The proposed U.S backed Ebola quarantine facility in Kenya faced opposition from Kenyan doctors, civil society groups, and legal organizations over biosecurity and public health concerns.
The Kenya Association of Physicians publicly opposed the facility, citing concerns about the Ebola strain involved and potential risks to local communities.
U.S. funding figures of about $13 million to $13.5 million
Reuters
Ethiopian Health professionals
page to voice for Ethiopian health professionals burning issues and general public health concerns
የተመረጠው ፓርቲ የመጀመሪያ የቤት ስራ ልሆን የሚገባው ጤና ስርዓቱን መታደግና የጤና ባለሙያዎችን ሞራል መገንባት ነው
02/06/2026
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች የ7 ወራት የዲዩቲ (የተረኝነት) ክፍያ ባለመከፈሉ ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ድምፃቸውን በሰላማዊ ሰልፍ እያሰሙ ይገኛሉ። የጤና ባለሙያ መብቱ ተከብሮ በሰላም ሲሰራ ነው የህዝብን ህይወት ማዳን የሚችለው! የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል።
ማንም ተመረጠ ማን የጤና ስርዐቱን ከውድቀት ታደጉ
ለአመታት የተወዘፈውን የዱይቲ ክፍያ ለባለሙያዎች ክፈሉ!!!
01/06/2026
ለዘንድሮ ምርጫ midwife and doctors should stay near to polling stations there is Precipitated labor thereby 😂😂🤔🤔🤔
የዛሬውን የምርጫ ጣቢያ Delivery report ሞሪኒንግ የሚያቀርቡት የምርጫ አስፈጻሚዎች ናቸው ወይስ ካድሬዎች ??😂😂😂😂🤔❤
01/06/2026
አበት ድራማ😂😂😂🤔🤔🤔🤔
እየመረጠች እያለ ምጧ የመጣው እናት…
ግንቦት 24/ 2018 ዓ.ም
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በመሳተፍ ላይ ሳለች በምጥ የተያዘችው ነፍሰ ጡር ድምጿን ሰጥታ ወደ ሆስፒታል አምርታለች።
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በነቂስ ወጥተው በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በከተማዋ ሜሪጆይ ህዳሴ ምርጫ ጣቢያ ድምጿን ለመስጠት የተገኘችው ወ/ሮ ማህሌት ወልዴ ለመምረጥ ተዘጋጅታ ሳለ ነበር ድንገት በምጥ የተያዘችው።
በዚህም ነዋሪዋ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት ይበጃል ለምትለው ተመራጭ ድምጿን ሰጥታ በአቅራቢያዋ ወደሚገኝ የጤና ተቋም አምርታለች።
31/05/2026
The escalating situation at is nothing short of heartbreaking.
The consecutive deaths of practicing healthcare professionals and bright young health science students have sent shockwaves through the community and the silence surrounding it is deeply concerning.
Those who step into a hospital to learn and to heal should never have to fear for their own lives.
We stand in solidarity with the grieving families and colleagues and we urgently call upon the administration and public health officials to address this crisis with the urgency, transparency and protective measures it desperately deserves.
Ethiopian Health professionals
😭😭😭😭RIP
31/05/2026
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ካምፓስ በደረሰ የቦንብ ጥቃት የሰው ህይወት አለፈ
ጎንደር፣ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም— በትናንትናው ዕለት ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ካምፓስ ውስጥ በደረሰ ድንገተኛ የቦንብ ጥቃት የሁለት ተማሪዎች ህይወት ማለፉንና ከ20 በላይ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
አደጋው የተከሰተው ትናንት ምሽት 2:00 ሰዓት አካባቢ፣ ተማሪዎች በካምፓሱ ዲኤስቲቪ (DSTV) መዝናኛ ስፍራ የፒኤስጂ (PSG) እና የአርሰናል (Arsenal) የእግር ኳስ ጨዋታ እየተመለከቱ በነበሩበት ወቅት ነው።
በስፍራው ላይ በተወረወረ ቦንብ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ተማሪዎች ህይወታቸው ወዲያውኑ ማለፉን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
የአደጋው ሰለባ የሆኑት ተማሪዎች አስክሬንም ወደ ቤተሰቦቻቸው ተሸኝቷል። በጥቃቱ ሳቢያ ከ20 በላይ ተማሪዎች የተለያዩ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
የተፈጠረው ይህ አሳዛኝ ክስተት በካምፓሱ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፣ የደህንነት አካላትም ጉዳዩን በተመለከተ አስፈላጊውን ምርመራ እያደረጉ እንደሚገኙ ይጠበቃል።
በአደጋው ህይወታቸው ላለፈው ተማሪዎች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን። ለተጎዱት ተማሪዎችም ፈጣን ምላሽና ሙሉ ጤና እንዲገጥማቸው እንመኛለን።
Viaጉርሻ page
RIP😭😭😭 Health professionals
31/05/2026
“ሙሉ ምርመራ ቢሰራልኝ በሰውነቴ ውስጥ ያለ ማንኛውም በሽታ በእርግጥ ይገኛል”
✅ እውነታ: ሁሉንም በሽታዎች የሚያገኝ አንድ ወይም “ሙሉ” የሚባል ምርመራ የለም። የሚያስፈልጉ ምርመራዎች በዕድሜ፣ በፆታ፣ በቤተሰብ የበሽታ ታሪክ፣ በሕይወት ዘይቤ እና ባሉ ምልክቶች መሠረት ይመረጣሉ።
⚠️ ይህ የተሳሳተ ግንዛቤ ለምን ይፈጠራል?
ብዙ ሰዎች “ሙሉ ምርመራ” የሚለውን ቃል ሲሰሙ በሰውነት ውስጥ ያለ ማንኛውም በሽታ በአንድ ጊዜ ሊገኝ ይችላል ብለው ያስባሉ።
❗ ነገር ግን በሕክምና ውስጥ “ሁሉንም የሚያገኝ” ምርመራ የለም።
ምርመራዎች የተለያዩ ዓላማዎች አሏቸው። አንዳንዶቹ ለተወሰኑ በሽታዎች ምልክት ለሚያሳዩ ሰዎች የሚደረጉ ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ምልክት ሳይኖር በሽታን ቀድሞ ለማግኘት የሚደረጉ ናቸው።
⚠️ “ሙሉ ምርመራ” የሚባሉ ፓኬጆች ምን ጉድለት አላቸው?
• ሁሉንም በሽታዎች አያገኙም
• አንዳንድ በሽታዎች በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ላይታዩ ይችላሉ
• አንዳንድ ውጤቶች የሌለ ችግር እንዳለ ሊያሳዩ ይችላሉ
• ተጨማሪ ወጪ፣ ጭንቀት እና አላስፈላጊ ምርመራዎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ
❗ አንድ የምርመራ ውጤት ኖርማል መሆኑ ሁልጊዜ ሙሉ ጤንነትን አያረጋግጥም።
የሕክምና ታሪክ፣ የሰውነት ምርመራ (physical examination) እና ተገቢ የሆኑ ላብራቶሪ ወይም የራዲዮሎጂ ምርመራዎች በአንድነት ሲታዩ ነው ትክክለኛ ግምገማ የሚደረገው።
✅ “ሙሉ ምርመራ ቢሰራልኝ በሰውነቴ ውስጥ ያለ ማንኛውም በሽታ በእርግጥ ይገኛል” የሚለው የተሳሳተ ግንዛቤ ነው። ጥሩ የጤና ምርመራ ማለት ብዙ ምርመራዎችን ማድረግ ሳይሆን ለእያንዳንዱ ሰው ተገቢ የሆኑ ምርመራዎችን በትክክለኛው ጊዜ ማድረግ ነው።
#የጤናግንዛቤ #ሙሉምርመራ #የጤናምርመራ
Dr Ermias Nigusie Balcha: MD , Internist
SPHMMC
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Website
Address
New Deldhi
Addis Ababa
