Masha Woreda Communication

Masha Woreda Communication የማሻ ወረዳ እምቅ ሀብቶቻችንን በጋራ እናልማ
https://t.me/Mashawordacom

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ያቀረቡት ስምንቱ የ2019 ዓ.ም ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፡-...
06/10/2026

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ያቀረቡት ስምንቱ የ2019 ዓ.ም ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፡-

👉 ሰላምና ሕብረት፡- ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሕብረትን፣ ትብብርን እና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር ማከናወን

👉 መዋቅራዊ ሽግግር፡- ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር ማምጣት

👉 ዜጋ ተኮር ልማት፡- ምርት፣ ጤና እና ማኅበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከል ያደረገ ልማት ማፋጠን

👉 አቅም ግንባታ፡- ለዕድገት ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንዱስትሪና የግብርና ግብዓቶች፣ እንዲሁም በዘመናዊ መሠረተ ልማት ግንባታ ራስን የመቻል አቅም መገንባት

👉 የፕሮጀክት አፈጻጸም፡- የፕሮጀክት እና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈጻጸምን ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ተጠያቂነት ያለው ማድረግ

👉 የታክስ እና ዕዳ አስተዳደር፡- የታክስ መሠረትን ማዘመን፣ የመንግሥት ገቢ እና ወጪን መቆጣጠር እና ዕዳን በአግባቡ ማስተዳደር

👉 የሥራ ቅንጅት፡- በፌዴራል መንግስትና በክልሎች መካከል ያለውን የስራ ቅንጅትና አፈጻጸም የተባበረ፣ የተደጋገፈ እና ቀልጣፋ ማድረግ

👉 ቀጣናዊ ትስስርና ዲፕሎማሲ፡- ለቀጣናዊ ሰላም እና ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር ቅድሚያ የሚሰጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቀባይነትን የሚያሳድግ የውጭ ግንኙነትን ማጠናከር

! ! !

የምክር ቤት አባላት ሰላም ማጽናትና ምርታማነትን ማሳደግ ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል - ፕሬዚዳንት ታዬ የምክር ቤት አባላት የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ማጽናት እንዲሁም ምርታማነትን ይበል...
06/10/2026

የምክር ቤት አባላት ሰላም ማጽናትና ምርታማነትን ማሳደግ ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል - ፕሬዚዳንት ታዬ

የምክር ቤት አባላት የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ማጽናት እንዲሁም ምርታማነትን ይበልጥ ማሳደግ ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።

የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የሁለቱ ም/ ቤቶች ተመራጭ አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

ፕሬዚዳንት ታዬ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ የምክር ቤት አባላት ሁለንተናዊ ዝግጅት የመረጣቸው ሕዝብ የሰጣቸውን አደራ የሚመጥን ብቻ ሳይሆን ወደ ከፍተኛ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ስለሆነም የምክር ቤት አባላት ቀዳሚ ትኩረት መልካም አስተዳደርን የሚያዘምን፣ የሀገራችን ኢኮኖሚ ይበልጥ ከፍ የሚያደርግና ምርታማነትን የሚያሳድግ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

በተጨማሪም የኑሮ ውድነትን የሚገራ፣ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በስፋት የሚዘረጋ እና የሕዝብን ሰላምና ደህንነት የሚያጸና መሆን አለበት ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የተወሰዱ ርምጃዎች ለቀጣይ አፈጻጸም ብርቱ መሠረቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።

ለአብነትም የኢትዮጵያ የግብርና ሥርዓት ይሻሻል ዘንድ በሥራ ላይ የዋሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂና የመስኖ መሠረተ ልማት፣ የማዕድን ሥራ፣ የቱሪዝም መዳረሻ መጠናከርና የዲጂታል መሠረተ ልማት ማደግን ጠቅሰዋል።

በተለያዩ ዘርፎች የመፈጸም አቅምና ልምድን በማዳበር በመንግሥትና በሕዝብ ትብብር የሚፈጸሙ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ይበልጥ ውጤታማ እየሆኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሀገራችንን የደን ሽፋን ጉልህ በሆነ መንገድ መጨመሩንና የኮሪደር ልማት በአጭር ጊዜ አስደናቂ ለውጥ ማምጣቱን ነው ያወሱት።

እነዚህና መሰል ሥራዎች በበርካታ አካላት አድናቆት ያተረፉና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ አብነት የሚነገርላቸው ስኬቶች መሆናቸውን አውስተዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

የምክር ቤት አባላት የተጣለባችሁ ሀገራዊና ሕዝባዊ ኃላፊነት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው - ፕሬዚዳንት ታዬ  የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት የተጣለባችሁ ሀገራዊ እና ሕዝባዊ ...
06/10/2026

የምክር ቤት አባላት የተጣለባችሁ ሀገራዊና ሕዝባዊ ኃላፊነት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው - ፕሬዚዳንት ታዬ

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት የተጣለባችሁ ሀገራዊ እና ሕዝባዊ ኃላፊነት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ የሁለቱ ምክር ቤት ተመራጭ አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

ስብሰባውን በይፋ ያስጀመሩት ፕሬዚዳንት ታዬ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋል፡፡

ተመራጮች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሕዝብን ይሁንታ አግኝተው የምክር ቤቶቹ አባል በመሆናቸውም የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ይህ ታላቅ ምክር ቤት የመንግሥት ስልጣን መሰረቱ እና ምንጩ የሰፊው ሕዝብ ይሁንታ እና ድምጽ እንደሆነ የሚረጋገጥበት ሕያው ማህተምና ምስክር መሆኑን አውስተዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች የምታከናውኗቸው ሥራዎች እና የምትደነግጓቸው ሕጎች ለዘመዊዋ ኢትዮጵያ የሥልጣን መንገድ በሕዝብ የይሁንታ ድምጽና ቅቡልነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ የተጣለበችሁ ሀገራዊና ሕዝባዊ ኃላፊነት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡

ስለዚህ የመረጣችሁ ሕዝብ ከአመኔታ ጋር ታላቅ አደራ የሰጣችሁ በመሆኑ ይህንን ኃላፊነተ በታላቅ አስተዋይነት፣ ጥበብ፣ ብልሃት እና ታታሪነት እንደምትወጡ የኢትዮጰያ ሕዝብ ያምናል ነው ያሉት፡፡

ሁለንተናዊ ዝግጅታችሁም ይህንን አደራ የሚመጥን ብቻ ሳይሆን ወደ ከፍተኛ ምዕራፍ የሚያሸጋገር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

06/10/2026
ሁለቱ ምክር ቤቶች ዛሬ የጋራ ስብሰባቸውን ያደርጋሉ***********************7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን...
06/10/2026

ሁለቱ ምክር ቤቶች ዛሬ የጋራ ስብሰባቸውን ያደርጋሉ
***********************

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ትላንት ማካሄዱ ይታወሳል።

በዚህም የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎቻቸውን በመሰየም ሥራቸውን የጀመሩ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟል።

የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ዛሬ ከደቂቃዎች በኋላ መካሄድ ይጀምራል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የኢፌዴሪ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ...
05/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የኢፌዴሪ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

👉 ዛሬ ከተማና ገጠሩ እየተቀየረ ነው፤

👉 ከተሞቻችን የዘመናዊ ከተማ መልክ ለመያዝ ጥረት ማድረግ ጀምረዋል፤

👉 ዛሬ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ውብ አበባ ተብላ ብትጠራ እውነታ እንጂ ሙገሳ ተደርጎ አይወሰድም፤

👉 መሶብ የኢትዮጵያን የአገልግሎት አሰጣጥ መልክ ሲያስተካክለው፤ ፋይዳ አዲሱን የዲጂታል ማንነት ሲያጠናክረው፤ የወንዝ ዳር ልማት የኢትዮጵያን የውኃ እሳቤ ሲቀይረው፤ የገበታ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን ነባር መልኮች በአዲስ መልክ ሲገልጡ በዓይናችን አይተናል፡፡

👉 የአዲስ አበባ ለውጥ የዓለም ጉባኤዎችን ኑ ወደኔ እያለ ሲጣራ፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የምርት ባህላችንን ሲያድሰው፤ የማዕድን ልማታችን ለዘመናት የወጪ ንግዳችንን በአጭር ጊዜ መብለጥ ሲችል ለመታዘብ በቅተናል፡፡

👉 እነዚህን ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

👉 ባለፉት ዓመታት የመጣንበት መንገድ እንደ ኮሪደር የተስተካከለ፤ እንደ ወንዝ ዳር ልማት ያማረ አልነበረም ብዙ ፈተናዎችን አልፈናል፡፡

👉 የኢትዮጵያ ለውጥ ያስደነገጣቸው አካላት በክፉ አይናቸው ያዩን ጀመር፡፡

👉 የችግኝ ዋርካ ከሆነች አንችላትም ብለው ሰጉ፤ ስለዚህ ባልበላው ጭሬ አፈሰዋለው በሚለው ደካማ መንገድ ተነሱ፡፡

👉 ከሮጠች አንይዛትም ብለው የመጨረሻውን ጥይታቸውን መተኮስ ጀመሩ፡፡

👉 ባዳና ባንዳ ለእኩይ ዓላማ ተባበሩ፤ ሀገር ሻጭና ሀገር በታኝ ቀብድ ተቀባበሉ፡፡

👉 በሰይፍም በሰልፍም፤ በውሸትም በሀሜትም፤ በተንኮልም በሽረባም ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉዟችን ሊያደናቅፉን መከራቸውን አዩ፤ ኢትዮጵያን ግን አልቻሏትም፤ አይችሏትም፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 7ኛው ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመንግሥት መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ዐቢይ ...
05/10/2026

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 7ኛው ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመንግሥት መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

በዚህ የ7ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ጉባኤ የመንግሥት መመሥረቻ ስብሰባ ላይ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

! ! !

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄ...
05/10/2026

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

በዚህም ወ/ሮ አየለች እሸቴን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

! ! !

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የምሥረታ ሥነ ሥርዓት (በምሥል) !  !  !
05/10/2026

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የምሥረታ ሥነ ሥርዓት (በምሥል)

! ! !

የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የተከበሩ ወሮ  ሙፈሪሃት ካሚል  አፈ ጉባኤ አድርጎ መረጠ የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት 7ኛው የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እ...
05/10/2026

የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የተከበሩ ወሮ ሙፈሪሃት ካሚል አፈ ጉባኤ አድርጎ መረጠ

የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት 7ኛው የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው ጉባኤ የተከበሩ ወሮ ሙፈሪሃት ካሚል አፈ ጉባኤ አድርጎ የመረጠ ሲሆን የተከበሩ አቶ ደስታ ሌዳሞ ደግሞ በምክትል አፈ ጉባኤነት መርጧል።

Address

Sheka Zone Masha Woreda Govt. Dep. T
Masha

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Masha Woreda Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share