31/05/2026
🚶♂️🌿 መንገዶቻችን ለሰዎች፤ ጤናማ ማህበረሰብና ዘላቂ የመንገድ ደህንነት መሠረት!
══════
በዘመናዊ ከተሞች ውስጥ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ብቻ ሳይሆን ለሰዎች የጤና፣ የመዝናኛ፣ የማህበራዊ ትስስርና የአካባቢ ጥበቃ ማዕከላት መሆን እንደሚችሉ እያሳየ ያለ ተግባር የ“ሞተር አልባ ቀን” ፕሮግራም ነው።
በሐረሪ ክልል በየሳምንቱ በሚካሄደው ይህ ልዩ እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳየ ያለው ንቁ ተሳትፎ፣ ፕሮግራሙ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ተወዳጅነት እያገኘ መምጣቱን በግልጽ ያረጋግጣል።
ይህ እንቅስቃሴ ጤናማ አኗኗርን ከማበረታታት ባሻገር፣ ንጹህ አየር፣ ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ፣ የተሻለ የከተማ ኑሮ እና የተጠናከረ ማህበራዊ ትስስር ለመፍጠር ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።
የዚህ ሳምንት የሞተር አልባ ቀን ፕሮግራም
በሸንኮር ወረዳ “ሰላም ጎዳና” ለ 116ኛ ጊዜ
በሐኪም ወረዳ (ከ4ኛ ቶታል እስከ ኦጋዴን አንበሳ) ለ 30ኛ ጊዜ
የተካሄደው ፕሮግራም በህፃናት፣ በወጣቶች፣ በአዛውንቶች፣ በሴቶች እና በሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ሰፊ ተሳትፎ ታጅቦ በደማቅና በአስደሳች ሁኔታ ተካሂዷል።
🏃♂️🚴♀️ በፕሮግራሙ የተከናወኑ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች
✅ ሩጫ
✅ የባይስክል ጉዞ
✅ የቡድን ስፖርቶች
✅ የኳስ ቅብብሎሽ
✅ የገመድ ዝላይና የህፃናት መዝናኛ ጨዋታዎች
✅ የአካል ብቃት ማሳያዎች
✅ የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ መልዕክቶች
ፕሮግራሙ እያመጣ ያለው አዎንታዊ ለውጥ
ጤናማና ንቁ ማህበረሰብ መፍጠር
የአየርና የድምፅ ብክለትን መቀነስ
ማህበራዊ አንድነትን ማጠናከር
የመንገድ ደህንነት ባህልን ማዳበር
ቤተሰብና ማህበረሰብን በጋራ ማቀራረብ
የሞተር አልባ ቀን ፕሮግራም ከስፖርትና ከመዝናኛ እንቅስቃሴ በላይ የሆነ፣ ጤናማ አኗኗርን፣ አካባቢ ጥበቃን፣ የመንገድ ደህንነትን እና ማህበራዊ አንድነትን የሚያጎለብት ዘላቂ ማህበራዊ ንቅናቄ ሆኖ ቀጥሏል።
የህብረተሰቡ እየጨመረ የመጣ ተሳትፎም እነዚህ እሴቶች በሕዝባችን ዘንድ እየሰረፁ መምጣታቸውን ያሳያል።
ስለዚህ ለትውልድ የሚተላለፍ ይህን መልካም ተሞክሮ በቀጣይነት ማጠናከርና የሁሉንም ክፍል ተሳትፎ ማሳደግ ይገባል።
👉 “መንገድን ለሰው ስንሰጥ፣ ከተማችንን ለሕይወት እናዘጋጃለን!”
👉 “ዛሬ የምንወስደው እርምጃ፣ የነገ ጤናማ፣ ንጹህና ዘላቂ ከተማችን መሠረት ነው!”
የሐረሪ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
ግንቦት 23/2018 ዓ.ም
ሐረር
27/05/2026
በትላንትናው ዕለት ከሐረሪ ት/መ/ል/ቢሮ ወደ መሶብ አንድ አገልግሎት የተዋሐዱትን የአሽከርካሪ እና የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጥ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ፣ በጥራት፣ በፍትነት፣ አገልግሎት ለመስጠት በተሰራው ካታሎድ መሠረት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለመሰብ አንድ ማዕከል ደጋፊ ባለሞያዎች እና ለተቋማችን ሠራተኞች ኦሬንቴሽን ተሰጠ።
ገለጻው ለመሶብ አንድ አገልግሎት ማዕከል ውስጥ የተሽከርካሪ እና የአሽከርካሪ ብቃት አገልግሎቶች ዘርፍ ለሚሰጡ ሠራተኞች የተዘጋጀ ሲሆን
አላማውም ተገልጋዮች ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ግልፅ አገልግሎት አሰጣጥ ክህሎት ማጎልበት እንዲያስችል ታስቦ እንደሆነም ተገልጿል።
በገለጻው የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ ስነ-ምግባር የተገልጋይ አያያዝ፣ ቀልጣፋ የስራ አፈፃፀም እና የቡድን ስራና ተቋማዊ ተጠያቂነት ጉዳዮች በስፋት ተጠቅሰዋል።
ስልጠናውን በትራንስፖርት ዘርፍ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጥ ማስፈጻም ዳሬክቶሬት ኢ/ር ጃዕፈር ኢብራሒም ከካታሎዱ አንጻር በአምስቱም አገልግሎቶች ላይ ሰፋ ያለ ገለጻ እና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የተሽከርካሪ ብቃትን ማረጋገጥ ማስፈጻም በመወከል አቶ ኤልያስ ከድር የአገልግሎት አሰጣጡን ሂደት የክፍላቸውን ተጨማሪ መብራራት ባለበት ጉዳዩች ላይ ማብራሪያ ሰተዋል።
በመጨረሻም ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎችና ማብራሪያ ለሚሹ ሐሳቦች መልስና ማብራሪያ ተሰጥቶ የመሶብ አንድ አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶች የዜጎችን እርካታ በማሳደግ ለተቋሙ ውጤታማነት እና ለመንግስት የሪፎርም ስራዎች ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገለፆ የእለቱ መድረክ ተጠናቋል።
ግንቦት 19/2018 ዓ.ም
ሐረር
26/05/2026
እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሀ አረፋ በአል አደረሳችሁ ይላል የሐረሪ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ።
ቢሮው ለመላው እስልምና እምነት ተከታይ ሙስሊሞች የእንኳን አደረሳችሁ በአሉ የመተሳሰብ የመዋደድ እና በአብሮነት በሰላም እምታከብሩት ይሁንላችሁ ።
ኢድ ሙባረክ መልካም በአል!!
የሐረሪ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ
26/05/2026
📘🧒🚸 ለኬጂ ሕፃናት በቀላልና ተስማሚ አቀራረብ የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ተሰጠ
════════
ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
ሕፃናትን ከመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመጠበቅና ከታናሽነታቸው ጀምሮ የደህንነት ባህልን እንዲለምዱ ለማድረግ በሚካሄደው ቀጣይ የግንዛቤ ስራ፣ ዛሬ በሐረር ከተማ አቦከር ወረዳ በሚገኘው 152 ሴት 190 ወንድ በድምሩ 342 የኤስ ኦ ኤስ ትምህርት ቤት ለኬጂ ሕፃናት ተማሪዎችና በርካታ መምህራን የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ተሰጥቷል።
ግንዛቤው ከሕፃናቱ ዕድሜና የመረዳት አቅም ጋር በሚመጣጠን መልኩ በቀላል ቃላት፣ በምስል፣ በጨዋታ እና በተግባራዊ ማሳያዎች ታግዞ ቀርቧል። ሕፃናቱም መንገድ ሲሻገሩ ቆሞ መመልከት፣ የትራፊክ መብራቶችን መከተል፣ በመንገድ ላይ አለመሮጥና አለመጫወት፣ እንዲሁም ከተሽከርካሪዎች ራሳቸውን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው በሚያስደስትና በሚያሳትፍ አቀራረብ ተምረዋል።
በፕሮግራሙ ወቅት ሕፃናቱ በጥያቄና መልስ ተሳትፈው ያላቸውን ግንዛቤ የገለፁ ሲሆን፣ ትምህርቱንም በደስታና በፍላጎት ተከታትለዋል። ይህም ሕፃናት ከትንሽነታቸው ጀምሮ ስለ መንገድ ደህንነት ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገልጿል።
በተጨማሪም ሕፃናትን ከአደጋ ለመጠበቅ የቤተሰብ፣ የመምህራንና ማህበረሰቡ ተባብሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።
በቀጣይም በሕፃናት ላይ ያተኮሩ ተመሳሳይ የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ፕሮግራሞች በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
═══════════════════════
🚦 “ሕፃናትን ከአደጋ መጠበቅ ዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገንም ትውልድ መጠበቅ ነው!”
በሐረራ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገለሰግሎት ዳይሮክቶሬት
ግንቦት 18/2018ዓ.ም
ሐረር
24/05/2026
🚦🌿 “ሞተር አልባ ቀን… ለጤና፣ ለንፁህ አየርና ለደህንነታችን የምንወስደው የጋራ እርምጃ!” 🚶♂️🚴♀️
═════════════════════════
በሐረሪ ክልል የሞተር አልባ እንቅስቃሴ እየተወደደና እየተናፈቀ ለሕብረተሰባችን ጥቅም መካሄዱን ቀጥሏል።
“የምንራመደው መንገድ ብቻ አይደለም… ጤናማ ነገን ነው!”
በሐረሪ ክልል በየሳምንቱ በሚካሄደው የሞተር አልባ እንቅስቃሴ የህዝብ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲሆን፣ የጤናማ ኑሮ፣ የአካባቢ ጥበቃና የመንገድ ደህንነት ባህልን በማጎልበት ረገድ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገበ ቀጥሏል።
በዚሁ መሠረት፦
በሸንኮር ወረዳ “ሰላም ጎዳና” ለ115ኛ ጊዜ በሐኪም ወረዳ (ከ4ኛ ቶታል እስከ ኦጋዴን አንበሳ) ለ29ኛ ጊዜ የተካሄደው የዚህ ሳምንት ፕሮግራም በህፃናት፣ ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ ሴቶችና በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ተሳትፎ ታጅቦ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ የተከናወኑ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች:
✔️ የህዝብ ሩጫ
✔️ የባይስክል ጉዞ
✔️ የቡድን ስፖርቶች
✔️ የኳስ ቅብብሎሽ
✔️ የገመድ ዝላይና የህፃናት ጨዋታዎች
✔️ የአካል ብቃት ማሳያዎች
✔️ የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ መልዕክቶች
🌍 ፕሮግራሙ እያመጣ ያለው አዎንታዊ ለውጥ:
💚 ጤናማና ንቁ ማህበረሰብ መፍጠር
🌿 የአየርና የድምፅ ብክለትን መቀነስ
🤝 ማህበራዊ አንድነትን ማጠናከር
🚦 የመንገድ ደህንነት ባህልን ማዳበር
👨👩👧👦 ቤተሰብና ማህበረሰብን በጋራ ማቀራረብ
✨ መንገዶቻችን ከተሽከርካሪ ነፃ ሲሆኑ ለሰዎች የጤና፣ የመዝናኛ፣ የስፖርትና የማህበራዊ ትስስር ማዕከል መሆናቸው በተግባር እየታየ ነው።
👉 “መንገድ ለሰው ነው — ሕይወትን እናክብር!”
👉 “ዛሬ የምንራመደው ለነገ የተሻለ ከተማ ነው!”
═════════════════════════
የሐረሪ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዳይሮክቶሬት
ግንቦት 16/2018 ዓ.ም
ሐረር
22/05/2026
የሐረሪ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ከፊታችን ለሚከበረውን ኢድ አል አድሀ አረፋ በአል አስመልክቶ የወር ገቢያቸው አናሳ ለሆኑ የቢሮው ሰራተኞች እና ተስፋ ብርሐን ኤች አይ ቪ ሰዎች በጎ አድራጊ ማህበር የምግብ ዘይትና የፉርኖ ዱቄት ድጋፍ አደረገ።
ቢሮው ለበአሉ አስቀድሞ ያደረገው ድጋፍ አላማው የኑሮ ጫና ያለባቸውን ወገኖች በአሉን በደስታ እንዲያከብሩ ታስቦ ነው ሲሉ የቢሮው ም/ቢሮ ሐላፊ ኢ/ር ፈትሒ ቶውፊቅ ተናግረዋል።
ወ/ሮ ይርጋለም በለጠ የቢሮው ሴቶችና ህፃናት ዳይሬክተር በበኩላቸው ቢሮው ማህበራዊ ሐላፊነትን መወጣት የተቋሙ ትኩረት ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው ከአሉ በኋላ በተለይ በበአላት ወቅት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖችን መደገፍ የአብሮነትና መተሳሰብን የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
በእለቱ የድጋፍ ስነስርአት ላይ የተለያዩ የቢሮው ዳይሬክተሮች የተገኙ ሲሆን ድጋፍ የተደረገላቸው የቢሮው ሰራተኞች እና የተስፋብርሐን በጎ አድራጎት ተወካይ ለተደረገላቸው ድጋፍ ቢሮውን አመስግነዋል።
ግንቦት 14/2018 ዓ.ም
ሐረር
22/05/2026
🚸🌟 “ህፃናትን ከትራፊክ አደጋ መጠበቅ… የነገን
ትውልድ መታደግ ነው!” 🚦
══════
ሐረር | ግንቦት 14/2018 ዓ.ም
ህፃናትን ከትራፊክ አደጋ መጠበቅ የዛሬን ህይወት ብቻ ሳይሆን የነገን ትውልድ መጠበቅ ነው። ህግን የሚያከብር፣ ራሱንና ሌሎችን ከአደጋ የሚጠብቅ ንቁ ትውልድ ለመፍጠር በትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ፕሮግራሞች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። 🚸🚶♂️🚶♀️
በዚህ መሠረት በሐረሪ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዩኒቲ አካዳሚ ጋር በትብብር፣ በሐኪም ወረዳ ለሚገኙ ከኬጂ እስከ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች፣ ለመምህራን እና ለሌሎች የት/ቤቱ ሠራተኞች የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ተሰጥቷል።
ግንዛቤውን የሰጡት ኢንጂነር በቀለ አንጊያ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ በመድረኩ ላይ የትምህርት ቤቱ ርዕሠ መምህር እንዲሁም ተማሪዎች በግጥምና በመሰል መነባነብ ለተሳታፊዎች አስተማሪ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
በግንዛቤ መርሃ ግብሩ ወቅት፦
🔹 የትራፊክ ህጎችን የመከበር ጠቀሜታ
🔹 ህግን አለማክበር የሚያስከትለው አደጋ
🔹 የቅድመ አደጋ መከላከያ ጥንቃቄዎች
🔹 የመንገድ መሠረተ ልማቶችን የመጠበቅ ኃላፊነት
🔹 ተማሪዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባ የግንዛቤ ሚና
🔹 በእግረኞችና በተሽከርካሪ ተጠቃሚዎች መካከል ያለው የጋራ ኃላፊነት
በሚመለከት ሰፊ ማብራሪያና ተግባራዊ ምክሮች ተሰጥተዋል።
በፕሮግራሙ ወንድ 650 እና ሴት 750 በድምሩ 1,400 ተማሪዎች ተሳትፈው ግንዛቤ ያገኙ ሲሆን፣ መምህራንና ሌሎች የት/ቤቱ ሠራተኞችን ጨምሮ ጠቅላላ የተሳታፊዎች ቁጥር 1,448 ደርሷል።
“አደጋን ከመከሰቱ በፊት መከላከል የሁሉም ኃላፊነት ነው” በሚል መልዕክት የተካሄደው ይህ ፕሮግራም፣ ህግን የሚያከብር፣ ህይወትን የሚጠብቅ እና ለማህበረሰቡ አዎንታዊ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ትውልድ ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል!
🚸 ህግን ማክበር ህይወትን መጠበቅ ነው!
📌 በሐረሪ ክልላዊ መንግስት
ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
19/05/2026
በሐ/ክ/መ/የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ የመንግስት አገልግሎቶች ና አስተዳደር ሪፎርም ፅንሰ ሐሳብ እና አተገባበር ዙሪያ ለተቋሙ ሠራተኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የመንግስት ተቋማትን አሰራር ለማሻሻል እና ሰራተኛው በሙሉ ብቃት ሐላፊነቱን መወጣት እንዲያስችል በተዘጋጀው የስልጠና መድረክ በንግግር የከፈቱት የቢሮው ሐላፊ ኢ/ር ኢብሳ መሐመድ አክለው እንዳሉት በቀጣይ የመንግሥት አቅጣጫ ከሰራተኛው ጋር አስተሳስሮ መሔድ እና ከዘመኑ ጋር የዘመነ አገልግሎት ለመስጠት ሪፎርሙ አስፈላጊ ነው ሲሉ የእለቱን መድረክ በይፋ ከፍተዋል።
የእለቱን ስልጠና የሰጡት የቢሮው ሪፎርምና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጀማል መሐመድሻሽ የመንግስት አገልግሎት አሠጣጥ ሪፎርም ፖሊሲ፤የመንግስት ሰራተኞች ብቃት ምዘና ስርአት አሰራር፤ ነፃ አገልግሎት እና አካታች የሰራተኞች ስምሪት እና የስራ አፈፃፀም አመራር ለውጦች እና እድገቶች በሚሉ አንኳር ሠነዶች ዙሪያ ለተቋሙ ሠራተኞች ስልጠና ሰጥተዋል።
አቶ ጀማል አክለውም የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም ፖሊሲ ከዚህ በፊት ከነበረው የሚለይበት መንገድ እና በዋናነት ምን አላማን ለማሳካት እንዳለመ በስልጠና መድረክ ላይ አንስተዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊ ሰራተኞች የተሰጡ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች መልስ በመስጠት የእለቱ የስልጠና መድረክ ተጠናቋል።
የሪፎርምና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ግንቦት 11/2018ዓ.ም
ሐረር