሌግራም ፔጅ ላይ መጫኑን ነግረው ሁሉም ሰራተኛ ደጋግሞ በማንበብ የበለጠ መረዳት እንደሚችል አንስተው ከመግባባት ላይ ከተደረሰ ቡኃላ ስልጠናው ተጠናቀቀ
ዘጋቢ
የተቋሙ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር
6/9/2018

Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

http://hppdso.gov.et/index, https://t.me/hppds2, http://hppdso.gov.et/

Address


Harar