የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር office of Harari Auditor General

የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር  office of Harari Auditor General

Share

ስለ ኦዲት በቂ መረጃና እውቀት ለማግኘት ፔጃችንን LIKE እና FOLLOW ያድርጉ

Photos from የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር  office of Harari Auditor General's post 13/01/2026

የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከፌደራል ዋና ኦዲተር እና አዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ጋር የልምድ ልውውጥና የሥራ ዝግጅት አደረጉ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖


​የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የኦዲት አሠራሩን ለማዘመንና ጥራቱን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ከፌዴራል ዋና ኦዲተር እና ከአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን የልምድ ልውውጥና የሥራ ዝግጅት መርሃ-ግብሮችን እያከናወነ ይገኛል።


የሀረሪ ክልል የተገዥነት ኦዲት (Compliance Audit) ዳይሬክተር እና ኦዲተሮች የፌደራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወይዘሮ መሰረት ዳምጤ ጋር በአሠራር ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም በክልሉ የተገዥነት ኦዲት ሥራን ለማስጀመር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በዝርዝር መክረዋል። ለሥራው ስኬታማነት አጋዥ የሚሆኑ የተለያዩ መመሪያዎች (Manuals) እና የሥራ ማስፈጸሚያ ቅጾችንም ከፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር ኦዲተሮች ተረክበዋል።

በተጨማሪ ​የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር ተየገዢ ኦዲት ዳይሬክተር እና ኦዲተሮች አዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በመገኘት በተለይም በኮንስትራክሽን ግዢ ኦዲት ዙሪያ ያለውን አሠራር ተመልክቷል። በዚህም ዘርፍ ያለውን ምርጥ ተሞክሮ በመቅሰም በክልላችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት አድርጓል።

​አሁን የተከናወኑ የልምድ ልውውጦች የክልላችንን የኦዲት አሠራር በዕውቀትና በቴክኖሎጂ በመደገፍ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው።

ጥር 5/2018

Photos from የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር  office of Harari Auditor General's post 06/01/2026

የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለሁሉም ሰራተኞች የ MBO አሰራር ስልጠና ሰጠ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዛሬ ታህሳስ 28/2018 ለመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የMBO ስልጠና ሰጠ ። የክልሉ ዋና ኦዲተር አቶ አብዱማሊክ በከር ም/ዋና ኦዲተር አቶ አብዱልሃኪም በተገኙበት ሁሉም ዳይሬክተሮች፣ ኦዲተሮች እና የመስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በሙሉ ስልጠናውን ወስደዋል።

በአዲሱ የምዘና አሰራር (MBO) ዙሪያ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በቂ ክህሎት እንዳገኙ በስልጠናው መድረክ ላይ ባደረጉት ተሳትፎ ገልፀው ሲስተሙን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንደሚያስገቡ ገልፀዋል።

22/09/2025

የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የድጋፍ ሰልፍ
⇨ የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት
⇨ መስከረም 12/2018

Photos from የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር  office of Harari Auditor General's post 22/09/2025

የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ ዛሬ መስከረም 12/2018 በሀረሪ ክልል በነበረው የድጋፍ ሰልፍ የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የደስታ ድጋፍ ሰልፍ ተሳትፏል።

Photos from የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር  office of Harari Auditor General's post 14/05/2025

የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በክልሉ ለሚገኙ የውስጥ ኦዲት ባለሞያዎች እና ለ/ግ/ፍ/ን /ዳይሬክተሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና
መስጠት ጀመረ

የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በክልሉ ለሚገኙ የውስጥ ኦዲት ባለሞያዎች እና ለ/ግ/ፍ/ን /ዳይሬክተሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እና
የጋራ የውይይት መድርክ በዛሬው እለት አስጀመረ ።

በክልሉ ለሚገኙ ለ49 ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች የግ/ፋ/ን/አስተዳደር ዳይሬክተሮችና ለወስጥ ኦዲተር ባለሞያዎች በመንግስት የፋይናንስ አሰተዳደር እና የውስጥ ቁጥጥር ስርአትን ለማሻሻል በሴክተር መ/ቤቶች በተደጋጋሚ የሚታዩ ግኝቶች ላይ ያተኮረ የጋራ የመወያያ መድረክ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ ግንቦት 6/2017 በሐረር ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።

ይህ በክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት አዘጋጅነት እየታካሄደ የሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የውይይት መድረክ ለ ሁለት ቀን የሚቆይ ይሆናል።

22/04/2025



የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር office of Harari Auditor General
Harari Auditor General

Photos from የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር  office of Harari Auditor General's post 22/04/2025

ለሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር የፋይናንሻል ኦዲተሮች የኮንስትራክሽን ኦዲት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ለሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የፋይናንሻል ኦዲተሮች በሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ለ6 ቀናት ሚያዝያ 13–18/2017 ድረስ የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

Photos from የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር  office of Harari Auditor General's post 16/04/2025

ለሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት compliance Auditor (ሕጋዊነት ኦዲተሮች) የአቅም ግንባታ ለ 4ቀን ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

እንደሚታወቀው የcompliance audit (ሕጋዊነት ኦዲት) በአለም አቀፍ ደረጃ የኦዲት አሰራር አንዱ ሲሆን ይህ አሰራር በሐገራችን ማለትም በሐገር አቀፍ ደረጃ ያልተጀመረ ነው።

የክልላችን ዋና ኦዲተር መ/ቤት በአዋጅ ሲቋቋም ተቆጥረው ከተሰጡት የኦዲት አሰራሮች አንዱ በመሆኑ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ ክልላችን ይህን ስራ በይፋ ጀምሯል።

ስለሆነም ለሕጋዊነት ኦዲተሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ።

Photos from የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር  office of Harari Auditor General's post 03/04/2025

ሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተረከበውን የጁገል እድሳት ሳይት ጠረጋ ጀመረ ።

Photos from የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር  office of Harari Auditor General's post 19/02/2025

የሐረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሰራተኞች በወቅታዊና ሃገራዊ ጉዳይ ተወያዩ

የሐረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሰራተኞች በወቅታዊ እና ሐገራዊ ጉዳይ ላይ በመወያየት የጋራ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል።

ይህም ባሳለፍነው ወር የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛው ጉባኤ ያስተላለፈውን ውሳኔዎች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚመለከት በክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ አሪፍ መሐመድ አዱስ ሰፊ ገለፃ ቀርቧል ።

የብልጽግና ፓርቲ በጉባኤው 10 አቅጣጫዎች ያስቀመጠ ሲሆን ከነዚህም መካከል ሃገራዊ አንድነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ የብሔራዊነት ገዢ ትርክት ግንባታ ስራዎችን እንደሚሰራ ፣ ውጤታማ የሰላምና ፀጥታ ግንባታ ፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት ማረጋገጥ እና ማህበራዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ የሚችሉ ስራዎችን ፣ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎችን ፣ ጠንካራ የሃገረ መንግሥት ግንባታ እነዚህ ከተቀመጡት አቅጣጫዎች ዋና ዋና መሆኑን ከመድረኩ በስፋት ገለፃ ተደርጓል ።

በቀረበው ሰነድ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ፓርቲው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ፓርቲው የጀመረውን ሐገራዊ የለውጥ ጉዞ የሚያፋጥኑ እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሰረታዊ አቅጣጫዎች መሆናቸውን ተሳታፊዎች በተለያዩ መልኩ ገልፀዋል።

በውይይት መድረኩ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አቶ አሪፍ መሐመድ አዱስ የክልሉ ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አብዱማሊክ በከር ጨምሮ ሌላ የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዳይሬክተሮች ፣ ሰራተኞች ተገኝተዋል።

⇨ የካቲት 12/2017

24/01/2025

ዜና ኦዲት

የዜና ምንጭ ☞ HTV
የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር office of Harari Auditor General

23/01/2025

ጥራቱን የጠበቀ የኦዲት ስራና ወቅታዊ የኦዲት ሪፖርት ተጠያቂነትን ያጎለብታሉ።

Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Aratenga New Road Front Of TTI College
Harar