09/05/2026
የአብዱልሀፊዝ ከሊፋ ወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከል ጤና ክፍል ለወጣቶች የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል!!
ማዕከሉ ለተጠቃሚዎቹ እያደረገ ያለው ይህ ድንቅ እንቅስቃሴ ለወጣቶቻችን ትልቅ ፋይዳ አለው ስሆን የማማከር፣ የግንዛቤ እና የተለያዩ የጤና ምርመራዎችን በማዕከሉ ያገኛሉ።
#ጤና #ወጣት #ወጣትማዕከል
03/05/2026
በሀረር ከተማ የ5 ኪሎሜትር የምሽት የኮሪደር ሩጫ በድምቀት ተካሄደ!
በሀረር ከተማ የተካሄደው ይህ ልዩ የ5 ኪሎሜትር የምሽት የኮሪደር ሩጫ፣ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት በልዩ ክብር ተካሂዷል።
“ለብልፅግና እሮጣለሁ፤ ድምፄንም እሰጣለሁ!” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ውድድር፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የመጡ ተሳታፊዎችን በአንድነት አካትቶ ተካሂዷል።
ይህ ውድድር የሀረርን አዲስ ገፅታ ለአለም ለማስተዋወቅ እና 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላምና በስኬት እንዲካሄድ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ ታሪካዊ የሩጫ ውድድር፣ የሀረሪ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በንቁ ተሳትፎ ተገኝተው የምሽቱን አድምቀውታል ።
ዝግጅቱም በሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።