Ethiopian Embassy, Paris, France

Ethiopian Embassy, Paris, France

Partager

Welcome to the official page of the Ethiopian embassy in France!

Photos from Ethiopian Embassy, Paris, France's post 04/06/2026

Droit de réponse à France 24 : Retour sur les élections législatives en Éthiopie avec Sabine Planel



03/06/2026
Photos from Ethiopian Embassy, Paris, France's post 01/06/2026

በፈረንሳይ የ2ኛ ትውልደ ኢትዮጵውያን ተማሪዎች መማክርት ተመሠረተ

ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ/ም በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደ መርሐ ግብር፣ በፈረንሳይ ተወልደው በትምህርት ላይ የሚገኙ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የሚያልፉባቸውን የትምህርት እርከኖችን በስኬታማነት ማለፍ እንዲችሉ እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ የቀጣይ የትምህርት አቅጣጫ እንዲኖራቸው ማስቻልን ግቡ ያደረገ መማክርት ተመሥርቷል።

በዚሁ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት በፈረንሳይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርና በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ መድረኩን በንግግር የከፈቱ ሲሆን፣ በንግግራቸውም 2ኛ ትውልድ ተማሪ ዲያስፖራዎች የቀጣይ ሀገር ተረካቢ በመሆናቸው በእድገት ጉዟቸው በሚገጥማቸው የተለያዩ ጫናዎች የወደፊት የእድገት አቅጣጫቸው እንዳይሰናከል ማድረግ ከሁሉም የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን አስምረዋል። በመሆኑም ውጤታማ ትውልድ ለማፍራት ተማሪዎቹ በሚያልፉባቸው ወሳኝ የሕይወት ምእራፎች በስኬት እንዲያልፉ የሚያግዝና የሚከታተል አካል እንዲኖር ማድረግ የሚኖረው ሚና የማይተካ በመሆኑ ይህን ኃላፊነት የሚወስድ መማክርት ለመሰየም ሁነቱ እንደተዘጋጀ ገልጸዋል።

የሚመሰረተው መማክርት ተማሪዎችን፣ ወላጆችንና ስኬታማ ምሁራን ዲያስፖራዎችን የሚያቅፍና በመረዳጃ ላይ የተመሰረተ የእድገት ምዕራፎች ሽግግርን የሚያሳልጥ፣ እንዲሁም የሚገጥሙ ችግሮችን በቅርበት የሚያማክርና የርስ በርስ ትስስርን በማጠናከር የጎለበተ ትውልድ እንዲፈጠር የማስቻል ሚና እንዲወጣ ታሳቢ መደረጉን አሳውቀዋል።

አክለውም ይህን በትውልድ እጣፈንታ ላይ የሚሠራ ትልቅ ኃላፊነት በመውሰድ በሚመሰረተው መማክርት ውስጥ የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና ለመወጣት ፈቃደኛ ለሆኑ ወጣት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወላጆችና ምሁራንን አመስግነዋል።

በመድረኩ በዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ በምሁራንና ወላጆች መካከል የልምድ ልውውጥ የተካሄደ ሲሆን የልምድ ልውውጡን ተከትሎ የተናጥል ውይይት፣ ትስስርና ይፋዊ የመማክርት ምሥረታ ተከናውኗል።

01/06/2026

"ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

ኢትዮጵያዉያን ስለኢትዮጵያ ሞክረዉ ያላሳኩት አንዳችም አገራዊ ግብ የለም!!!

ግንቦት 24 /2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የሺህ ዓመታት የሥነ መንግሥት ልምምድ ያላት በጋራ ሀገር ያፀኑ የብዙኃን ሀገር ናት ፡፡ ይህ የዳበረ የታሪክ መሠረቷ ደግሞ አሁን ለጀመረችው የዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ ታላቅ አቅምና ጉልበት ሆኗታል፡፡

ኢትዮጵያውያን ወደ ዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ ከገቡ ጥቂት ዓመታት ተቈጥረዋል፡፡ በእነዚህ ጥቂት ዓመታት የዴሞክራሲ መርሖዎች ልምምድ በተግባር ተፈጥሯል፤ ነጻ እና ገለልተኛ የምርጫ አስፈጻሚ ተቋማት በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ እንደ ጅምር መሻሻል የሚገባቸው ሂደቶች የነበሩባቸው ምርጫዎችም ተካሂደዋል፤ ሂደቶቹም ከጊዜ ወደ ጊዜ በእጅጉ እየበሰሉና ጥራታቸውን እያሳደጉ መጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን በዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና ነጻ ምርጫ መንግሥታቸዉን ለመምረጥ ለወራት ፍጹም ዝግጅት አድርገዋል፡፡ በዛሬዉ ዕለት ደግሞ የዴሞክራሲ ሥርዐትን በፅኑ መሠረት ላይ ለማኖር በነቂስ ወትተው ድምፃቸዉን እየሰጡ ነው፡፡ በርካታ ሚሊዮኖች ድምፅ ለመስጠት በንቃት ተመዝግበዉ፤ ቊጥራቸዉ የበዛ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች አማራጭ ሐሳቦቻቸዉን በነጻነት ለሕዝብ አቅርበዉ ደማቅ የምረጡኝ ቅስቀሳ አድርገው፤ የምርጫ አስፈጻሚ እና ታዛቢ አካላት አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት በላቀ ደረጃ አጠናቅቀው ነው ለዛሬው የድምፅ አሰጣጥ የተደረሰው፡፡

እነሆ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ደርሶ ሚሊዮኖች እንደየአካባቢዉ ኹኔታ የጧት ውርጭ፣ ዝናብ እና የቀን የፀሐይ ሐሩር ሳይበግራቸዉ የቀጣይ አምስት ዓመታት መንግሥታቸዉን በነፃ ፈቃዳቸዉ ለመምረጥ በደስታ ወጥተዋል፡፡ ይህ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የሚሳተፉበት ምርጫ በምሥራቅ አፍሪካ የዴሞክራሲ ፀሐይን ይበልጥ የሚያደምቅ፤ አፍሪካዉያን የራሳቸዉን መንግሥት በራሳቸዉ ነፃ ፈቃድ የመምረጥ ሙሉ ብቃት እንዳላቸው የሚያሳይ፤ የኢትዮጵያውያንን የዴሞክራሲ እመርታ በዓለም አደባባይ የሚያበስር ታላቅ ክስተት ነው፡፡

ኢትዮጵያዉያን ስለኢትዮጵያ ሞክረዉ ያላሳኩት አንዳችም አገራዊ ግብ የለም፡፡ ዓድዋ ላይ ለወራት ተዘጋጅተዉ በአንድ ጀምበር የዓለምን ታሪክና ፖለቲካ የለወጠ ታሪካዊ ድል አስመዝግበዋል፤ ሕዳሴ ግድብ ላይ ለዓመታት ጥሪታቸዉን በፈቃደኝነት ለግሰዉ የዓባይን ተፋሰስ ጂኦ-ፖለቲካ የለወጠ ድንቅ ድል ዐውጀዋል፤ በአረንጓዴ ዐሻራ በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች ችግኝ በጋራ በመትከል የራሳቸዉን አረንጓዴ ክብረ ወሰን ደጋግመዉ አሻሽለዋል፤ በዘንድሮዉም ምርጫ በተመሳሳይ የላቀ ተነሳሽነት ለወራት ተዘጋጅተዉና አማራጮችን በሰፊው ሰምተዉ ለአፍሪካ ተምሳሌ የሚኾን ነፃና ሰላማዊ ተሳትፎ ለማብሰር ድምፅ መስጠት ጀምረዋል፡፡

ይህ የዜጎች ንቁ ተሳትፎ የሚታይበት ምርጫ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ሥርዐት ይበልጥ ወደላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር፣ የአፍሪካዉያንን ዴሞክራሲን የማጽናት አቅም በጉልህ የሚያሳይ ታላቅ ሚና አለው፡፡ “በዚህ ዕለት ወጥቼ በነፃነት መርጫለሁ!” እያሉ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ራሳቸዉ ኢትዮጵያውያን በኩራትና በባለቤትነት ስሜት የሚናገሩለት ትልቅ ምርጫ ነው፡፡ ለዚህም ነው ካርድ የወሰዱ ዜጎች ኹሉ በደስታና በነቂስ ወጥተው ድምፃቸዉን እየሰጡ የሚገኙት፡፡ ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው፡፡

ምርጫዋ ዴሞክራሲን ማፅናት፤ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግርን እውን ማድረግ፤ ዜጎች በነፃ ፈቃዳቸዉ መንግሥታቸዉን የመምረጥ ሉዓላዊነታቸዉን በተግባር ማሳየት፣ የዛሬዉ ምርጫ ግቦች ናቸው፡፡ ለዚህ ታሪካዊ ምርጫ መሳካት ድምፃቸዉን በመስጠት፣ ምርጫዉን በብቃት በማስኬድ፣ በመታዘብ እና ዜጎች በሰላማዊ ኹኔታ እንዲመርጡ በማድረግ ዴሞክራሲያዊነቱ እንዲረጋገጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያደረጉ ላሉ ኹሉ ታሪክ ሁልጊዜም በክብር ያስባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

30/05/2026

የ7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ መረጃዎች:-

1. ምርጫው ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ. ም. የሚካሄድ ሲሆን 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 871 መራጮች ተመዝግበዋል፣ ከ547 መቀመጫዎች በ501ዱ ምርጫ ይካሄዳል፣ ለተቀሩት 48 መቀመጫዎች አስቻይ ሁኔታ ተፈጥሮ ምርጫው ይካሄዳል፣

2.በአጠቃላይ 42 የአገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው ይወዳደራሉ፤

3. 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም 80 የግል እጩዎች በምርጫው ይወዳደራሉ፣

4. ፓርቲዎች በተደለደለላቸው የአየር ሰዓት 19 የክርክር መድረኮችን በአምስት ቋንቋዎች አካሂደዋል፤

5. ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከ250 ሺህ በላይ ተወካዮቻቸውን የምርጫውን ሂደት እንዲከታተሉ ይልካሉ፤

6. ለታዛቢነት የአፍሪካ ሕብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ተወካዮቻቸውን ልከዋል፤

7. የአፍሪካ ሕብረት 59 አባላት ያሉት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ እየተመራ ያሰማራል፣ ኢጋድ ደግሞ በቀድሞ የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዚደንት የሚመሩ 26 አባላት ያሉት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ያሰማራል፤

8. በሀገር ውስጥ የተደራጁ 55 የሲቪክ ማኅበራት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ገብተዋል፤ እነዚህ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች በ1 ሺህ 562 የምርጫ መታዘብ ስራ ይካፈላሉ፣ የምርጫውን ሂደት የሚዘግቡ 68 የመገናኛ ብዙሃን ይሰማራሉ፣

9. የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ለ33፣ በአፋር ለ32፣ በአማራ ለ130፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለ22፣ በማዕካላዊ ኢትዮጵያ ለ35፣ በድሬዳዋ ለ48፣ በጋምቤላ ለ14፣ በሐረሪ ለ3፣ በኦሮሚያ ለ179፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ለ56፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለ22 ክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ ተሰራጭቷል።

Photos from The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia's post 25/05/2026

La présidente du Conseil électoral national d'Éthiopie (NEBE), Melatwork Hailu, a porté à la connaissance des diplomates et des représentants des organisations internationales basés à Addis-Abeba aujourd'hui les préparatifs de la 7ème élection générale éthiopienne prévue pour le 1er juin 2026.

Photos from Ethiopian Embassy, Paris, France's post 22/05/2026

በዩኔስኮ እ.ኤ.አ. ሜይ 21 ቀን 2026 በተካሄደው የአፍሪካ ሳምንት ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ የሀገራችንን ባህላዊ አለባበስ እና የባህል ብዝሃነት በደማቅ ሁኔታ ለዓለም ማሳየት ተችሏል። በዝግጅቱ ላይ በ Dann ltd ፣ Asharo ፣ Zemenay ፣ Qena afrika ዲዛይነርስ እንዲሁም በሌሎች አማካኝነት የተለያዩ ብሔረሰቦችን ባህላዊ አልባሳት ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህል እና የፋሺን ውበት በሚያምር መልኩ ቀርበዋል።

ይህ ፕሮግራም በፓሪስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ዲፕሎማቶች እና ወጣቶች በአንድነት በመሳተፍ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሀብትና ብዝሃነት ለዓለም ያስተዋወቅ ድንቅ የባህል ትዕይንት ሆኗል።

በመጨረሻም ሜይ 22 ቀን 2026 በፈረንሳይ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ በፕሮግራሙ ላይ የሀገራችንን የባህል አልባሳትን በማስተዋወቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የAssociation Passerelle Ethiopie ቡድን አባላትን ወደ ኤምባሲው በመጥራት የምስጋናና የዕውቅና ፕሮግራም አዘጋጅተዋል::

Vous voulez que votre entreprise soit Service Du Gouvernement la plus cotée à Paris ?

Cliquez ici pour réclamer votre Listage Commercial.

Emplacement

Adresse

35, Avenue Charles Floquet
Paris
75007

Heures d'ouverture

Lundi 09:00 - 12:00
13:00 - 17:00
Mardi 09:00 - 12:00
13:00 - 17:00
Mercredi 09:00 - 12:00
13:00 - 17:00
Jeudi 09:00 - 12:00
13:00 - 17:00
Vendredi 09:00 - 12:00
13:00 - 17:00