Ari Zone Innovation and Technology Office

Website

Ari Zone Innovation and Technology Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ari Zone Innovation and Technology Office, Government Organization, Jinka, Jinka.

 # #ፋይዳመታወቂያ‎ ፋይዳ መታወቂያ (Fayda ID) የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (National ID Program - NIDP) የሚሰጠው የ12 ዲጂት ልዩ ዲጂታል መለያ ቁጥር ነው...
14/08/2026

# #ፋይዳመታወቂያ
‎ ፋይዳ መታወቂያ (Fayda ID) የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (National ID Program - NIDP) የሚሰጠው የ12 ዲጂት ልዩ ዲጂታል መለያ ቁጥር ነው።
‎ # #ፋይዳ ምንድን ነው?
‎በኢትዮጵያ ለሚኖሩ እና አስፈላጊውን መስፈርት ለሚያሟሉ ሰዎች የሚሰጥ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ነው።አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ የሚኖረው አንድ እና አንድ ልዩ መታወቂያ ቁጥር ነው።
‎ # #ፋይዳ ዋና ዓላማው
‎የግለሰቦችን ማንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመለየት። በተለያዩ የመንግስት እና የግል አገልግሎቶች ላይ ማንነትን ማረጋገጥ እና አገልግሎቶችን ማግኘት ለማቀላጠፍ።
‎ # #ፋይዳአግልግሎት
‎የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዎን በሞባይል መተግበሪያ (ለምሳሌ በጎግል ፕሌይ ላይ የሚገኘው) ማየት፣ ማውረድ እና ማስተዳደር ይቻላል።

# #ፈጥነው ይመዘገቡ!! "ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ለሀገራዊ ብልጽግና "
‎
‎ለወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
‎Telegram :-https://t.me/azitoTgroup
‎Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100088179777880
‎ = 0467751442
‎E-mail=[email protected]
‎
‌‎🛰‎🛰🚦🚥📌✈️🇪🇹
‎ 👉የኣሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት👈

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከጂንካ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከ60 በላይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ተሰጥኦ ላላቸው ተማሪዎች የክረምት ስልጠና መስጠት ተጀመረ፣‎‎ሐም...
06/08/2026

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከጂንካ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከ60 በላይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ተሰጥኦ ላላቸው ተማሪዎች የክረምት ስልጠና መስጠት ተጀመረ፣
‎
‎ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም (አሪ ዞን ኢቴ ጽ/ቤት)
‎
‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2018 ዓ.ም. የክረምት መርሃ ግብር ከ60 በላይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ተሰጥኦ ላላቸው ተማሪዎች ስልጠና በጂንካ ዩኒቨርስቲ እየሰጠ ይገኛል።
‎
‎ስልጠናው ከአሪ ዞን እና ከደቡብ ኦሞ ዞኖች የተውጣጡ ከ60 በላይ ተማሪዎች ከሐምሌ 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ወር ከ15 ቀናት የሚቆይ የክረምት ስልጠና እየወለዱ መሆኑን ክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የኢኖቬሽንና ምርምር ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሽብሩ በቃውሌ ተናግረዋል።
‎
‎የአሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይሄነው ተስፋዬ ፣ የስልጠናው ዋና ዓላማ ዓለም በሳይንስ፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ የደረሰበትን እድገት የሚወዳደር ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት ሲሆን፣ ቢሮውም በዘርፉ የላቀ እውቀትና ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች ለማብቃት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል ስልጠናውን ልዩ ትኩረት በመስጠት መከታተልና መሰልጠን እንዳለባቸው አሳስበው።
‎
‎የክረምት ስልጠናው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ተሰጥኦ ላላቸው ታዳጊ ወጣቶች እውቀታቸውን ለማሳደግና የፈጠራ አቅማቸውን ለማጎልበት የሚያስችል ጠቃሚ ዕድል ሲሆን፣ ለሀገሪቱ የወደፊት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድም ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
‎
‎ለስልጠናው የተመረጡት ተማሪዎች በእንግሊዝኛ፣ በሒሳብ፣ በፊዚክስ እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ላይ ተሰጥኦ ያላቸውና በትምህርት ውጤታቸው ከፍተኛ አፈጻጸም ያሳዩ መሆናቸው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይሄነው ተስፋዬ ተናግረዋል።
‎
‎ቢሮው ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ-ስፓሻል ኢንስቲትዩት እንዲሁም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሚያካሂደው ስልጠና በአስትሮኖሚ፣ በሮኬት ሳይንስ፣ በድሮን (UAV)፣ በጂአይኤስ (GIS) እና በሳቴላይት ሲስተሞች ላይ ያተኮረ የንድፈ ሐሳብና የተግባር ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጿል።
‎
‎ስልጠናው ሲጠናቀቅ በድህረ ምዘና የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በቀጣይ በሀገር አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መርሃ ግብሮች ላይ ለመሳተፍ የሚመረጡ ተማሪዎችም እንደሚኖሩ ተጠቁሟል ።
‎
‎
‎ዘገባው👉የአሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ነው።
‎
‎"ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ለሀገራዊ ብልጽግና "
‎
‎ለወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
‎Telegram :-https://t.me/azitoTgroup
‎Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100088179777880
‎ = 0467751442
‎E-mail=[email protected]
‎
‎‌🛰🛰🚦🚥📌✈️🇪🇹
‎👉የኣሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት👈
‎

20/05/2026
የአሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት Online Customer Satisfaction Evaluation             ኦን ላየን የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት 👉2018e.c👇👇👇👇👇👇👇👇...
07/05/2026

የአሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት
Online Customer Satisfaction Evaluation ኦን ላየን የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት 👉2018e.c
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉🏾https://mjv6hu1w.forms.app/arizonesitd-customer-satisfaction-survey

"ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ለሀገራዊ ብልጽግና "
‎
‎ለወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
‎Telegram :-https://t.me/azitoTgroup
‎Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100088179777880
‎ = 0467751442
‎E-mail=[email protected]
‎
‌‎🛰‎🛰🚦🚥📌✈️🇪🇹
‎ 👉የኣሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት👈

የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወጣቱን የዲጂታል ክህሎት አሳድጓል- የጂንካ ከተማ ሰልጣኞች ሚያዝያ 10/2018 ዓ.ም የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወጣቱን የዲጂታል ክህሎት ማሳደጉን የጂንካ ከተማ ሰል...
18/04/2026

የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወጣቱን የዲጂታል ክህሎት አሳድጓል- የጂንካ ከተማ ሰልጣኞች

ሚያዝያ 10/2018 ዓ.ም

የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወጣቱን የዲጂታል ክህሎት ማሳደጉን የጂንካ ከተማ ሰልጣኞች ተናገሩ።

መንግስት በኢትዮጵያ የዲጂታል ክህሎት አቅምን በማሳደግ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያለመ ስልጠና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል እየሰጠ ይገኛል።

በጂንካ ከተማ ስልጠናውን የተከታተሉ ሰልጣኞችም የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከቴክኖሎጂ ጋር በቀላሉ እንዲላመዱ እንዳገዛቸው ለኢዜአ ገልጸዋል።

የከተማዋ ነዋሪ ወጣት በረከት አባይነህ በኢትዮጵያ ኮደርስ ስልጠና ከተካተቱ አራት ኮርሶች ሙሉውን በማጠናቀቅ ሰርተፊኬት መውሰዱን ገልጿል።

በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ፣ በፕሮግራሚንግ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የስልጠና መስኮች በቂ ዕውቀት ማግኘቱን ተናግሯል።

የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከቴክኖሎጂ ጋር በቀላሉ እንዲላመዱ እንዳገዛቸው የገለፀችው ደግሞ ወጣት ምህረት ፍሬው ናት።

ከፕሮግራሚንግ በቀር ሦስት ኮርሶችን በማጠናቀቅ ሰርተፊኬት መውሰዷን ገልፃ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወጣቱን የዲጂታል ክህሎት በእጅጉ የሚያሳድግ ጠቃሚ ስልጠና መሆኑን ተናግራለች።

የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ከፍታ ለመረዳት ያስችላል ያለው ደግሞ ወጣት በቃሀኝ ጥላሁን ነው።

በወሰዳቸው የፕሮግራሚንግ እና የዳታ አናሊስስ ስልጠናዎች ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ መጠቀም የሚያስችለውን የዲጂታል ዕውቀት ማሳደግ መቻሉን ገልጿል።

መንግስት እንዲህ አይነት ጠቃሚ ስልጠናዎችን በነፃ በመስጠት ወጣቱን ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ የጀመረው ጥረት ይበል የሚያሰኝ መሆኑን አንስቷል።

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ዩኒት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ግርማ እንዳሉት በከተማ አስተዳደሩ በዘንድሮ ዓመት ከ4 ሺህ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል።

በስልጠናው ከተሳተፉት ውስጥ 3ሺህ 26 የሚሆኑት ስልጠናቸውን ሙሉ ለሙሉ አጠናቅቀው ሰርተፊኬት መውሰዳቸውን ጠቁመዋል። #ኢዜአ

‎"ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ለሀገራዊ ብልጽግና "
‎
‎ለወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
‎Telegram :-https://t.me/azitoTgroup
‎Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100088179777880
‎ = 0467751442
‎E-mail=[email protected]

🛰🚦🚥📌✈️🇪🇹 👉የኣሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት👈

‎የአሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይሄነው ተስፋዬ የስቅለትና ትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ‎‎ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳ...
10/04/2026

‎የአሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይሄነው ተስፋዬ የስቅለትና ትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
‎
‎ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና ትንሳኤ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
‎
‎በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን የስቅለትና የትንሳኤ በዓል አስመልክተው ለእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
‎
‎በመልዕክታቸዉም በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ፍቅርን የሰበከበት ስለሆነም በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን ወገኖችን በመርዳት፣ በመተጋገዝ እና እርስ በእርስ በመከባበር እንዲሁም ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር ሊሆን ይገባልም ብለዋል።
‎
‎በመጨረሻም በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
‎
‎"ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ለሀገራዊ ብልጽግና "
‎
‎ለወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
‎Telegram :-https://t.me/azitoTgroup
‎Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100088179777880
‎ = 0467751442
‎E-mail=[email protected]

🛰🚦🚥📌✈️🇪🇹 👉የኣሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት👈

የጂንካ ሚሊኒየም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ክበበብ የፈጠራ ስራዎችን በማቅረብ በዛሬው ዕለት ተከብሮ ውሏል።የኣሪ ዞን ሳይንስ እና ተክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይሄነው  እን...
06/04/2026

የጂንካ ሚሊኒየም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ክበበብ የፈጠራ ስራዎችን በማቅረብ በዛሬው ዕለት ተከብሮ ውሏል።

የኣሪ ዞን ሳይንስ እና ተክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይሄነው እንደተናገሩት ዓለም ወደ አንድ መንደር መምጣቷን ማሳያዎች መኖሩን አመላክተው መላው የትምህርት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቤተሰቦች በዛሬው ዕለት የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች ልደገፉ እና ልበረታቱ እንደምገባ እና ትላልቅ ተመራማሪዎች የሚወጡበት መማማሪያ መሆኑን አመላከቱ።

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ውባለም ገዛህኝ አለም የፈጠራ ውጤት ነች
የፈጠራ ስራዎች መነሻው ትምህርት በቶች እንደመሆናቸው የጂንካ ሚሊኒየም ተሞክሮ በማቅረብ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ መምህራን እና ተማሪዎች በተገኙበት እያከበረ መሆኑን አድንቀው ለሎች ትምህርት ቤቶች የጂንካ ሚሊኒየም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ተሞክሮ ልወስዱ እንደምገባ ተናገሩ።

ዘገባው የጂ.ከ.መ.ኮ

🛰🚦🚥📌✈️🇪🇹 👉የኣሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት👈

የጂንካ ሚሊንየም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ3ኛ ግዜ የሚከበረው  #የሳይንስ ሳምንት እነሆ ዛሬ ይከበራል።      መላው የትምህርት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቤተሰቦች ተጋብዛችኋል 🔬🔬🔬🔬🔬መጋቢት 2...
06/04/2026

የጂንካ ሚሊንየም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ3ኛ ግዜ የሚከበረው #የሳይንስ ሳምንት እነሆ ዛሬ ይከበራል።
መላው የትምህርት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቤተሰቦች ተጋብዛችኋል 🔬🔬🔬🔬🔬

መጋቢት 28/2018 ጂንካ💐💐💐💐

‎🛰🚦🚥📌✈️🇪🇹 👉የኣሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት👈

በአሪ ዞን ሁለተኛ ዙር የአንድ ጀምበር 100 ሺ የኮደርስ ምዝገባ የሚካሄደው አርብ በ 06/06/2018 ዓ ም በመሆኑ በበይነ መረብ ከወረዳዎች፣ ከተማ ፣ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ጋር ቅድመ ...
07/02/2026

በአሪ ዞን ሁለተኛ ዙር የአንድ ጀምበር 100 ሺ የኮደርስ ምዝገባ የሚካሄደው አርብ በ 06/06/2018 ዓ ም በመሆኑ በበይነ መረብ ከወረዳዎች፣ ከተማ ፣ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ጋር ቅድመ ዝግጅት ላይ ውይይት ተደረገ።

ጥር 30/2018 ዓ.ም

===================
‎🛰🚦🚥📌✈️🇪🇹 👉የኣሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት👈

Address

Jinka
Jinka
06

Opening Hours

Monday 02:00 - 10:30
Tuesday 02:00 - 11:30
Wednesday 02:00 - 11:30
Thursday 02:00 - 11:30
Friday 02:00 - 11:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ari Zone Innovation and Technology Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share