04/06/2026
Harari Urban Development and Construction Bureau
ይህ ገጽ የሐረሪ ከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን ቢሮ ፌስ ቡክ ?
የ መ/ቤቱ ተግባርና ስልጣን
• ያመለካከት ለውጥ በማምጣት የለውጥሰራዊት በመገንባትና የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የዘርፉን ተልኮ ያሳካል፤
• የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋሞች ልማት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
• የጥቃቅንና አነስተኛኢንተርፕራይዞች ልትበዘርፉ ስትራቴጂ መሰረት ይመራል እንቅስቃሴዎችን ያስተባብራል በተገቢዉ ሁኔታ መተግበሩን ያረጋገረጣል
•ስለመሬት ልማትና አስተደደር በዘር ስትራቴጂ መሰረት ይመራል እንቅስቃሴዎችን ያሥተባብራል በተገቢዉ ሁኔታ መከበሩን ያረጋግጣል፡፡
•ግልጽና ፍታዊ የመሬት አስተዳደር በክልሉ እነዲከበር ያደርጋል፤
• የከተማውን መሬትና መሬት ነክ ንብረት አስተዳደር መረጃ ያጠናቅራል፤ ያደራጃል፤ያሰራ
04/06/2026
04/06/2026
02/06/2026
02/06/2026
ከሀረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
የሀረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከ7ኛው ክልላዊና ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥቷል።
ምክር ቤቱ በመግለጫውም በ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫው ሂደት ወቅት የታዩ አዎንታዊ ጅምሮችን ይበልጥ በማጠናከር የምርጫውን ሰላማዊነት፣ ዲሞክራሲያዊነት፣ ነፃና በሕዝብ ዘንድ ታማኒነቱን ማጠናከር ይገባል ብሏል።
የጋራ ምክር ቤቱ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዝቡን ውሳኔ እና ድምፅ እንዲያከብሩ፣ ደጋፊዎቻቸውን ወደ ሰላም፣ መከባብር እና ሕጋዊ አሠራር እንዲመሩ እና ማንኛውንም ልዩነት በውይይት እና በሕግ ማዕቀፍ እንዲፈቱ ጥሪውን አቅርቧል።
የምርጫው ውጤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ መሠረት ተረጋግጦ እስከሚገለፅ ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትዕግሥትና በኃላፊነት ስሜት እንዲቀሳቀሱ ጠይቋል።
ከምርጫ በኋላም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የምክክር እና የመግባባት ባህል እንዲጠናከር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በጋራ እንደሚሰራ ነው ያስታወቀው።
ማንኛውም ቅሬታ በሕጋዊ መንገድ ብቻ መፍታት እና በሰላምና በብሔራዊ ጥቅቅም ጉዳይ ትብብርን መሠረት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተመላክቷል።
የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት እና በዴሞክራሲያዊ ሂደት የመፍታት ባሕላችንን ማጠናከር እና የትብብር እና የፉክክር ሚዛንን በማስጠበቅ የመደብለ ፓርቲ የዲሞክራሲ ባሕልን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን የጋራ ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።
02/06/2026
ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ኢትዮጵያውያን በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመምረጥ ኢትዮጵያን አሸናፊ አድርገዋል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
ጠቅላላ ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁንም አመልክቷል።
አገልግሎቱ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! ሲል ገልጿል።
አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመላከተው፣ ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችውን ሁሉ በፈለገችው ጊዜና ሁኔታ የምታገኝ ሀገር መሆኗንና ለሀገራቸው የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ እንደምትኮራ ገልጿል።
ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ ከመሻቷ በላይ እንደተሳካላትና ዛሬም የተደገመው ይኸው እንደሆነ አብራርቷል።
ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን ለመምረጥ እንዲሁም ሕገ-መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ለማስያዝ እንደምትሻ የጠቀሰው መግለጫው፤ ለዚህ ደግሞ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም ማስፈለጉን አስታውቋል።
ለዚህ አገራዊ ጥሪ በምላሹ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው ቀኑን ሲጠባበቁ መቆየታቸውንና የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበልም በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ መዋላቸውን አገልግሎቱ ገልጿል።
መራጮች ሌሊቱንም ጭምር አጋምሰው ድምፅ የሰጡ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈው ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫ ያደርገዋል ብሏል።
ምርጫው እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተው ያልቆፈሩት ጉድጓድና ያልደረደሩት እንቅፋት እንዳልነበረ የጠቀሰው መግለጫው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር ባለመኖሩ ሂደቱ በስኬት መጠናቀቁንና ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ ማሸነፏን አረጋግጧል።
የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃው ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ የላቀ ምስጋና ታቀርባለች ሲል አገልግሎቱ አስታውቋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Harar
