Yetimgeta Asrat Maru

Yetimgeta Asrat Maru President of Central Ethiopia Region State

28/10/2026
 #ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ራዕይ! በመደመር መንግስተ ምስረታ ማግስት ስናደርጋቸው የነበሩ ህዘባዊ ውይይቶች የዚህ ዙር የመጨረሻ መድረክ_የም።የታሪክ፣ የባህል፣የሥልጣኔ፣ እና ሌሎቹ...
27/10/2026

#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ራዕይ!

በመደመር መንግስተ ምስረታ ማግስት ስናደርጋቸው የነበሩ ህዘባዊ ውይይቶች የዚህ ዙር የመጨረሻ መድረክ_የም።

የታሪክ፣ የባህል፣የሥልጣኔ፣ እና ሌሎቹንም መገለጫዎቹን ጠብቆ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የማሸጋገር ልምድ ባካበተዉ፣ የታማኝነትና የታታሪነት ልዕልናን በተጎናፀፈዉ፣ ስርቆትን እና ተመፅዋችነትን በሚፀየፈው በየም ምድር ተገኝተን፣ ከየም ዞን ወረዳዎች እና ከሳጃ ከተማ ከተዉጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር በዘላቂ ሠላም፣ በልማት፣ በመሠረተ ልማት እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ዛሬ ምከክር አድርገናል።

በተጨማሪም፣ የተፈጥሮ ጥበብ ግዝፈት ማሳያ በሆነዉ በሰንሰለታማዉ ቦር ተራራ ተገኝተን፣ የዘንድሮዉን የጥቅምት 17 ዓመታዊዉን የየም የሀገር በቀል መድኀኒት ለቀማ እና ቅመማ ስነ ስርዓት _'ሳሞ ኤታ' ታድመናል። ብዙ አስደማሚ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ገፅታዎችን ተመልክተና። ይህንን ጠብቀዉ ላቆዩልን ለቀደምት የየም ትዉልዶች አክብሮታችን ከፍ ያለ ነዉ፤ ከልብ እናመሠግናለን!

የዕለት ተዕለት ዉሎዉ በታታሪነት፣ በታማኝነት እና በመልካም እሴቶች የታነፀዉን የየም ሕዝብን ይዘን፣ የአካባቢውን ፀጋ ወደ ሀብት ለመቀየር፣ የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ ታታሪዎችና ታማኞች ሆነን እንሠራለን።

 #ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ራዕይ!ህዝባዊ ምክክራችን ቀጥሏል!መሠረታቸዉ የ'ሴራ' ባህላዊ ስርዓትና እሴት ከሆኑት፣ ከኅብር፣ ከትብብርና ከመደመር እሳቤ የተግባር  አብነቶቹ _ ከሀላ...
25/10/2026

#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ራዕይ!

ህዝባዊ ምክክራችን ቀጥሏል!

መሠረታቸዉ የ'ሴራ' ባህላዊ ስርዓትና እሴት ከሆኑት፣ ከኅብር፣ ከትብብርና ከመደመር እሳቤ የተግባር አብነቶቹ _ ከሀላባዎች ጋር ዛሬ ምክክር አካሂደናል።

ከሀላባ ዞን ወረዳዎች እና ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ የተዉጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች በሠላም፣ በመሠረተ ልማት፣ በልማትና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳባቸዉን፣ አስተያየታቸዉን፣ ጥያቄአቸዉን ሰንዝረዋል፤ ንቁ ተሳትፏቸዉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል ።

የሀላባ ህዝብ ፣ ለጋራ ግብ፣ በተነሳሽነት የመሥራት የመደመር እሳቤ አብነት ነዉ፤ ይህንን ብርቱ ህዝብ ይዘን የሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በትጋት እንሠራለን።

24/10/2026
 #ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ራዕይ!ህዝባችንን ማዳመጥ ቀጥለናል፣በ'ለማ ለሞ' እሴት፣ በደጋሌ ዋርካ  ስር በዳበረ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓቱ ከሚታወቀዉ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ  ከተዉጣጡ...
24/10/2026

#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ራዕይ!

ህዝባችንን ማዳመጥ ቀጥለናል፣

በ'ለማ ለሞ' እሴት፣ በደጋሌ ዋርካ ስር በዳበረ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓቱ ከሚታወቀዉ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ከተዉጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሠላም፣በመልካሞ አስተዳደር ፣ በልማት እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ምክክር አድርገናል።

የጠሞባሮ ልዩ ወረዳ በልዩ ልዪ ፀጋዎች የታደለ ነዉ፣ አነዚህን ፀጋዎች በማዉጣት፣ በማልማት የዜጎችን ሕይወት ማሻሻል ደግሞ የተቃና እሳቤና የተቀናጀ አመራር ይሻል ።

የሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በትጋት እንሠራለን፤ የምንሰስተዉ ጉልበት ፣ የምናባክነዉ ጊዜ አይኖርም። ሌብነትን እና ስንፍናን በእውነት፣ በትጋት እና በፍትሃዊነት እንታገላለን።

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yetimgeta Asrat Maru posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share