02/10/2026
የሃዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በሚያወጣ ወጪ የመድኃኒት ግዥ ፈጸመ፡፡
ቀን 22/01/2019 ዓ.ም ሃዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል
...........................................................................
.............................................
የሃዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል የተጠቃሚዎችን እና የህሙማንን እርካታ ይበልጥ ለማሳደግ እንዲሁም በአቅርቦት በኩል የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት በዛሬው ዕለት ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከፍተኛ የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓት ግዥ መፈጸሙን አስታወቀ።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ (CEO) አቶ ሀይልሸት በቀለ እንደገለጹት፣ ይህ ግዥ የተፈጸመው የህሙማንን እንግልት ለመቀነስ እና በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶችን ሙሉና ተደራሽ ለማድረግ ነው። አስፈላጊ የሆኑ የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓቶች መሟላታቸው የህሙማንን ፈጣን ማገገም ከማረጋገጡም በላይ የሆስፒታሉን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ወደ ላቀ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ብለዋል።
ሆስፒታሉ የሕዝባችንን የጤና ዋስትና ለማረጋገጥና ደረጃውን የጠበቀ፣ አስተማማኝና ተደራሽ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ይቀጥላል።