Harar TVET Agency Prosperity party

Harar TVET Agency Prosperity party

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Harar TVET Agency Prosperity party, Political Party, Harar.

Photos from Harar TVET Agency Prosperity party's post 02/04/2026

የግል እና የመንግስት ተቋማት ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች በሀገራዊ ምርጫ መሳተፍ አለበቸው:- ወ/ሮ ኢማን መሐመድ
----------------------------------------------------

የሀ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ በክልሉ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ተቋማት ተጠሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኢማን መሐመድ ምርጫው እንዲሳከ የግል እና የመንግስት ተቋማት ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መሳተፍ አለበቸው ሲሉ ገልፀዋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አክለውም ሁሉም ሰልጣኞች ተገቢውን ኦሬንቴሽን በመውሰድ ምርጫ ካርድ በመውሰድ ድምፃቸውን መስጠት እንደሚገበ አሳውቋል።

በዕለቱ ውይይት ላይ የተገኙት አቶ አፈንዲ ሰለሞን በግል ተቋማት የሚገኙ ሰልጣኞች በርካታ በመሆነቸው ሁሉም ሰልጣኞች በሚኖሩበት አከባቢያቸው የምርጫ ካርድ በመውሰድ እንዲሳተፉ አሳስቧል።

በመድረኩ የተገኙት የግል እና የመንግስት ተቋማት ዲን እና ተጠሪዎች ለሰልጣኞች እና ለአሰልጣኞች ተገቢውን ኦሬንቴሽን በመስጠት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲሳተፉ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ለተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የኤጀንሲው ዳይሬክተር መልስ በመስጠት የዕለቱ ስብሰባ ተጠናቀቀ።

በውይይቱ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኢማን መሀመድ፣ አቶ አፈንዲ ሰለሞን፣ የኤጀንሲው ተወካዮች እንዲሁም የግል እና የመንግስት ዲኖች ተገኝቷል።

መጋቢት 23/2018 አመት
ሐረር
ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/harar.tvet?mibextid=ZbWKwL
ቴሌግረም:- https://t.me/H_Tvetagency

Photos from Harar TVET Agency Prosperity party's post 01/04/2026

የሐ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ የብልፅግና ህብረት 3ኛ ሩብ አመት ኮንፈረንስ በደማቅ ሁኔታ አካሄደ።
----------------------------------------------------

የሐረሪ ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የብልፅግና ህብረት የሁለተኛ ሩብ አመት ኮንፍረንስ በደመቀ ሁኔታ ተካሄዷል።

መርሃ ግብሩን የመክፈቸ ንግግር ያደረጉት የሐ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ ህብረት ሰብሳቢ ወ/ሮ ኢማን መሀመድ በኤጀንሲው ብልፅግና ህብረት የተሰሩ ስራዎች አበራተች መሆኑን ጠቅሰው በኮንፍረንሱ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ለኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች አቅርበው ውይይት አካሄዷል።

በኮንፍረሱ ላይ :- 1.የብልፅግና ህብረት እና የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ኮሚቴ የ 2018 ዓ.ም 3ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ አባላቱ በሙሉ ድምፅ አፀድቋል።

የኤጀንሲው ብልፅግና ህብረት ምክትል ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ዘርፍ ሰብሳቢ አቶ ደምመላሽ ይህዓለም ለኤጀንሲው አባላት በ3ኛ ሩብ አመት የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን አባላቱ ውይይት ሰፊ ውይይት በማድረግ በሙሉ አፅድቋል።

የኤጀንሲው አባላት በቀጣይ ያልተሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ እንዲሁም የላቀ አፈፃፀም እንዲየመጡ ሁሉም አባላት በትጋት መስራት እንደሚጠበቅበት የሐ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ ብልፅግና ህብረት ሰብሳቢ ወ/ሮ ኢማን መሀመድ አሳስቧል።

በተጨማሪም በኮንፈረንሱ በመመሪያው መሰረት የተጓደሉ የህብረቱ አመራርን በመምረጥ እና በማጸደቅ እንዲተኩ ተደርጓል።

በመጨረሻም አንድ እጩ አባልን ወደ አባልነት እንዲሁም ሁለት እጩ አባላትን በማፅደቅ የ3ኛ ሩብ አመት ኮንፈረንስ ተጠነቀቀ።

መጋቢት 23/2018 አመት
ሐረር
ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/harar.tvet?mibextid=ZbWKwL
ቴሌግረም:- https://t.me/H_Tvetagency

Photos from Harar TVET Agency Prosperity party's post 31/03/2026

ከሀሰተኛ መረጃዎች በመጠንቀቅ ሁሉም አባላት የጠላት ፕሮፖጋንዳን ማክሸፍ አለበት:- ወ/ሮ ኢማን መሐመድ
**************************************************

የሐረሪ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ብልፅግና ህብረት “ለአኢትዮጽያ መቆም የጠለትን ቀኝን ማሳጠት ስልት የመመከቻ ብሄራዊ አርበኝነት ስትራቴጂ እና የማስፈፀሚያ እቅድ” በሚል የተዘጋጀ ስልጠና ለአባላቱ ሰጠ።

የዕለቱን ሰነድ ያቀረቡት ወ/ሮ ኢማን መሀመድ የኤጀንሲው ዳይሬክተር እና የብልፅግና ህብረት ሰብሳቢ ሁሉም አባላት ከሀሰተኛ መረጃዎች እንዲጠነቀቅ እንዱሁም ሌሎች ክፍሎችንም ግንዛቤ በመፍጠር የጠለትን ፕሮፖጋንዳ ማክሸፍ ይጠበቀል ሲሉ ገልፀዋል።

ጊዜው የቴክኖሎጂ በመሆኑ ሁሉም አባላት በተለያዩ ሚዲያዎች የሚዘዋወሩትን ሀሰተኛ መረጃዎች የአርበኝነት ስትራቴጂ በመጠቀም እንዲሁም የሚዲያ አርሚ በመሆን መዋጋት ይኖርብነል ሲሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ እና አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ለተግለገዮች ቀልጣፈ በሆና መንገድ ማስተናገድ እንደሚገበ አሳስቧል።

የኤጀንሲው የብልፅግና ህብረት አባላት በበኩለቸው በቀረበው ሰነድ ጊዜውን የጠበቀ እንዲሁም 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ በተቀረበበት ሰዓት ሀሰተኛ ወሬዎችና መረጀዎችን የሚዲያ ሰራዊት በመሆን ሀለፊነተቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

በተጨማሪም አባላቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም እንደሚሰሩ አሰዉቋል።

በመጨረሸም ከአባላት ለተነሱ ጥያቄ ሀሰብ እና አስተያየቶችን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር እና የብልፅግና ህብረት ሰብሳቢ ወ/ሮ ኢማን መልስ በመስጠት የዕለቱ ስልጠና ተጠናቀቀ።

መጋቢት 22/2018 አመት
ሐረር
ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/harar.tvet?mibextid=ZbWKwL
ቴሌግረም:- https://t.me/H_Tvetagency

17/02/2026

የሀ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ ሰራተኞች የኢትዮጽያ ብሄራዊ መዝሙር
🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹

Photos from Harar TVET Agency Prosperity party's post 14/02/2026

ብልፅግና ፓርቲ ትላንት የታለሙ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ዛሬ በተግባር አሳክቶ ለህዝብ ጥቅም ያዋለ ብርቱ ፓርቲ ነው:- ወ/ሮ ኢማን መሐመድ
************************************************

የሐረሪ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ብልፅግና ህብረት
የምርጫ ማኔፌስቶ እና ለአባላቱ የአርማ ትውውቅ አካሄደ።

የሀ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ ብልፅግና ህብረት ሰብሳቢ እና የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኢማን መሐመድ የ7ኛው አገራዊ ምርጫ የብልጽግና ምልክት "የስንዴ ነዶ" መሆኑን ገልፀው ይህ ምልክት የመደመር ፍልስፍናችን፣ የብልጽግና ስኬቶቻችን እና የአንድነታችን ወካይ መገለጫ እንደሆነ ጠቅሱ፡፡

በተጨማሪም የዘንድሮ ምርጫ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" የሚል መሪ ቃል የመረጥነው የብልጽግናችን የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ማሻገር በመሆኑ ነው በማለት ገልፀዋል።

ኢትዮጵያን ማሻገር የሚቻለው በስራ እና በፅናት ብቻ ነው! ለነገዋ የተከበረች ሀገር እና ለልጆቻችን ለምለም ምድር ለማስረከብ ብልፅግናን እንመርጣለን!

በመጨረሻም የኤጀንሲው ብልፅግና ፓርቲ አባላት የኢትዮጽያ ብሄረዊ መዝሙር በመዘመር የዕለቱ መርሃ ግብር ተጠናቀቀ።

ብልፅግናን መምረጥ—ኢትዮጵያን የማሻገር ውል! 💙🌾

የካቲት 07/2018
ሐረር

Photos from Harari Government communication affairs Office's post 12/02/2026
Photos from Harari Region Prosperity Party - ብልፅግና's post 06/02/2026
Photos from Harar TVET Agency Prosperity party's post 05/02/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ቃል የሀረሪ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ ብልፅግና ህብረት ለአባላቱ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።
***************************************************

በትለንትነው እለት የተጀመረው “ኢትዮጰያን ወደ ተምሳሌት ሀገር”በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የአባለት ስልጠና መድረክ "ውጤታማ ምርጫ ለተምሳሌት ሀገር" እንዲሁም “ጠንካረ አደረጃጀት ለተሳከ ምርጫ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ሰነዶች የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር እና የህብረቱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ኢማን መሐመድ ለአባላቱ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ 7ዉን ምርጫ የምታደርገዉ ከቀደሙት ምርጫዎች በተሻለ መንገድ ማስፈጸም የሚችሉ የዴሞክራሲ ተቋማትን በገነባችበት ወቅት ነዉ፡፡

በመሆኑም ዘንድሮ የሚደረገዉ ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በመሆን በሀገራችን የምርጫ ታሪክ ሌላ የስኬት ምዕራፍ ይከፍታል፡፡

ለዚህ አላማ መሳካትም የምርጫዉ ባለቤት የሆነዉ መላዉ አባለቱ መሳተፍ ይኖርበታል በማለት ገልፀዋል።

በሁለተኛ ቀን “የብልፅግና ፖርቲ አመራሮችና አባላት ሊያውቋቸውና ሊያከብረቸው የሚገቡ ምርጫን የሚመለከቱ የአገሪቱ መሰረታዊ ሕጎች” በሚል ቃል የተዘጋጀውን ሰነድ ለአባላት አቅርበዋል እንዲሁም የፓርቲ አባላት በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ቀን እና በድህረ ምርጫ ቀናት ተልኮዎች አስገንዝበው ሁሉም የፓርቲ አባላት ዲጂታል መታወቂያ እንዲወስዱ አቅጣጫ ሰጥቷል።

በመጨረሻም አባላቱ በቀሩበት ሰነዶች ዉይይት በማድረግ ለተነሱት ጥያቄዎች እና ሀሰቦች ማብራሪያና መልስ በመስጠት ሲካሄድ የቆያው ስልጠና ተጠናቀቀ።

ጥር 28/2018
ሐረር

05/02/2026
Photos from Harar TVET Agency Prosperity party's post 04/02/2026

''ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር'' በሚል መሪ ሀሳብ የሀረሪ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ ብልፅግና ህብረት ስልጠና መስጠት ጀመረ።
***************************************************
የሀረሪ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ “ኢትዮጰያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል ለአባለት ስልጠና መስጠት ጀመረ።

መድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር እና የህብረቱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ኢማን መሐመድ ውይይቱን ያስጀመሩ ሲሆን በመቀጠልም ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል።

ስልጠናው የአባላቱን እውቀት፣ ክህሎት እና አቅምን የሚገነባ በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል። እንዲሁም ስልጠናው ለሁለት ቀን እደሚቆይ ተገልፆል።

ጥር 27/2018
ሐረር

Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address

Harar