Kibet Town Government Communication Affairs Office

Call Website

Kibet Town Government Communication Affairs Office ⏩እንኳን ወደ የተለያዩ ትኩስና ተአማኒነት ያላቸው ከተማዊ፣ ሀገራዊና ዓለምአቀፋዊ መረጃዎችን የሚያገኙበት ፔጃችን በሰላም መጡ⏪

የቅበት ከተመ መትንዳደሬ ወባጀ ጋር 4ለኜ ዉርት 30ለኜ ሴረኜ ቡልሻነከ አትዋስዶት ጀመረ!ህዳር 1/2019 የቅበት ከተመ መንግስት ተራከባትበቡልሻኒ የኩፋቾ አሳወ ያሱይ የቅበት ከተመ መትንዳ...
10/11/2026

የቅበት ከተመ መትንዳደሬ ወባጀ ጋር 4ለኜ ዉርት 30ለኜ ሴረኜ ቡልሻነከ አትዋስዶት ጀመረ!

ህዳር 1/2019 የቅበት ከተመ መንግስት ተራከባት

በቡልሻኒ የኩፋቾ አሳወ ያሱይ የቅበት ከተመ መትንዳደሬ ወባጀ ጋር ቡር አፈ-ቡልሻን የሁርሚቴ የስርሞሎ ዘህራ ወባጀ ጋሪ የአትኬዋኚ ቃምቸ የ2019 ያፍቴ ቂንጥ አይዶ የዉጥን ተረሻት ብል ሃለት በሱት ተረሶተከ በትክታተሎት ዋ ኡግዠ ባሶት ሂንኩምንገ የኡመተይ የፈየ መትንዳደሬ ሱል ጀዋብ ኢረክባነኮ ላሶት ዋ ቡንዱሉሌም ኡመቲ ተምካት እትጋፈራነኮ የገገከ አትዋጫት ቲያሽ ንበሮተከ ጬቀሞን።

በቡልሻኒ የከተማይ የአትኬዋኚ ክትበት ጋርቸ ዮ2019 በጀት ዘማን ያፍቴ ቂንጥ አይዶ ውጥን ተረሻት የከተማይ ተኬታይ ከንቲበዋ የመስኒጃ ጋር ቡር ወሻይብ የዲላላ ቀድሩ ባቅረቦት ደር ኢትረከቦን።

ከዞን የመጣው ግብረ ሃይል የሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ከከተማው ንግድና ገበያ ልማት ባለሙያ ጋር የውጪ ኢንስፔክሽን አካሄደ-------------------------ጥቅምት 30/201...
09/11/2026

ከዞን የመጣው ግብረ ሃይል የሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ከከተማው ንግድና ገበያ ልማት ባለሙያ ጋር የውጪ ኢንስፔክሽን አካሄደ
-------------------------
ጥቅምት 30/2019: ቅበት ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን።
--------------------------
ከዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የመጣው ግብረ ሃይል የሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ከከተማው ንግድና ገበያ ልማት ባለሙያ ጋር በመሆን ከሕገ-ወጥ ንግድ፣ ከአዲስ ፍቃድ እንዲሁም ከፍቃድ እደሳ ጋር ተያይዞ ባደረገው የውጭ ኢንስፔክሽን ጉድለት የተገኘባቸውን 4 የንግድ ድርጅቶችን በማሸግ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ከዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የመጣው የኢንስፔክሽን ቡድን አጠቃላይ በዉጭ የመስክ እንዲሁም በጽህፈት ቤቱ በሩብ ዓመቱ የተሰሩ የዉስጥ ስራዎችን በማየት በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎችን ላይ የጋራ ማድረግ ስለመቻሉ ነው የተገለጸው።

የኢንስፔክሽን ቡድኑ የተለያዩ ድርጅቶችን ተዘዋውሮ የተመለከተ ሲሆን በህገ ወጥ መልኩ የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስቧል።

በተጨማሪም የኢንስፔክሽን ቡድኑ በተቋምና በውጪ በታዩ ክፍተቶች ዙሪያ የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ረዳት የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ሲቲ ጀማል በተገኙበት ግብረ መልስ ሰጥቷል።

በዚህም የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን ይበልጥ ለማስቀጠል እና የታዩ ጉድለቶችንና የአፈፃፀም ክፍተቶችን በዝርዝር በመለየት በቀጣይ ትኩረት በሚሹ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ መድረኩ ተጠናቋል።

በዚሁ መድረክ ላይ የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ረዳት የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ሲቲ ጀማል፣ የቅበት ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሰሚራ ሀሰን፣ የዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ባለሙያዎች እንዲሁም የጽህፈት ቤት ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

  የቅበት ከተመ መትንዳደሬ 4ለኜ ውሪት 30ለኜይ ሴረኜ ቡልሻን ጌስ መገርገበያ በአያም 1/03/2019 ቶ.ኢ ኢትረሻነኮ የቅበት ከተመ መትንዳደሬ ወባጀ ጋር አቻለ። ---------------...
09/11/2026



የቅበት ከተመ መትንዳደሬ 4ለኜ ውሪት 30ለኜይ ሴረኜ ቡልሻን ጌስ መገርገበያ በአያም 1/03/2019 ቶ.ኢ ኢትረሻነኮ የቅበት ከተመ መትንዳደሬ ወባጀ ጋር አቻለ።
--------------------------
ጥቅምት 30/2019 ቅበት ከተመ መንግስት ተራከባት
----------------------------
በስልጤ ዞን የቅበት ከተመ መትንዳሬ የ4ለኜ ውሪት 30ለኜ ሴረኜ ቡልሻን ጌስ መገርገበያ በአያም 1/03/2019 ቶ.ኢ ኢትረሻነኮ የወባጀ ጋሪ ቡር አፈ ቡልሻን የሁርሚቴ የስርሞሎ ዛህራ አቻሎን።

በቡልሻኒ የ2019 በጀት ዘማን የ1ለኜ ቂንጥ አይዶ የአትኬዋኚ ሴክተርቸ ውጥን ተረሻት ሪፖርትዋ የከተመ መትንዳደሬይ የ2019 በጀት ዘማን የ2ለኜ ቂንጥ አይዶ የብል ውጥን ኢቀርባነኮ ቴወዳን።

በድባያም ሉላሉሌ ሹመትቸ ኢሰብቶነምኮ ኢትቄራን።

የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ-------------------------ጥቅምት 30/2019: ቅበት ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን።------...
09/11/2026

የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ
-------------------------
ጥቅምት 30/2019: ቅበት ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን።
--------------------------
የቅበት ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃሊያ ጉባኤ በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

በመድረኩ የቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መሀመድ ኑራቶ፤ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ተቋም፤ የማህበረሰባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና እኩልነት ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ እና የማይተካ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።

የሴቶችን እና ህጻናትን ሁለንተናዊ መብት ከማስከበር ባለፈ በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ የሁልጊዜም ማዕከላዊ ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ዋና የመንግስት ተጠሪው አጽንኦት ሰጥተዋል።

አቶ መሀመድ አክለውም የሴቶችን አደረጃጀት ወደ ተግባር በማስገባት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በተለይ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ማህበራዊ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ተጠቃሚነት ሙሉ በሙሉ እንዲረጋገጥ ከመንግሥት ጎን ለጎን ባለድርሻ አካላትና መላው ማህበረሰብ የተናበበ፣ የነቃ እና የተጠናከረ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው ዋና የመንግስት ተጠሪው አሳስበዋል።

ባለፈው ዓመት የታዩ አበረታች ጠንካራ ሥራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል፣ በዕቅድ አፈጻጸም እና በቅንጅት ስራዎች ላይ የታዩ ክፍተቶችን በቁርጠኝነት በማረም ወደፊት በጠንካራ ዝግጅት እና በላቀ ውጤት መጓዝ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የቅበት ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ነስሪያ ሰብሎና፤ ጽህፈት ቤቱ ባለፈው ዓመት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት፣ ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች በዝርዝር የያዘ ሪፖርት አቅርበዋል።

ኃላፊዋ ሴክተሩ በተለይ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ሴቶችን በኢኮኖሚ የማብቃት፣ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ እናቶችን የመደገፍ፣ እንዲሁም የህጻናትን መብትና ደህንነት የመጠበቅ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

በተለይ በባለፈው ዓመት የ3450 ሴቶችን ጥቅም የማስጠበቅ ስራ መሰራቱንም ወ/ሮ ነስሪያ ገልጸዋል።

የተጀመሩ የልማትና የድጋፍ ስራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ከተቋማትና ከግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር ያለው ቅንጅትና አሰራር በላቀ ደረጃ መከናወን እንዳለበትም አብራርተዋል።

በተያዘው በጀት ዓመትም በዕቅድ የተያዙ ዋና ዋና አበይት ጉዳዮችን ከግብ ለማድረስ አመራሩና ባለሙያው በቁርጠኝነት እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሠሩ ሀላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል።

በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊዎች በቀረቡት ሪፖርቶች እና አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ በቀጣይ በከተማው አጠቃላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የላቀ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ጠንካራ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በመጨረሻም ከተቋም የስራ ሀላፊዎች ጋር የግብ ስምምነት የተደረገ ሲሆን በ2018 በጀት አመት የተሻለ ለፈጸሙ ሴት ባለሙያዎች፣ ቀበሌዎች እንዲሁም ለሴክተሩ ስኬት ድጋፍ ላደረጉ ተቋማትና የልማት ድርጅቶች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።

የአርሶ አደሩን ህይወት በዘላቂነት ማሻሻል የሚቻለው ሁሉ አቀፍ በሆነ መልኩ የተቀናጀ የግብርና ልማትን ተግባራዊ ማድረግ ሲቻል መሆኑን ተገለፀ‎--------------------------ጥቅምት...
09/11/2026

የአርሶ አደሩን ህይወት በዘላቂነት ማሻሻል የሚቻለው ሁሉ አቀፍ በሆነ መልኩ የተቀናጀ የግብርና ልማትን ተግባራዊ ማድረግ ሲቻል መሆኑን ተገለፀ
‎--------------------------
ጥቅምት 30/2019: ቅበት ከተማ ኮሙኒኬሽን
‎--------------------------
‎''የተቀናጀ ግብርና ለዘላቂ ቤተሰብና ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የቅበት ከተማ አስተዳደር ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድረክ እና የ2019 በጀት ዓመት የቀጣይ ዋና ዋና ስራዎች የትኩረት አቅጣጫ ላይ የሚያተኩር መድረክ አካሂዷል።

ጽህፈት ቤቱ በዛሬው ዕለት ያካሄደው የንቅናቄ መድረክ፤ በበጀት ዓመቱ የሚተገበሩ የተቀናጀ ግብርና ልማት ስራዎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ መተግበር እንዲችል ለማስቻል በአሰራር ሂደቱ የጋራ መግባባት ለመፍጠር በማለም ነው።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የቅበት ከተማ አስተዳደር ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርዳው አሊ፤ በግብርናው መስክ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እንዲሁም የምግብ ዋስትናን በአስተማማኝ ደረጃ ለማሳደግ የተቀናጀ ግብርና ልማት ስራዎች ወሳኝነት ያላቸው ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
‎
‎ሀላፊው አያይዘው በተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎችን መስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ በመፍጠር፤ በእንስሳት ሀብት፣ በመስኖ፣ በቡናና ፍራፍሬ፣ በጃከፍሩትና ሌሎች ተግባራት ላይ ውጤታማ በመሆን አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
‎
‎እንደ ከተማ በንብ ሀብት ልማት እምቅ አቅም ያለ በመሆኑ ይህንን ሀብት በተገቢው በማልማት የማህበረሰቡን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ አርሶ አደሩ በበቂ ሁኔታ የእንስሳት ተዋጾዎችን ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ሊያሳድግ እንደሚገባ አቶ ይረዳው አስገንዝበዋል።

አሁን ላይ የግብርናው መስክ ከኋላ ቀርነት ተላቆ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ከማድረግ ጀምሮ ከተረጂነት የተላቀቀ ማህበረሰብ እንዲፈጠር በማድረግ ረገድ ተጨባጭ ውጤት‎ ማምጣት ይገባል ነው ያሉት ሀላፊው።
‎
‎የድህነታችን መንስኤ ያሉንን ጸጋዎች ለይቶና አልምቶ ወደ ሀብት መቀየር አለመቻላችን ነው ያሉት አቶ ይረዳው፤ የተቀናጀ ግብርና የቤተሰብ ብልጽግና ኢኒሼቲቭ ይህንን እሳቤ የሚቀይርና የመንግስትን መሠረታዊ አቅጣጫዎች መነሻ ያደረገ ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

ጎታች ከሆኑ አስተሳሰቦች ፈጥኖ በመውጣት በከተማው የሚገኙ ሁሉም ቀበሌያት የተቀናጀ የግብርና ተግባርን በአደረጃጀት በመምራት የግብርና ምርቶችን በማምረት ውጤታማ ስራ መስራት እንዳለባቸው ሀላፊው በንግግራቸው ወቅት አስቀምጠዋል።

‎የቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መሀመድ ኑራቶ፤ በበኩላቸው የተቀናጀ የግብርና ልማት የሚባለው የእንስሳት መንደርን መፍጠር፣ የወተትና የዶሮ መንደሮችን መፍጠር እንዲሁም በከተማው አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ነው ብለዋል።

በተቀረጹ ኢኒሼቲቮች አማካኝነት የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋም፣ በትምህርት ተቋማት እና በሌሎችም ላይ ከተሰራ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ዋና የመንግስት ተጠሪው አመላክተዋል፡፡

አቶ መሀመድ አክለውም በቀጣይ የመስኖ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሲሉም አትተዋል።

የአካባቢን ፀጋ አልምቶ ድህነትን ታሪክ ለማድረግ፣ ብልጽግናን በቤተሰብ ደረጃ በየደጁ እውን ለማድረግ የሚያስችል የተቀናጀ ግብርና የቤተሰብ ብልጽግና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ ሊሰራ እንደሚገም ነው ዋና የመንግስት ተጠሪው የገለጹት።

በአሁኑ ወቅት የደረሰውን የእህል ሰብል ሳይበላሽ በፍጥነት መሰብሰብ እንደሚገባ ያነሱት አቶ መሀመድ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካል የየራሱን ድርሻና ኃላፊነት በግንባር ቀደምትነት መወጣት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በሁሉም አካባቢዎች ወጥ በሆነ መልኩ የግብር ልማት ስራዎችን ከመፈፀም አንፃር የሚስተወሉ ክፍተቶችን በማረም በሁሉም አይነት የግብርና ልማት ስራዎችን በቁርጠኝነት ለመፈፀም ዝግጁ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የተቀናጀ ግብርና ለዘላቂ ቤተሰብ ብልፅግና በሚል የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድረክ ከመጀመሩ አስቀድሞ በአቶ ሙሰማ ረዲ እየለማ የሚገኘውን የጃክ ፍሩት ምርት የተጎበኘ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ ይህን ተሞክሮ በመውሰድ በጓሮ አምርቶ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያነሳሳ የመስክ ምልከታ ነው ተብሏል።
‎
በመጨረሻም ከተቋሙ ባለሙያዎች ጋር የግብ ስምምነት በማካሄድ መድረኩ ተጠናቋል።

በመድረኩ የቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ መሀመድ ኑራቶ፣ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ዛሃራ ስርሞሎ፣ የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የመንግሥት ረዳት ተጠሪዎች ወ/ሮ ሲቲ ጀማል እና አቶ ከይረዲን ሙስጠፋ፣ የተቋም የስራ ሀላፊዎች፣ የቀበሌ አመራር እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ --------------ጥቅምት 30/2019: ቅበት ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን።-----------...
09/11/2026

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ
--------------
ጥቅምት 30/2019: ቅበት ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን።
--------------
የቅበት ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃሊያ ጉባኤ እያካሄደ ነው።

ለመድረኩ የተዘጋጀው ሰነድ በቅበት ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ነስሪያ ሰብሎና እየቀረበ ይገኛል።

መድረኩ በቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ መሀመድ ኑራቶ እየተመራ ነው።

በመድረኩ የቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ መሀመድ ኑራቶ፣ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ዛሃራ ስርሞሎ፣ የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የመንግሥት ረዳት ተጠሪዎች ወ/ሮ ሲቲ ጀማል እና አቶ ከይረዲን ሙስጠፋ፣ የተቋም የስራ ሀላፊዎች፣ የቀበሌ አመራር እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

በዝርዝር ዘገባ እንመለሳለን........

የተቀናጀ ግብርና ለዘላቂ ቤተሰብና ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የቅበት ከተማ አስተዳደር ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድረክ እና የ2019 በጀት ዓመት የቀጣይ ዋና ዋ...
09/11/2026

የተቀናጀ ግብርና ለዘላቂ ቤተሰብና ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የቅበት ከተማ አስተዳደር ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድረክ እና የ2019 በጀት ዓመት የቀጣይ ዋና ዋና ስራዎች የትኩረት አቅጣጫ ላይ ያተኮረ መድረክ እየተካሄደ ነው
--------------------------
ጥቅምት 30/2019፡ ቅበት ከተማ ኮሙኒኬሽን
---------------------------
ለመድረኩ የተዘጋጀው ሰነድ በቅበት ከተማ አስተዳደር ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ይረዳው አሊ እየቀረበ ይገኛል

መድረኩ በቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ መሀመድ ኑራቶ እየተመራ ነው።

በመድረኩ የቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ መሀመድ ኑራቶ፣ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ዛሃራ ስርሞሎ፣ የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የመንግሥት ረዳት ተጠሪዎች ወ/ሮ ሲቲ ጀማል እና አቶ ከይረዲን ሙስጠፋ፣ የተቋም የስራ ሀላፊዎች፣ የቀበሌ አመራር እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

በዝርዝር ዘገባ እንመለሳለን........

በቅበት ከተማ አስተዳደር  01 ቀበሌ እየለማ የሚገኘው የጃክ ፍሩት ማሳ በባለድርሻ አካላት ተጎበኘ፦ ጥቅምት 30/2019 የቅበት ከተማ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በቅበት ከተማ አስተዳደር  01 ...
09/11/2026

በቅበት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ እየለማ የሚገኘው የጃክ ፍሩት ማሳ በባለድርሻ አካላት ተጎበኘ፦

ጥቅምት 30/2019 የቅበት ከተማ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን

በቅበት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ በአቶ ሙሰማ ረዲ እየለማ የሚገኘውን የ ጃክ ፍሩት ማሳ በባለድርሻ አካላት ተጎብኝቷል።

የተቀናጀ ግብርና ለዘላቂ ቤተሰብ ብልፅግና በሚል የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድረክ ከመጀመሩ አስቀድሞ የተደረገው ይህ ጉብኝት የአካባቢው ማህበረሰብ በጓሮ አምርቶ ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ ይህንን ተሞክሮ ወስዶ ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

አቶ ሙሰማ ረዲ ከዚህ ጎን ለጎን የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞችን የሚያፈሉ ሲሆን ለአካባቢው ነዋሪዎችና ለሌሎች አርሶ አደሮች የተሻሻሉና ምርታማ የፍራፍሬ ችግኞችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ መንገድ ይከፍታል።

በቅበት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ የፍራፍሬዎች ንጉስ የሆነው የጃክፍሩት እየለማ መሆኑ ተገለፀ ጥቅምት 29/2019 የቅበት ከተማ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን በቅበት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ...
08/11/2026

በቅበት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ የፍራፍሬዎች ንጉስ የሆነው የጃክፍሩት እየለማ መሆኑ ተገለፀ

ጥቅምት 29/2019 የቅበት ከተማ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን

በቅበት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ በአቶ ሙሰማ ረዲ መኖሪያ ቤት ውስጥ እየለማ የሚገኘው የጃክ ፍሩት ለሌሎች ነዋሪዎችና ለከተማ ግብርና መስፋፋት እንደ ትልቅ ምርጥ ተሞክሮ የሚወሰድ ነው።

በከተማ ውስጥ ባለ ጠባብ የመኖሪያ ቤት ግቢ፣የጓሮ ቦታ በመጠቀም ጠቃሚና ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ የፍራፍሬ ዝርያ ማልማት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ መሆኑ ተጠቅሷል።

የአካባቢው ነዋሪዎችና ሌሎች አርሶ አደሮች ከአቶ ሙሰማ ግቢ በመነሳት የጃክፍሩት ፍራፍሬን እንዴት ማልማትና መንከባከብ እንደሚቻል በተጨባጭ የሚማሩበትና ልምድ የሚቀስሙበት መሆኑም ተገልጿል።

ልማቱ ለቤተሰብ የተመጣጠነ ምግብ ከማቅረብ ባለፈ፣ ለከተማ ነዋሪዎች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መፍጠር እንደሚቻል የሚያረጋግጥ ህያው ማሳያ መሆኑ ተመላክቷል።

በ2018 በጀት ዓመት 4 አዳዲስ ጤና ጣቢያዎችን፣ 3 ሁላቀፍ ጤና ኬላዎችንና 3 የማህበረሰብ  መድሃኒት ቤቶችን ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፦ አቶ ሸምሱ ሀይረዲንጥቅምት 29/2019 ቅበት ከተ...
08/11/2026

በ2018 በጀት ዓመት 4 አዳዲስ ጤና ጣቢያዎችን፣ 3 ሁላቀፍ ጤና ኬላዎችንና 3 የማህበረሰብ መድሃኒት ቤቶችን ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፦ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን

ጥቅምት 29/2019 ቅበት ከተማ ኮሙኒኬሽን)

"ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ የ2018 ዓመታዊ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

የመድረኩን ማስጀመሪያ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን በመልዕክታቸው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አራት ዋና ዋና ግቦች ተቀምጠው ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰዋል።

በዚህምሁለንተናዊ የጤና ሽፋንና ተደራሽነትን ማፋጠን ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ መሰራቱን ሀላፊው ተናግረዋል።
በሂደቱም ማህበረሰቡን በተለይም እናቶችን እና ህፃናትን ተጠቃሚ ያደረጉተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል።

የመንግስትንና የማህበረሰብን ሀብት አስተባብሮ ከ215 ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ 4 አዳዲስ ጤና ጣቢያዎች፣ 3 ሁላቀፍ ጤና ኬላዎችና 3 ማህበረሰብ አቀፍ መድሃኒት መደብሮች እንዲሁም 2 የኦፕራሲዮን አገልግሎት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን የመምሪያ ሀላፊው አብራርተዋል።

በሌላም በኩል በ34 ጤና ጣቢያዎች አልትራሳውንድ በማሟላት ከ42 ሺህ በላይ የሚሆኑ እናቶች አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በተያያዘም የክትባት ሽፋንን በማሳደግ ኩፍኝና የመሳሰሉ ወረርሽኞችን ማስቀረት መቻሉን እንዲሁም በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ከ210 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ በክለል ደረጃ ግንባር ቀደም ስራ መሰራቱን አቶ ሸምሱ አስታውቀዋል።

ይሁን እንጂ ከተገኙ ስኬቶች ጎን ለጎን ልዩ ትኩረት የሚሹ የአፈጻጸም ልዩነቶችና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መኖራቸውን መምሪያ ሀላፊው ተናግረዋል።

መጸዳጃ ቤቶችን በአግባቡ ከመጠቀም አንፃር ክፍተቶች መኖራቸውን፣ የአምቡላንስ አጠቃቀም ላይ ከድንገተኛ እና ከእናት አገልግሎት ውጭ ለሌላ ጉዳይ የማዋል እንዲሁም የጥገና ችግሮች ሊፈቱ ከሚገቡ ውስንነቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የመድሃኒት አቅርቦት፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ላይ በርካታ የማህበረሰቡ ቅሬታዎች መኖራቸውን ያነሱት ሀላፊው የወባ በሽታ መከላከል ስራዎች የተሻለ ለውጥ 45% መሻሻል ቢያሳይም ልዩ ትኩረት እንደሚፈልግ አመላክተዋል።

በተያያዘም የጤና ተቋማት ቦርድ ውይይቶች እና የህዝብ ፎረሞች አፈፃፀም ላይ የሚስተዋሉ ድክመቶችን መቅረፍ እንደሚገባ መምሪያ ሀላፊው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ስልጤ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን)

Address

Silte Zone Kibet Ketema Astedader
Kibet

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 10:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251954201649

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kibet Town Government Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share