Hadiya Zone Education Department

Hadiya Zone Education Department የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ የሚገኘው በማዕከላዊ ኢቲዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ውስጥ ሲሆን በትምህርት ሚንስቴር ስር ሆኖ ከተዋቀረበት ጊዜ ጀምሮ ዓላማውን አንግቦ ኢየሰራ ይገኛል፡፡

26/09/2026

Masqal ugudo "2019 H. D"

https://www.facebook.com/share/1JxUzNggBz/
17/09/2026

https://www.facebook.com/share/1JxUzNggBz/

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ተደርጓል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት በመጠቀም ማየት እንደሚችሉም ጠቁሟል፡፡

የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት ይህንን ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/view-placement መጠቀም እንደሚችሉም ጠቁሟል፡፡

በምደባው ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት ብቻ ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንዲያቀርቡም አሳስቧል፡፡

የቅሬታ ማቅረቢያ ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints
በዚህም በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመምጣት የሚቀርብ የምደባ ቅሬታ የማይስተናገድ መሆኑን፤ በተጨማሪም የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ መሆኑን ተማሪዎችና ወላጆች እንዲገነዘቡ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያለ2019 የትምህርት ዘመን መጀመሪያ ለወላጆች፣ ለተማሪዎች እና ለመምህራን ያስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ እና የጥሪ መልዕክት -===ለክቡራን ወላጆች እና አሳዳ...
16/09/2026

የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ
ለ2019 የትምህርት ዘመን መጀመሪያ ለወላጆች፣ ለተማሪዎች እና ለመምህራን ያስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ እና የጥሪ መልዕክት -===
ለክቡራን ወላጆች እና አሳዳጊዎች፦
አዲስ የትምህርት ዘመን ሲጀመር የልጆቻችሁን መጻኢ እድል ለመቅረጽ የምናደርገውን ጥረት የምታግዙበት ወቅት ነው። የ2019 የትምህርት ዘመን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ተገንዝባችሁ ልጆቻችሁ ካለ ምንም መዘግየት በመደበኛው የትምህርት ካሌንደር መሠረት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። አስፈላጊውን የትምህርት ግብዓት በማሟላት፣ መጻሕፍትን በማደራጀት እና የተማሪዎችን ሥነ-ምግባር በመከታተል ረገድ የበኩላችሁን የቤት ሥራ እንድትወጡ አደራ እንላለን። የትምህርት ጥራት የሚረጋገጠው በቤት እና በትምህርት ቤት መካከል ጠንካራ ትብብር ሲኖር ነው። ህርት ቤት መካከል ጠንካራ ትብብር ሲኖር ነው።
ለውድ ተማሪዎች፦
አዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ እውቀት የምትገበዩበት፣ አዳዲስ ዕድሎችን የምታገኙበት እና ለነገይቱ ሀገራችሁ የምትዘጋጁበት ልዩ ምዕራፍ ነው። ጊዜያችሁን በአግባቡ በመጠቀም፣ በትጋት በማጥናት እና የትምህርት ቤታችሁን ሕግና ሥርዓት በማክበር ውጤታማ እንድትሆኑ እንመክራችኋለን። ካለፈው ዓመት ጥንካሬና ድክመቶቻችሁ በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከትምህርት መጀመሪያ ቀን ጀምሮ በንቃት እንድትሳተፉ እናሳስባለን።
ለክቡራን መምህራን እና የትምህርት ባለሙያዎች፦
ትውልድን የመቅረጽ እና ሀገርን በትምህርት የመገንባት ታላቅ ኃላፊነት በናንተ ትከሻ ላይ ይገኛል። አዲሱን የትምህርት ሥርዓተ ትምህርት በአግባቡ ወደ ተማሪዎች በማድረስ፣ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና የመማር ማስተማር ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በተለመደው የሙያዊ ቁርጠኝነት እንድትረባረቡ ጥሪያችን የላቀ ነው። የትምህርት መክፈቻ ጊዜን ተከትሎ የሚጠበቅባችሁን ቅድመ ዝግጅት በወቅቱ በማጠናቀቅ ለውጤታማ ሥራ እንድትዘጋጁ እናሳስባለን።
ለሁላችሁም የተሳካ፣ የሰላም እና የውጤታማነት የ2019 የትምህርት ዘመን እንዲሆንልን እንመኛለን።

15/09/2026

+-------------------------------------------------------------------------+

| HADYA ZONE EDUCATION DEPARTMENT |
| "የነገው ብሩህ ተስፋ ዛሬ በክፍል ውስጥ ይገነባል!" |
+-------------------------------------------------------------------------+

| |
| [ PHASE 1 ] [ PHASE 2 ] [ PHASE 3 ] |
| Early Enrollment School Readiness Active Learning |
| 🎒 🏫 🧠 |
| (ቅድመ ምዝገባ) (የትምህርት ቤት ዝግጅት) (ንቁ ተሳትፎ) |
| |
| │ │ │ |
| └──────────────┬───────┴──────────────────────┘ |
| ▼ |
| [ ULTIMATE GOAL ] |
| ✨ Future Achievement ✨ |
| (የተተኪው ትውልድ ስኬት) |
| 🎓 |
+-------------------------------------------------------------------------+

| |
+-------------------------------------------------------------------------+

የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ከሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ==ለመላው የዞናችን መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የትምህርት አመራሮች፣ ወላጆች እና የትምህርት ማህበረሰብ አባላትበሙሉ፤በመጀመሪያ መላው የ...
10/09/2026

የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ከሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ==

ለመላው የዞናችን መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የትምህርት አመራሮች፣ ወላጆች እና የትምህርት ማህበረሰብ አባላትበሙሉ፤በመጀመሪያ መላው የሀገራችን ህዝቦች በተለይም የዞናችን ነዋሪዎች ከ2018 ዓ.ም ወደ አዲሱ 2019 ዓ.ም ዘመንመለወጫ በሰላም፣ በጤና እና በደስታ ስላሸጋገራችሁ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።
ያለፈው የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ጥራት ማሻሻል፣ በስነ-ምግባር ግንባታ እና በውጤታማነት ረገድ
በርካታ ስራዎችን የሰራንበት፣ ተግዳሮቶችን በጋራ ጥረትና ትብብር የተሻገርንበት ዓመት ነበር። ለዚህም በትምህርትስራችን ላይ ሌሊትና ቀን በመልፋት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ መምህራን፣ ለዞኑ አመራሮች፣ ለወላጆችና ለባለድርሻአካላት በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
አዲሱ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዞናችን ይበልጥ የተሳካ የትምህርት ስራ የምናከናውንበት፣ የትምህርት ጥራትንይበልጥ የምናረጋግጥበት እና የተማሪዎቻችንን ውጤት የምናሻሽልበት እንዲሆን እንመኛለን። ተማሪዎቻችን ለአዲሱየትምህርት ዘመን በከፍተኛ ተነሳሽነትና ትጋት ራሳችሁን እንድታዘጋጁ፣ ወላጆችም እንደ ሁልጊዜው ለልጆቻችሁ
አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የትምህርት ስኬት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።
መልካም አዲስ ዓመት!
የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ

Address

Hossana
Hossana
0024

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya Zone Education Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share