Hakim Woreda Communication

Hakim Woreda Communication

Share

Hakim Woreda is one of the nine woredas found in Harari national regional state

02/06/2026

ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያውያን በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመምረጥ ኢትዮጵያን አሸናፊ አድርገዋል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

ጠቅላላ ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁንም አመልክቷል።

አገልግሎቱ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! ሲል ገልጿል።

አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመላከተው፣ ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችውን ሁሉ በፈለገችው ጊዜና ሁኔታ የምታገኝ ሀገር መሆኗንና ለሀገራቸው የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ እንደምትኮራ ገልጿል።

ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ ከመሻቷ በላይ እንደተሳካላትና ዛሬም የተደገመው ይኸው እንደሆነ አብራርቷል።

ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን ለመምረጥ እንዲሁም ሕገ-መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ለማስያዝ እንደምትሻ የጠቀሰው መግለጫው፤ ለዚህ ደግሞ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም ማስፈለጉን አስታውቋል።

ለዚህ አገራዊ ጥሪ በምላሹ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው ቀኑን ሲጠባበቁ መቆየታቸውንና የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበልም በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ መዋላቸውን አገልግሎቱ ገልጿል።

መራጮች ሌሊቱንም ጭምር አጋምሰው ድምፅ የሰጡ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈው ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫ ያደርገዋል ብሏል።

ምርጫው እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተው ያልቆፈሩት ጉድጓድና ያልደረደሩት እንቅፋት እንዳልነበረ የጠቀሰው መግለጫው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር ባለመኖሩ ሂደቱ በስኬት መጠናቀቁንና ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ ማሸነፏን አረጋግጧል።

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃው ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ የላቀ ምስጋና ታቀርባለች ሲል አገልግሎቱ አስታውቋል።

Photos from Harari Government communication affairs Office's post 01/06/2026
28/05/2026

በጥሞና ወቅት ምን ምን ማድረግ አይቻልም?

ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ምርጫው ዕለት ድረስ ያሉት ቀናት የጥሞና ቀናት ናቸው።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ መከናወን የሌለባቸው ጉዳዮች ፦

👉በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች ማካሔድ አይቻልም

👉ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች፤ የቤት ለቤትና የዐደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች አይካሔዱም ፤

👉የቅስቀሳ ኅትመቶችን እና ቁሳቁሶችን መለጠፍና ማሠራጨት፤ እንዲሁም ለቅስቀሳ የሚያገለግሉ አልባሳትን መልበስ አይቻልም፤

በእነዚህ የጥሞና ቀናት ውስጥም መገናኛ ብዙሃን ባሏቸው የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች፣ ፕላትፎርሞች ማስተናገድ የሌለባቸው ጉዳዮች ፦

👉በቀጥታ ሥርጭትም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞችን ማስተላለፍ አይቻልም፤

👉እነዚህ ስርጭቶች የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግንም የሚያካትቱ በመሆናቸው አይስተናገዱም፤

👉በየትኛውም አካባቢ የፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ ሥራዎች በእነዚህ የጥሞና ቀናት አይስተናገዱም

የጥሞና ጊዜን ማክበር የምርጫውን ተዓማኒነት ያረጋግጣል! መራጩም ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወሥን ይረዳል።

Photos from Hakim Woreda Communication's post 27/05/2026

የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሀረር እየተከበረ ነው

በሀረሪ ክልል 1ሺሕ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሀረር ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።

በክልሉ በገጠርና ከተማ ወረዳዎች የሚገኘው የእምነቱ ተከታይ ከማለዳው ጀምሮ በሀረር በሚገኘው ኢማም አህመድ ስታድየም በመሰባሰብ እያከበሩት ይገኛሉ።

በበዓሉ አከባበር ላይም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ፣ የሃይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ የክልሉ መንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Photos from Hakim Woreda Communication's post 26/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው ዓመት ሂጅራ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ:- አቶ ዙቤር መሀመድ

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በሃይማኖቱ አስተምህሮ መሰረት የተቸገሩ ወገኖቹን በማሰብና ያለውን በማካፈል እንዲሆን አስገንዝቧል።

እንደዚሁም ህዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር አንድነቱንና ወንድማማችነቱን በሚያጠናክር መልኩ በዓሉን ማሳለፍ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

በዓሉ የሰላም ፣የብልፅግና፣ የመረዳዳት፣ የስኬት፣የፍቅር፣የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣የአብሮነት እንድሆንላችሁ ስል የሐኪም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዙቤር መሀመድ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

Photos from Hakim Woreda Communication's post 26/05/2026

የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ፣ የሚሊሻ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ የፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮችና አባሎች፣የወረዳ አመራሮች ፣የሰላም አደረጃጀቶች ፣የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላቶች ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በአል የስግደት ቦታዎችን የፅዳት መርሃ ግብር ተካሄደ ፡፡---------------------------
ማክሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም
ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በአል የስግደት ቦታ በኢማም አህመድ እስታዲየም እና በሁሉም የስግደት ቦታዎች የፅዳት መርሃ ግብር በዛሬው እለት የተከናወነ ሲሆን
በመርሃ ግበሩ የተገኙት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ የ1447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በአል በሁሉም ስግደት የሚደረግባቸውን ቦታዎች በአብሮነት በማፅዳት የተባበሩትን የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮችና የህብረተሰብ ክፍሎች ፣የሰላም አደረጃጀቶች ፣ወጣቶችን በጋራ በማመስገን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ፡፡

የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤም ሃይማኖታዊ በዓላትን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አንድነቱንና ትብብሩን የሚያጠናክርባቸው መልካም እሴቶቻችን ናቸው በማለት እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በአል ዋዜማ አደረሳችሁ በማለት መርቀዋል ፡፡

አቶ ቶፊቅ መሀመድ አክለውም ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እለት ዋዜማ ላይ እንደመገኘታችን ኃይማኖቶች ለሰላም ፣ለአብሮነት ፣ለአንድነትና ለሀገር ግንባታ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው በክልላችን ላለው ዘላቂ ሰላም የሁላችንም ድርሻ እና ሀላፊነት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ክልላችን በምትታወቅበት የተለመደ የመከባበር ፣የመተዛዘንና የመረዳዳት እሴትን በመተግበር መሆን እንዳለበት እና ከተማችንን ፅዱና ማራኪ ማድረግ እንዳለብን በማህበራዊ ሚዲያ ሀገር ጠል የሆኑ ግለሰቦች የሚያሰራጩትን የተሳሳተ መረጃ እንዲሁም የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችና ቡድኖች እኩይ ሴራ በማጋለጥ ማህረሰቡ ለሰላማችን ዘብ ሊቆምና 7ኛውን አገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ በመንገድ ማጠናቀቅ ይገባናል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በመርሃ ግብሩ የሚሊሻ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ ፣የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮችና መኮንኖች ፣የወረዳ አመራሮች ፣የሰላም አደረጃጀቶች ፣የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላቶች ፣የሰላና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የማኔጅመንት አባላቶች ፣የሚሊሻ አባላት ተገኝተዋል ፡፡

Photos from Hakim Woreda Communication's post 25/05/2026

ድምፃችን የነገ ማንነታችን ውሳኔ ነው!

የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ከማለዳ ጀምሮ በደመቀ ሁኔታ በሀረሪ ክልል እየተካሄደ ነው ።

በዝህም የድጋፍ ሰልፍ የሐኪም ወረዳ አመራሮች ፣ ወጣቶች፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ በአጠቃለይ መለው የሐኪም ወረዳ ነዋሪዎች ከጠዋት ጀምረው በነቂስ እና በደማቅ ሁኔታ በመገኘት ለፖርቲው የላቸውን ድጋፍ አሳይቷል።

ድምፃችን የነገ ማንነታችን ውሳኔ ነው! በመሆኑም ምርጫችንን ለምናውቀው፣ በተግባር ለምናምነውና ሁልጊዜም ከጎናችን ለቆመው ፓርቲያችን እንሰጣለን!

Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Harar

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00