ግንቦት 24 የተካሄደው 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በክልላችን ፍትሃዊ ዲሞክራሲ እንዲሁም ያለ አንዳች ችግር በመጠናቀቁ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል ። የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች
Harari Region Prosperity Party - ብልፅግና
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Harari Region Prosperity Party - ብልፅግና, Political organisation, Bote Street, Harar.
ግንቦት 24 አንደ ሀረሪ ክልል ሲካሄድ በነበረው ምርጫ ሂደት የህዝቡ ተሳትፎ አስደማሚ ነበር፣ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተሳተፉበት ነበር።
"የሕዝብን ድምፅ በፀጋ ለመቀበልና ለማክበር ዝግጁ ነኝ" ፦
አቶ ጀማል አባገሮ
ለሀረሪ ክልል ምክር ቤት የግል እጩ ተወዳዳሪው
Filannoon biyyoolessaa marsaa 7ffaa caamsaa 24 geggeeffame karaa dimokiraasii, haqaafi nagaa taheen geggeeffamee xumuramuu isaatti gammachuu guddaa qabna.
Gara fuulduraattis, Kan dorgomee mo'ame dimokiraasii waan taheef karaa nagaan dhimma guddina biyyaa irratti Mootummaa waliin hiriiree hojjechuu qaba:
Jiraattota Naannoo Hararii
ግንቦት 24 ዚትሜሓራ ባድ ሑቁፍ ሚልሓ ሰላሚያ፣ አሓድ አምኒ ጪንቂ ዋ አሓድ ኡሱእ ጤኖት ቢላይ ዲሞክራሲያ ሐቅዚናው መትናፈእቤ ኒኸሻዛና ፓርቲው ዚማላሕናቤው ኢንታ።
ሀረሪ ሑስኒ ነባሪያች
03/06/2026
በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማጎልበት የተሠሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው - የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን
የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ እና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የቡድኑን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያ ግምገማ ውጤትን በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ውቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዴሞክራሲን ለማጎልበት የሠራውን ሥራ እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።
አጠቃላይ የምርጫው ሂደትም የኢትዮጵያን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች ማዕቀፍን በተከተለ መልኩ መካሄዱን በግምገማው ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።
ከቅድመ ምርጫው ጀምሮ የነበረው ሂደት አበረታች እንደነበር የገለጹት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የአፍሪካ ኅብረት ከምርጫው ዋዜማ አንሥቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።
የመራጮች ትምህርት አሰጣጥ በተመለከተም ሕዝቡ እንዴት መምረጥ እንዳለበት ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኝ መደረጉን እና በምርጫው ዕለት የነበረው የተቀናጀ መናበብ ለመራጮች ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን አስረድተዋል።
በምርጫው ሂደት ጥቅም ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ በተለይም ለወጣቶች የፈጠረው ዕድል ከፍተኛ መሆኑን የታዛቢ ቡድኑ መሪ በመግለጫቸው አብራርተዋል።
የድምፅ መስጫ ሰዓት መራዘሙ ለመራጮች ተጨማሪ ዕድል መፍጠሩን፣ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ቅድሚያ መሰጠቱ የዜጎችን ተሳትፎ በእጅጉ ማነቃቃቱንም ጠቁመዋል።
በመላው ኢትዮጵያ የምርጫ አስፈፃሚዎች እና የፀጥታ አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጥሩ ሁኔታ መወጣታቸውን፣ የመገናኛ ብዙኃንም በተመሳሳይ በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት ሥራቸውን ማከናወናቸውን አድንቀዋል።
ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫው ያሳየው ተሳትፎ እና ትልቁን ኃላፊነቱን በጀግንነት መወጣቱ እጅግ የሚያስመሰግን መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል።
03/06/2026
ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ መርጣለች!
ሀገራችን ባከናወነችው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ረዣዥም የመራጮች ሰልፍ መስተዋሉ፣ ዜጎች በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ስለመሆናቸው ጉልህ ማሳያ ነው።
የዕድሜ መግፋት ፣ የጤና ሁኔታ መታወክ፣ አራስነት፣ ከቤት መቆየትን የግድ ያለው አሰገዳጅ ክስተት ሳይበግራቸው ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው ይበጀኛል ያሉትን መርጠዋል።
አንድ ድምፅ ዋጋ እንዳለው በመረዳት ከሌሊት እስከ ሌሊት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
በምርጫው ዕለት የታዩ ረዣዥም የመራጮች ሰልፎች የሕዝብ የፖለቲካ ፍላጎት እና የዴሞክራሲ ተሳትፎ መጉላትን የሚያሳዩ ናቸው።
03/06/2026
የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ
የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡
ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡
የሐረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ዙሪያ የሰጠው መግለጫ ።
02/06/2026
የጋራ ምክር ቤቱ የሕዝቡን ውሳኔ እና ድምፅ ያከብራል፦ የሐረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
የሐረሪ ክልል የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ምክር ቤቱ በመግለጫው፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ላይ የታዩ አዎንታዊ ጅምሮችን ይበልጥ በማጠናከር የምርጫውን ሰላማዊነት፣ ዲሞክራሲያዊነት፣ ነፃና በሕዝብ ዘንድ ተዓማኒነቱን ማጠናከር እንደሚገባ አንስቷል።
በአንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኩል የቀረቡ ቅሬታዎችን፣ የአፈጻጸም ክፍተቶችን እና ተግዳሮቶችን በጥንቃቄ በምርጫ ዴስክ በኩል ለመፍታት ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን የጠቀሰው ምክር ቤቱ፣ በአሁኑ ወቅትም ቅሬታዎችን በሕጋዊ እና በተቋማዊ አግባብ ለመፍታት ተገቢው ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁሟል።
የጋራ ምክር ቤቱ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዝቡን ውሳኔ እና ድምፅ እንዲያከብሩ እና ደጋፊዎቻቸውንም ወደ ሰላም፣ መከባበር እና ሕጋዊ አሠራር እንዲመሩ እንዲሁም ማንኛውንም ዓይነት ልዩነት በውይይትና በሕግ ማዕቀፍ ብቻ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል።
የምርጫው ውጤት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ መሠረት ተረጋግጦ እስከሚጠናቀቅና ይፋ እስከሚደረግ ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትዕግሥት እና በኃላፊነት ስሜት መጠባበቅ እንዳለባቸውም ተገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ ከምርጫ በኋላ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የምክክር እና የመግባባት ባህል ይበልጥ እንዲጠናከር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ምክር ቤቱ አረጋግጧል።
የጋራ ምክር ቤቱ በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ላይ በንቃት ለተሳተፉ ዜጎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የምርጫ አስተዳደር አካላት፣ የፀጥታ ተቋማት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና የሚዲያ ተቋማት ለተወጡት ሀገራዊ ከፍ ያለ ክብር እንደሚሰጥ በመግለጫው አስታውቋል።
02/06/2026
Itoophiyaan Injifattee Jirti!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Harar
