14/08/2026
የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት ከነሐሴ11 -12/ 2018 ዓ.ም መደበኛ ጉባኤ እንደሚካሄድ የዞኑ አፈጉባኤ አስታውቋል።
የቤንች ሸኮ ዞን የዞኑ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ከነሐሴ11 -12/ 2018 ዓ.ም ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቁን የዞኑ ዋና አፈጉባኤ አስታውቋል።
በጉባዔውም፣ የዞኑ ምክር ቤት፣ የአስፈፃሚ አካላትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ፣የ3ቱም የመንግስት አካላት የ2019 ጠቋሚ ዕቅድና የ2019 ዓ.ም የዞኑ በጀት ቀርቦ እንደሚፀድቅ ጠቁመዋል።
አክለውም ሌሎች አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸውም የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ ጌዲዮን ኮስታብ ተናግረዋል።
በጉባኤው የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሴቶችና የወጣቶች ተወካዮች ፣ የዞን ሴክተር መስሪያ ቤት አመራሮች ፣የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በማሳተፍ በታላቅ ድምቀት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል ሲል የቤንች ሸኮ ዞን ኮምኒኬሽን ዘግቧል።