Kewot Wereda Government Communication affairs office

Kewot Wereda Government Communication affairs office

Share

የቀወት ወረዳ በአማራ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን መስተ?

የቀወት ወረዳ በአማራ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር ትገኛለች፡፡ወረዳዋን በሰሜን ኤፍራታና ግድም፣በደቡብ ጣርማ በር ፣በምእራብ ጣርማበርና መንዝ ማማ ወረዳዎች እንዲሁም በምስራቅ የአፋር ክልል ያዋስኗታል፡፡ የወረዳ ዋና ከተማ ሸዋሮቢት ስትሆን ከአዲስ አባባ 225 ኪ.ሜ ፣ከደብርብርሃን /ዞን ከተማ/ 95 ኪ.ሜ፣ከባህር ዳር /ክልል ከተማ/ በአዲስ አበባ በኩል 785 ከ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡የሸዋረሮቢት

03/06/2026

ከተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል የአርጎባ አንድነት ጀበርቲ ፓርቲ ስለ 7ኛው ሃገራዊ ምርጫ የሰጡት አስተያየት

Photos from Kewot Wereda Government Communication affairs office's post 03/06/2026

ምርጫው ሰላማዊ ፣ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንደነበር በምርጫ ክልሉ የተወዳደሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ገለፁ

ሸዋሮቢት ፡- ግንቦት 26/2018 ዓ/ም (ቀ/ወ/መ/ኮ) በሮቢት ምርጫ ክልል የተወዳደረው አርጎባ አንድነት ጀበርቲ ፓርቲ ምርጫው ሰላማዊ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ እንደነበረ አስታወቀ ፡፡

የፓርቲው እጩ ተወዳዳሪ አቶ ማህሙድ መሀመድ እንደገለፁት የተካሄደው ምርጫ ሰላማዊ ፍትሃዊ ዲምክራሲ እንደነበረ ያስረዱ ሲሆን በሮቢት ምርጫ ክልል ስር በሚገኙ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ማህበረሰቡ ይበጀኛል፤ ያስተዳድረኛል ፣ይሆነኛል ያለውን ወኪል ያለተፅኖ መምረጥ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

አክለውም ፓርቲያቸው በሸዋሮቢት፣ በቀወት፣ በአንኮበር የሚገኙ ማህበረሰብ ክፍል የሚወክል ሲሆን በ6ተኛ ሀገራወዊና ክልላዊ ምርጫ በሮቢት ምርጫ ክልል በነበረው የአካባቢ የፀጥታ ችግር ምክንያት ላለፉት 5 አመታት ወኪል ሳይኖረው በመቆየቱ ቁጭት ያደረበት ሲሆን በአሁኑ ምርጫ በንቃት እንዲሳተፍ እና ወኪሉን ለመምረጥ በፅናት ለመምረጥ አስቸሏታል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ህዝቡ የሰጠውን ድምፅ ይሆነኛል ያለውን ፓርቲ በመምረጡ የህዝቡነ ድምፅ በማክበር አሸናፊ ከሆነው ፓርቲ ጋር በጋራ አብረን እንሰራለን ሲሉ ሃሳባቸውን አንፀባርቀዋል ፡፡

Photos from Kewot Wereda Government Communication affairs office's post 03/06/2026

"በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ አሸንፈዋል" ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ

ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ትናንት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማካሄዷንና በአማራ ክልልም ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ መጠናቀቁን ገልጸዋል። በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ ማሸነፋቸውን ጠቅሰዋል።

"ከጥንትም ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው የክልላችን ሕዝብ ትናንት ደግሞ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ያለውን ቀናዒ ፍላጎት ለዓለም አሳይቷል፤ በአማራ ክልል ምርጫ ማካሄድ ድምጽ ከመስጠት ባሻገር ነው" ብለዋል።

በክልላችን ምርጫ እንዳይካሄድ፤ ዜጎች መብታቸውን እንዳይጠቀሙ፤ በሕዝብ ድምጽ የተመረጠ መንግሥት እንዳይመሠርት፣ ክልሉ ሁልጊዜ በድህነት እና በግጭት ውስጥ እንዲኖር የሚፈልጉ የውይይት እና የሰላም ተቃራኒ ኃይሎች ብዙ ጥረት ማድረጋቸውንም አንስተዋል። "ይሁን እንጂ በሕዝባችን አስተዋይነት እና በጸጥታ ኃይላችን ጀግንነት እነርሱ የፈለጉት ሳይኾን ሕዝብ የፈለገው ኾኗል" ነው ያሉት።

የክልሉ ሕዝብ ትናንት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያሳየው ተሳትፎ፣ ጽናት እና ትዕግሥት የብልሃት እና የጥበብ ምንጭ መኾኑን ያሰመሰከረበት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ምርጫው ሕዝቡ ለፈተና የማይበገር፤ በዛቻ እና በማስፈራሪያ የማይሰበር፣ ለሰላም እና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የትኛውንም መስዋዕትነት እንደሚከፍል ያሳየበት እንደሆነ አስታውቀዋል። "የክልላችን ሕዝብ በትናንትናው ምርጫ የፖለቲካ ሥልጣን የሚገኘው በሕዝብ ድምጽ እንጂ በኃይል አለመኾኑን ግልጽ መልዕክት ያስተላለፈበት ነው" ብለዋል።

የአማራ ክልል ሕዝብ ሰላም ወዳድነቱን፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ፈላጊነቱን፤ በሕግና በሕዝብ ይሁንታ ለሚጸና መንግሥት ቀናዒነቱን በግልጽ እንዳሳየም አብራርተዋል። ለዚህ ደግሞ የከበረ ምስጋናዬን ከጥልቅ አክብሮት ጋር ማቅረብ እወዳለሁ ነው ያሉት።

"ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ምርጫው በክልላችን በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረገው ለሀገር መከለካያ ሠራዊት፣ ለክልላችን የጸጥታ ኃይል፣ በየደረጃው ለሚገኙ የክልላችን አመራሮች እና ለመላው የክልላችንን ሕዝብ በራሴ እና በአማራ ክልል መንግሥት ስም የላቀ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።

ለሀገር እና ለሕዝብ በአንድነት መሥራት ምን አይነት ስኬታማ ውጤት እንደሚያስገኝ ምርጫው ሕያው ምስክር መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በምርጫው ጫፍ ረገጥ አስተሳሰቦች እስከ አደረጃጀቶቻቸው በሕዝብ ደምጽ ከሽፈዋል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሸንፋለች ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ባስተላለፉት መልእክት።

አሚኮ

Photos from Kewot Wereda Government Communication affairs office's post 02/06/2026

"የአለም አካባቢ ቀን" በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ሸዋሮቢት፡ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (ቀ/ወ/መ/ኮ) የቀወት ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ፅ/ቤት "የአለም አካባቢ ቀንን" በአካባቢ ፅዳት ዘመቻ እና በፓናል ውይይት በደማቅ ሁኔታ አከበረ ።

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ53ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ33ኛ በአማራ ክልል ለ29ኛ የተከበረው ይህ ወሳኝ ቀን እለቱ በተለያዩ ሁነቶች የተከበረበት መሰረታዊ ዓላማ ህብረተሰቡ በአየር ንብረት ለውጥ ተዛማጅ የአካባቢ ጉዳዮች የሚኖራቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ እና አወንታዊ ሚና የሚወጣ ዜጋ በማፍራት ፅዱ እና ምቹ አካባቢ ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል ።

የወረዳው አካባቢና ደን ጥበቃ ተጠሪ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አቶ ጌታመሳይ እንግዳወርቅ በማጠቃለያ ንግግራቸው ንፁህ ከባቢ አየር ለመፍጠርና ራሳችንን ከሰው ሰራሽ በሽታዎች ለመከላከል የቆሻሻ አወጋገድ መመሪያዎችን በመተግበርና ህጋዊ ተጠያቂነትን በማስፈን በርብርብ መስራት አለብን ሲሉ አሳስበዋል ።

Photos from Shewa Robit City Administration Kentiba office's post 01/06/2026
Photos from Amhara North Shewa Zone  Communication's post 01/06/2026
Photos from Kewot Wereda Government Communication affairs office's post 01/06/2026

በሮቢት ምርጫ ክልል 7ኛውሀገራዊ ምርጫ ተሳትፎው እንደ ቀጠለ ነው።

ሸዋሮቢት፦ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (ቀ/ወ/መ/ኮ)
በሮቢት ምርጫ ክልል 7ኛው ሀገራዊ ና ክልላዊ ምርጫ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ድምጿቸውን እየሰጡ ሲሆን ምርጫውም ሰላማዊ ድሞክራሲያዊ መሆኑንም ገልፀዋል።

Photos from Kewot Wereda Government Communication affairs office's post 01/06/2026

🗳 ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

በሸዋሮቢት ከተማ በማለዳው ድምፅ ለመስጠት የወጣው ህዝብ። 👇

🇪🇹

Photos from Tarmaber Werda communication affairs office's post 01/06/2026
Photos from የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር  ኮሙዩኒኬሽን ጸ/ቤት's post 01/06/2026
Want your business to be the top-listed Government Service in Jijiga?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Jijiga
251