Ethio First

Ethio First

Share

ወንጀል ፈፅመው እስከ አለም ዳርቻ ቢሮጡ ከአይን እይታ እንጂ ከአይምሮ ፀፀት አያመልጡም !!

01/04/2026

የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በአየር ክልላቸው እንዳያልፉ የከለከሉ አገራት፦ ስፔን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ስዊዘርላንድ።

ፖላንድ፦ ለአሜሪካ የሚሳኤል ባትሪዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነችም።

የማይታመን ነገር እየተከሰተ ነው፤ አውሮፓውያን ለብዙ አሥርተ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ የራሳቸውን ውሳኔ እየወሰዱና የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ወደ ጎን እየገፉት ይገኛሉ።

28/02/2026

ሜጀር ጄኔራል አብዲሪሳክ ማህሙድ ሃጂ ("ኤርትራ") የሶማሊያ አየር ኃይል አዲሱ አዛዥ ሆነው ተሾሙ

40 ዓመት ያልሞላቸው ወጣቱ መኮንን በፕሬዚዳንት ፎርማጆ ዘመን በኤርትራ (SAWA) ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ እና ትግርኛን አቀላጥፈው የሚናገሩ 10,000 የሶማሊያ ወታደሮችን መርተዋል።

ጄኔራል ኤርትራ በአሁኑ ጊዜ ስምንት ሄሊኮፕተሮችን እና አራት ተዋጊ ጄቶችን ብቻ የሚያዝ ቢሆንም፣ ሶማሊያ ከፓኪስታን የጄኤፍ-17 ተዋጊ ጄቶችን ለመግዛት ውል ስለፈረመች የአየር ኃይሉ በሚቀጥሉት ዓመታት በአፍሪካ ውስጥ ካሉት ጠንካራ ወታደሮች አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል።

የዚያድ ባሬ አገዛዝ ከመውደቁ በፊት ሶማሊያ ከ70 በላይ ተዋጊ ጄቶች እንደነበሯት የሀገሪቷ ሚዲያዎች የዘገቡ ሲሆን ይህም ከግብፅ ቀጥሎ በአፍሪካ ሁለተኛው ትልቁ የአየር ኃይል ያደርጋት እንደነበር አክለዋል።

ኢትዮጵያ ጋር ከተደረገው ጦርነት ማግስት ግን ሶማሊያ እንኳን የጦር ጄት መንግስት ማፅናት የተሳናት እንደሆነች ነው የሚነገረው፡፡

ቴሌግራም
https://t.me/ethifirst

22/02/2026

“ህወሓት ጦርነቱን የሚጀምር ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል”

ጄ/ል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ

ከዚህ ቀደም በስልጣን ዘመኑ ያከማቸዉን የጦር መሳሪያ ታጥቆ ከፍተኛ ሽንፈት የተከናነበዉ ህወሓት አሁን ሻዕቢያን አስከትሎ ኢትዮጵያን ለመዉጋት ዝግጅት እያደረገ ነዉ፡፡

የቡድኑን የጦርነት ጉሰማ ተከትሎ የቀድሞው የሕወሃት ጦር መሪ ጀነራል ጻድቃን ገብረ ተንሳይ ሕወሃት ጦርነቱን አካሂዳለሁ እምቢ የሚል ከሆነ ፣ የሚደረገው ጦርነት እጅግ አጭርና በኢትዮጵያ በኩል በትንሽ ኪሳራ ብቻ የሚፈታ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ወንጀለኞቹ ራሳቸው የፈጠሩትን ችግር ራሳቸው እንዲጋፈጡት በማድረግ የሚጠናቀቅ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።

Photos from Ethio First's post 21/02/2026

መከላከያ ሰራዊት ትግራይ ሊገባ ነው ወይ?

ሰሞኑን የመከላከያ ሰራዊት ወደትግራይ ሊገባ ነው የሚል ወሬ ሲናፈስ የትግራይ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በOfficial ገፁ “ውሸት ነው” ምናምን ብሎ አስተባበለ። ሲጀምር የመከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለመጠበቅ ትግራይ ገብቶ ካምፕ ውስጥ ለመቀጥም ሆነ የ Security ስራ ለመስራት የግዚያዊ አስተዳደሩም ሆነ የህውሀት ፍቃድ አያስፈልገውም። ስለዚህ የታደሠ ወረደ ቢሮ ውሸት ነው እኛ አልፈቀድንም ብሎ ማስተባበል አይችልም። ሲጀምር ማን ነው በኢትዮጵያ ሰማይ ስር መከላከያ ሰራዊትን እዚህ ግባ እዚያ አትግባ ብሎ የሚፈቅድለት? የሐገር መከላከያ ሰራዊቱንስ እኛ ሳንፈቅድልህ አትገባም የሚል ክልል በአለም ላይ አለ ወይ?

መከላከያ ሠራዊታችን የኢትዮጵያ ግዛት በሆነች በእያንዳንዷ ኮሪደር ላይ የጦር ቤዝ የመትከልም ሆነ በፈለገበት የኢትዮጵያ መሬት አልፎ የመሄድ ሊከለከል የማይችል ህገመንግስታዊ መብት አለው። አለፍ ካለም ደግሞ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የትግራይን ሰላምና ሰጥታ የማስጠበቅ እንዲሁም የኢትዮጵያን ሉአላዊ ግዛቶች የመጠበቅ ግዴታ አለበት።

ትግራይ ደግሞ የኢትዮጵያ መሬት ህዝቡም የኢትዮጵያ ህዝብ አካል ነው። የትግራይ እያንዳንዷ ግዛትም የኢትዮጵያ ግዛት እንደመሆኗ መጠን ለመከላከያ ሰራዊታችን መስመር አስምሮ “በዚህ እለፍ በዚያ ደግሞ ሳንፈቅድልህ እንዳታልፍ” ማለት የሚችል አንድም አካል የለምም አይኖርምም።

ስለዚህ ብዙዎቻችሁ ወሬውን ሰምታችሁ መከላከያ ወደትግራይ ይገባል ወይ? ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ ሰዎች ምላሼ አጭር ነው። .... መግባት ሲኖርበት በፈለገው ሰአት ይገባል!!

https://t.me/ethifirst

21/02/2026

Special news : ውጥረት ባየለበት ወቅት ሶስት የቀድሞ የ ትግራይ ኃይሎች ከፍተኛ አዛዦች ወደ አዲስ አበባ ሸሹ!

ሶስት የቀድሞ የትግራይ ኃይሎች ከፍተኛ አዛዦች በዚህ ሳምንት ትግራይን ለቀው በመውጣት ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን አዲስ ስታንዳርድ አረጋግጧል።

ብርጋዴር ጄኔራል ጉዕሽ ገብሬ፣ ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ እና ኮሎኔል ንጉሤ ወልደገብርኤል የተባሉት እነዚህ መኮንኖች፤ ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የትግራይ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ የአመራር ቦታዎችን የያዙ ነበሩ።

ይህ የተሰማው፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ ከሶስት ዓመታት በኋላ በፌዴራል መንግሥቱ እና በትግራይ ባለሥልጣናት መካከል ባልተፈቱ አለመግባባቶች ምክንያት ለሳምንታት የዘለቀው ውጥረት እየተባባሰ በመጣበት እና ወታደራዊ ዝግጅቶች እየተደረጉ ባሉበት ወቅት ነው።

ብርጋዴር ጄኔራል ጉዕሽ ትናንት አርብ ዕለት ለአዲስ ስታንዳርድ በሰጡት ቃል፣ ሦስቱም መኮንኖች ረቡዕ ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸውን አረጋግጠዋል።

“ሕይወታችንን መምራት አልቻልንም። ይሰልሉናል፤ ይከታተሉናል፤ እንዲሁም ኑሯችንን አስቸጋሪ አድርገውብናል” ያሉ ሲሆን “ወደዚህ የመጣነው የራሳችንን ዘዴ ተጠቅመን ነው” ሲሉ አክለዋል።

https://t.me/ethifirst

Photos from Ethio First's post 28/01/2026

ቢቢሲ አማርኛ ባወጣው ወታደራዊ መረጃ ይዞ ወጥቷል

የኢትዮጵያ እና የጎረቤቶቿ አየር ኃይሎች አቅም ሲነጻጸር በምን ደረጃ ይገኛሉ? የሚል ሲሆን መረጃው ከዳሰሳቸው 145 አገራት ውስጥ ኢትዮጵያ በ47 ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ጎረቤቶቿ (ኤርትራ 119ኛ፣ ሱዳን 66ኛ ደረጃ፣ ኬንያ 84ኛ ደረጃ፣ ደቡብ ሱዳን 113ኛ ደረጃ፣ ሶማሊያ 137ኛ ደረጃ ይገኛሉ።)

=>በአጠቃላይ ወታደራዊ አቅም ሲታይ ከአፍሪካ ከአንድ እስከ አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ግብፅ፣ አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ ናቸው።

=>ከኢትዮጵያ ጎረቤት አገራት መካከል ከአፍሪካ በወታደራዊ አቅም ጥንካሬ ሱዳን 9ኛ፣ ኬንያ 12ኛ፣ ደቡብ ሱዳን 23ኛ፣ ኤርትራ 25ኛ እና ሶማሊያ 34ኛ ደረጃ ላይ።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር፣ የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም እና የአየር ኃይሉ አዛዥ ሰሞኑን በተከበረው የአየር ኃይሉ 90ኛ ዓመት በዓል ወቅት የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፤ እንደ አውሮፓውያኑ በ2030 የኢትዮጵያ አየር ኃይልን አቅም ወደ አምስተኛው ትውልድ ለማሻገር ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል።

አምስተኛው ትውልድ ወይም (fifth-generation) ዘመነኛ የውጊያ አቅም ያላቸው ምጡቅ የጦር መሣሪያዎችን ያካትታል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አቅም የሚገኝበትን ዘመናዊ ቁመና በመግለጽ አገሪቱን ለሚገዳደሩ ኃይሎች ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል።

"ሚግ-21 ላይ ቆመው የቀሩ" ላሏቸው አገራትም ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን እና ጥቅሟን ለማስጠበቅ በተንጠቀቅ የሚጠባበቅ ጠንካራ አየር ኃይል እንዳላት የሚጠቁም ንግግር አድርገዋል።

ሙሉ ዘገባውን ቢቢሲ አማርኛ ላይ አንብቡት

Photos from Ethio First's post 27/01/2026

የኢራን "የመሬት ውስጥ የሚሳኤል ከተሞች" (Missile Cities) በአለም አቀፍ ወታደራዊ ተንታኞች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው እና ለጠላት እጅግ አስቸጋሪ የሆኑ ስውር ምሽጎች ሲሆኑ ኢራን እነዚህን ተቋማት የገነባችው የአሜሪካን ወይም የእስራኤልን የአየር ድብደባ ለመቋቋም በሚያስችል መልኩ ነው ተብሏል።

1. ስፋትና ጥልቀት

እነዚህ ዋሻዎች ከመሬት በታች እስከ 500 ሜትር(ግማሽ ኪሎሜትር) ጥልቀት ላይ የተቆፈሩ ናቸው። ይህም የቱንም ያህል ጠንካራ የሆነ "Bunker Buster" ቦምብ በቀላሉ እንዳያፈርሳቸው ያደርጋል።
*ኢራን እነዚህ የሚሳኤል ከተሞች በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ተራራማ አካባቢዎች ስር እንደሚገኙ ትናገራለች። እስካሁን በቪዲዮ የታዩት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው ።

እነዚህ ተቋማት ሙሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚደረግባቸው ማዕከላት ናቸው፡-
ሚሳኤሎች ከመሬት በታች ሆነው በቀጥታ ወደ ላይ የሚወነጨፉባቸው አውቶማቲክ ሲስተሞች አሏቸው። በአንዳንድ ዋሻዎች ውስጥ የሚሳኤል ክፍሎችን የሚገጣጥሙ ፋብሪካዎች ጭምር አሉ። ወታደሮች ለረጅም ጊዜ መኖር የሚችሉባቸው ክፍሎች፣ የነዳጅ ማከማቻዎች እና የኤሌክትሪክ ማመንጫዎች ተሟልተውላቸዋል።

4. ስልታዊ ጠቀሜታቸው
መሣሪያዎቹ ከመሬት በታች ስለሆኑ ሳተላይቶች ሊያዩዋቸው አይችሉም። ይህም ኢራን ሳትታወቅ ድንገተኛ ጥቃት እንድትሰነዝር እድል ይሰጣታል። የአሜሪካ ጄቶች የኢራንን የአየር ክልል ቢቆጣጠሩ እንኳ፣ እነዚህን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች አንድ በአንድ አድኖ ማጥፋት እጅግ አድካሚ እና የማይቻል ሊሆን ይችላል።

ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ የነዚህን ከተሞች ምስል ለዓለም ያሳየችው በ2015 ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ግን የቴክኖሎጂ አቅሟን ለማሳየት በየጊዜው አዳዲስ ዋሻዎችን በቴሌቪዥን ትለቃለች።

Photos from Ethio First's post 14/01/2026

ውጥረቱ ተወጥሯል ..

በሰላማዊ ሰልፈኞችና በተቃዋሚዎች ያሰበችውን ያህል ያልተገፋላትን የኢራንን መንግሥት ለመጣል አሜሪኪት በአካባቢው ላይ ኃይሏን እያጠናከረች፣ ዝግጅቷን እያጧጧፈች፣ ጦሯም የዜሮዋን ሰዓት እየጠበቀ መሆኑ እየተገለፀ ነው።

* ኢራን በአካባቢው ለአሜሪካ ያልገበረች ብቸኛዋ አገር መሆኗ ይታወቃል።

* ትናንት ቱራምብ ኢራኖች እንደራደር ብለው ለምነውኛል ያለ ሲሆን ኋላ ላይ አልተቀበልኩም ብሏል።

* አሜሪካ ኢራን ያላችሁ ዜጎቼ ወደ አርሜኒያና ቱርክ ውጡ ብላለች።

* አንዳንድ የአውሮፓ አገራትም ማሳሰቢያ ለዜጎቻቸው ሰጥተዋል ።

* ኢራን ደግሞ ከተነካሁ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለ የአሜሪካ የጦር ሰፈርም ሆነ ጥቅም ሁሉ ዒላማ ውስጥ ነው ብላለች።

* ለዚህም በዋናነት አለኝ የምትለውን ባላስቲክ ሚሳይሎቿን አጥምዳለች።

* ጥቃቴ ኢዝራኢልንም ጭምር ያጠቃልላል ያለች ሲሆን ኢዝራኢል በበኩሏ በጉዳዩ የለሁበትም ካለች በኋላ ዜጎቿ ከአደጋ ጊዜ ምሽጎቻቸው እንዳይርቁ አሳስባለች።

* ኔታኒያሁ የግል አውሮፕላንም ወደ ግሪክ እንዳመራች ይነገራል ።

ምሽቱንና እስከ ነገ በብዙ ይጠበቃል።

12/01/2026

የቱርክ- ሳኡዲ አረቢያ- ፓኪስታን ወታደራዊ ጥምረት የቀጠናውን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አሰላለፍ ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ ያለውን የሀይል ሚዛንም ሌላ መልክ የሚያሲዝ ግዙፍና ጨዋታ ቀያሪ ጥምረት ነው።

ሶስቱ ሀገራት ከሙስሊም ሀገራቶች ሀያላን ናቸው። ቱርክ ከአሜራካ በመቀጠል የኔቶ ሁለተኛዋ ሀያል ጦር ባለቤት ስትሆን ወታደራዊ ቴክኖሎጂዋ ከቀዳሚዎቹ የሚመደብ ከጦር መርከቦች እስከ 5ኛው ትውልድ የጦር ጄቶች የምታመርት ከአለም 10 ሀያላን የጦር ባለቤቶች አንዷ የሆነች ሀገር ነች።

ሳኡዲ አረቢያ የአለማችን ግዙፍ የተፈጥሮ ሀብት ላኪ ሀገር ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ያላት ሀይማኖታዊና ጂኦፖለቲካዊ አቅሟ ትልቅ ተፅእኖ ፈጣሪነትን ያጎናፀፋትና ጦሯን ለማዘመን ከተፈጥሮ ሀብት የተላቀቀ ኢኮኖሚ ለመገንባት እየታተረች ያለች ሀገር ነች።

ፓኪከስታን ከአለም ብቸኛው ሙስሊም የኑክሌያር ባለቤት ሀገር ፤ J-17 የተሰኙትን ዘመናዊ ጦር ጄቶችን ፤ ከበፍተኛ የሚሳኤል ቴክኖሎጂን የምታመርት ጠንካራ ጦር ካላቸው የአለማችን ሀገራት አንዷ የሆነች ግዙፍ ህዝብና ሰፊ አቅም ያላት በጦርነት ተፈትና እዚህ የደረሰች ሀገር ነች።

የሶስቱ ሀገራት ወታደራዊ ጥምረት ታዲያ አንዱ የሌሉውን ለአንዱ የሚሰጥ ሶስቱንም በታሌቅ አቅም የሚያፀና ሌሎች ሀገራትን ለመግባት የሚያጓጓ ጥምረት ነው። የሶስቱ ጥምረት ፓኪስታንና ሳኡዲ አረቢያን ከቱርክ ዘመናዊ የጦር ቴክኖሎጂዎች ሲያጋምድ ቱርክ እና ሳኡዲ አረቢያን ደግሞ ከፓኪስታን የኑክሌር ቴክኖሎጂ ያቋድሳል። ፓኪስታን ደግሞ ከሳኡዲና ቱርክ የኢኮኖሚ የፋይናንስ በርን በከፍተኛው የሚከፍትላት ሲሆን የሶስቱ ሀገራት ጥምረት ኢኮኖሚያቸውንም የጦር ኢንዲስትሪያቸውንም የሚያሳድግ ትልቅ አብዮት የሚፈጥር ጥምረት ነው።

ጥምረቱ በቀጠናው ለምሰራፋት እየሰራ ያለውን የኢማራት-እስራኤል-ግሪክ-ህንድ አክሲስ የሚመክት የቱርክን የሀይል አማራጭ የሚያሰፋ ፤ የሳኡዲን የአሜሪካ ጥገኝነት የሚቀንስ የፓኪስታንን ኢኮኖሚ ጠግኖ ወታደራዊ አቅሟን የሚያሳድግ ፤ የህንድን ድንፋታ የሚያበርድ ነው።
እውን ሆኖ ተጠናክሮ ከቀጠለ በርካታ ሀገራት ለመግባት ደጅ የሚጠኑበት ጥምረት ይሆናል።

ይሄ ለሙስሊሙ አለም ትልቅ ተስፋ የሚያጭር ጥምረት ሲሆን ምናልባት የመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ምእራፍ ማብሰሪያም ሊሆን ይችላል!

24/11/2025

Guyyaa 15/3/2018
Aanaa Arxummaa Fursii magaalaa cirrattiti balaa ibiddi ka'een manneen sadii guutumaa guututti barbadaa'ani jiru, manni tokko gartokkoon gubatee, dabalataan balaa kanaan loowwan huubamanii jiru.

በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ በጨረቲ ከተማ ዛሬ በቀን 15/3/2018 ዓ/ም በደረሰ የእሳት አደጋ ሶስት መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ አንድ ቤት ከፊል ቃጠሎ ደርሶበታል በተጨማሪ የቀንድ ከብቶችም የአደጋው ሰለባ ሆነዋል



Police News Network

Want your business to be the top-listed Government Service?

Telephone