Adem aliyu

Adem aliyu

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Adem aliyu, Political Party, Hera Street, Jeddah.

Photos from Adem aliyu's post 25/04/2026

ብዙ ግዜ ሰሜን ሸዋ ላይ ስለምትገኘው ትንሿ መንደር ስጽፍ "ትንሿ ጋዛ" እላት ነበር።
በሰሜን ሸዋ ገርበ ጉራቻ መዳረሻ የምትገኘው እና ነዋሪዎቿም በቁጥር ከአምስት ሺህ የማያልፍ
ግና በሺህ የሚቆጠር ምስኪን መንገደኞች የሚገ ደሉ ባት ፣ ሾፌሮች ፣ መንገደኞች እርጉዝ እናት ፣ የ3 አመት ህጻን ታግተው ሚሊዮኖች የሚከፈልበት ፣ ከአመት በፊት በአንድ ቀን ሰማንያ ሰዎች ታግተው ሰማንያ ሚሊየን ብር የተጠየቀባት ። አንድም ቀን አጋቾች ግን ያልተያዙባት ስለ ትንሿ የ "አሊዶሮ" መንደር በተደጋጋሚ ጥያቄ አንስቸ ነበር ።

አሁን ምላሹ ግልጽ እየሆነ ነው ። ማን ያግታል ፣ ማን ባንክ ውስጥ ሆኖ ገንዘቡን ያዘዋውራል ፣ መረጃው እንዳይወጣ ማን እንዲያዘገይ ያደርጋል ከነ ስማቸው እንመጣባቸዋለን።
Viv Gumaa

25/04/2026

"ከበቡሽ" ብለን ያሾፍን ጊዜ ነበር አንዱን እግራችንን የቆረጡት!

ለየብቻ ነጣጥለው መብላት ሲጀምሩ ነበር እምቢ ማለት የነበረብን። ጀዋር መሀመድን በድቅድቅ ጨለማ ለማፈን እና ከተቻለም ለማስወገድ ሲንቀሳቀሱ ይሄ የማፊያ ድርጊት ነው፣ በወንጀል ተጠርጥሮም ከሆነ ህጋዊ ሥርዓትን ተከተሉ ማለት ሲገባን "ከበቡሽ" እያልን ዘመርን። የወገኖቻችን ደም ስላስቆጣን በባላንጣችን ላይ የሚወሰድ የትኛውንም እርምጃ ትክክል ሆኖ ታየን። የወቅቱ ስሜት መጪውን ዘመን ጋረደብን። በህግ አምላክ ብሎ ጩኸት ያሰማን ግለሰብ "ከበቡሽ" ብለን ስም አወጣንለት።

ማለት የነበረብን አስቸካኳይ ምርመራ ይደረግ፣ የህግ የበላይነት ይከበር፣ ጀዋር በግድያው እጁ ካለበት ይጠየቅልን፣ ፍትህ ይስፈን ነበር። ይሄን ብንል ኖሮ ለዛሬ እርሾ እናስተርፍ ነበር። የተወሰነው የማህበረሰብ ክፍል ዛሬ ላይ "እከሌን ባልወደውም የሚደርስበትን ግፍን ህገወጥ ተግባር እቃወማለሁ" ይል ነበር። አሁን እሰይ የሚለው ድምፅ ትናንት ከተከልነው ቂም በቀል አርግዞ ነው። ለእነ እንትና ሲመጡ እኛ ዘንድ የማይደርስ መስሎን ነበር።

አሁንም አልረፈድም: ህገወጥ ተግባር ሲፈፀም፣ በደል እና ግፍ ስናይ ነግ-በኔ እያልን እናውግዝ። በጋራ ድምጽ እናሰማ። ያኔ እንደ 3 በሬዎች ለየብቻ አይበሉንም። ከትናንት እንማር!"ከበቡሽ" ብለን ያሾፍን ጊዜ ነበር አንዱን እግራችንን የቆረጡት!

ለየብቻ ነጣጥለው መብላት ሲጀምሩ ነበር እምቢ ማለት የነበረብን። ጀዋር መሀመድን በድቅድቅ ጨለማ ለማፈን እና ከተቻለም ለማስወገድ ሲንቀሳቀሱ ይሄ የማፊያ ድርጊት ነው፣ በወንጀል ተጠርጥሮም ከሆነ ህጋዊ ሥርዓትን ተከተሉ ማለት ሲገባን "ከበቡሽ" እያልን ዘመርን። የወገኖቻችን ደም ስላስቆጣን በባላንጣችን ላይ የሚወሰድ የትኛውንም እርምጃ ትክክል ሆኖ ታየን። የወቅቱ ስሜት መጪውን ዘመን ጋረደብን። በህግ አምላክ ብሎ ጩኸት ያሰማን ግለሰብ "ከበቡሽ" ብለን ስም አወጣንለት።

ማለት የነበረብን አስቸካኳይ ምርመራ ይደረግ፣ የህግ የበላይነት ይከበር፣ ጀዋር በግድያው እጁ ካለበት ይጠየቅልን፣ ፍትህ ይስፈን ነበር። ይሄን ብንል ኖሮ ለዛሬ እርሾ እናስተርፍ ነበር። የተወሰነው የማህበረሰብ ክፍል ዛሬ ላይ "እከሌን ባልወደውም የሚደርስበትን ግፍን ህገወጥ ተግባር እቃወማለሁ" ይል ነበር። አሁን እሰይ የሚለው ድምፅ ትናንት ከተከልነው ቂም በቀል አርግዞ ነው። ለእነ እንትና ሲመጡ እኛ ዘንድ የማይደርስ መስሎን ነበር።

አሁንም አልረፈድም: ህገወጥ ተግባር ሲፈፀም፣ በደል እና ግፍ ስናይ ነግ-በኔ እያልን እናውግዝ። በጋራ ድምጽ እናሰማ። ያኔ እንደ 3 በሬዎች ለየብቻ አይበሉንም። ከትናንት እንማር!

23/11/2025

ኧረግ ኧረግ😅
ብርሃኑ ነጋ ለካ ከሂጃቡ ጉዳይ በተጨማሪ በዘመናይ ሴቶች በኩል ሶስተኛውን የአለም ጦርነት ሊያስነሳበት የሚችል መራራ አዋጅ አውጇል አሉ…አሁን አይደል እንዴ ልብ ያልኩት 😅

አዋጁ 👉 ሴቶች በትምህርት ቤት ውስጥ…አርተፊሻል ጸጉር የለ የሰይጣን ጥፍር የመሰለ ነገር መቀጠል የለ…ቅንድብ መቀንደብ የለ 2 ኪሎ ተኩል ዱቄት መሳይ ሜካፕ መደፍለቅ የለ 😅
በቃ እንዲሁ አላህ እንደሰራቸው ቋ ቀጭ እያሉ ይማሩ ዘንድ ታውጇል አሉ 🙎
👉አስባችሁታል በሜካፕ ደምቃና አሸብርቃ የምታውቋትና …ፐ… ይች ቆንጆ ልጅ ስታምር… ያላችሗት ልጅ

👉በዚህ አዋጅ የተነሳ የናይጀሪያን ደንብ አስከባሪ መስላ ብቅ ስትል 😒😅

21/10/2025

ወላህ አሁን አሁን የአማራ ክልልን ሁኔታ በተመለከተ የአንዳንድ የሙስሊም አክቲቪስቶች አካሄድ ምንም እየገባኝ አይደለም። በዚህ ሰዓት ክልሉ ጦርነት ላይ ነው። ማንም ተነስቶ የፈለገውን ማድረግ የሚችልበት ወቅት'ና ጊዜ ላይ ነን። እያየን ያለነውም ይሄኑ ነው !

ታዲያ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እውነት አማራ ክልል እየተገደለ ላለው ሙስሊሙ ያሰበ ሰው ከዚህ ሆኖ 'ፋኖ ገ ዳዩ ፣ ፋኖ አሸባሪው ፣ እኚ ነፍጠኛዎችን ልካቸውን ማስገባት ነው ፣ አማራ ብሄርተኝነት ሙስሊም ጠልነት....' ምናምን እያለ እንዴት ነገር ያባብሳል ? እንዴት በእሳት ላይ ነዳጅ ያርከፈክፋል ? የተፈለገው በክልሉ የሚኖረው ሙስሊም ምን እንዲሆን ነው ?

ሌላው ይቅር ጭራሽ ሙጂብን ለማድነቅ 'የቡዳ መድሃኒት...' ምናምን የሚል ቃል የምትጠቀሙ ሰዎች ምናችሁ ነው የሚያማችሁ ? ማን ነው ቡ ዳው ?

አረ ተው አስተውሉ ! እሺ ወይይ ማስተዋል ከከበዳችሁ ሌላውን ተዉትና እስኪ እዛ ክልል ላይ የሚኖሩ ሙስሊሞችን ለማናገር ሞክሩ !?

እንዴዴዴዴ አንድ ከሩቅ ቦታ ሆኖ ለታጋቾች ድምፅ እሆናለው የሚል ሰው አጋቾች ናቸው ያላቸውን ሰዎች የሚያበሳጭ ነገር ይናገራል ወይ ? ታዲያ የእናንተ ስራ የዚህ አይነት የሞኝ ተግባር ነው እኮ።

ነው በእናንተ እልህ ታጋቾቹ እንዲያልቁ ትፈልጋላችሁ ?

አረ አላህን ፍሩ። የእናንተን የበሰበሰ የፖለቲካ ዳቧችሁን በሙስሊሙ ደም ላይ አትጋግሩ። 'ለእናንተ እንጨነቃለን...' በሚመስል መልኩ የአማራ ክልል ሙስሊምን ሌላ አጣብቂኝ'ና መከራ ውስጥ አትጨምሩት። ያለበትን ጭንቀትና ስጋት ይበቃዋል !

ይልቅ ለሁሉም የሚሆን የተቋም (መጅሊስ) መስረተናል የተባለው ለዚህ ጊዜም ከሆነ ከክልሉ ሙስሊሞች'ና ከሌላ የእምነት ተቋም አመራሮች ጋር በመነጋገር ለዚህ ምስኪን ህዝብ መፍትሄ ይፈልጉለት !

የእናንተ በክልሉ ሙስሊሞች መገደል'ና መፈናቀል አስታካችሁ ከዚህ ሆናችሁ የምትሰነዝሩት ጥላቻ ግን ፣ እዛ ለሚኖረው ህዝብ መፍትሄ ሳይሆን መዘዝ ነው ይዞ የሚያመጣበት !

04/08/2025

ችግር የቱንም ያክል ተስፈ አስቆርጦ ላልተገቡ ውሳኔዎች ሊዳርጋችሁ ቢችልም፤ በተቻለ መጠን ለዱንያ ብላችሁ አጠራጣሪ በሆኑ መንገዶች አትጓዙ፤ ራሳችሁን ለአደጋ አታልጡ። ቤተሰብን እንረዳለን ብላችሁ ይበልጥ ቤተሰብን ለስቃይና ለሐዘን አትዳርጉ። አላህ ወጥቶ ከመቅረት ይጠብቀን፣ በሐላሉም ያብቃቃን።

01/08/2025

ልጅ እያለን ሚሪንዳ ሲገዛልን እናገኝ የነበረዉን ደስታ ግማሽ ያህሉን እንኳን ማግኘት እንዴት ይሳነናል? ማደግና ደስተኛ መሆን ነበር እኮ ህልማችን🥰

01/08/2025

ፀሀይ ከምትወጣበት ቀን ሁሉ ምርጡ የጁምአ ቀን ነው። አደም የተፈጠረበት፤ ጀነትም የገባበት ከሷም የወጣበት ቀን ነው። ሰአቷም(የፍርዱ ቀን) አትቆምም በጁምአ ቀን ቢሆን እንጂ!

ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም❤

31/07/2025

የተሰማው ከሆነው እጅግ በጣም ጥቂቱ መሆኑን እናውቃለን።

ይህን ከምን ጋር ታወዳድረዋለህ? ወደር ይገኝለታል ወይ? ከየት መጥቶ ወደር እና አቻ ይገኝለታል። ተመልከት ከዓለም ጥጋጥግ ተለምኖ እና ተሰብስቦ ከሚመጣው እርዳታ 0.1% የሚያኽለው ርሃብ ለሚያሳድዳቸው የጋዛ ሰዎቾ ቢደርስ’ንጂ ቀሪው በአውሬዎቹ መንገድ ላይ ተጠልፎ ይሰወራል። ተመልሶ ጠኔ ለጠለፋቸው ምስኪኖች በጣም በውድ ዋጋ ለገበያ ይቀርባል ይባላል። መቼስ መሸጥን የለመደ እዚህም በዚህም ከእነዚህም ትርፍ ያሰላል።

31/07/2025

ሰዎች ቢሳሳቱ እንኳን ክብራቸው ሊጠበቅ ይገባል። ክብር ሰው ሰው በመሆኑ ሊያገኘው የሚገባ ነው። ስራቸውን ማውገዝ አንድ ነገር ነው በሰው ክብር መረማመድ ግን ፈጽሞ ተገቢ አይደለም። አንድ ግለሰብ ተጠረጠረ ማለት በትክክል አድርጎታል ማለት አይደለም።
ቢያንስ ፍርዱ ከአላህ ሆኖ ሳለ ራሳችንን ፈራጅ አድርጎ ማስቀመጥና ፍትህን ወይም እውነትን በመፈለግ ስም ነፍስያን መከተል መጨረሻው ጸጸት ነው።

ዝም ያለ ነጃ ወጣ (ሱ.ዓ.ወ)

14/05/2025

አንዴ ጅማ ላይ አንዱ ሎተሪ ገዝቶ እንደ ጋዜጣ በሩ ላይ በማስቲሽ ይለጥፈዋል 😁

ከአንድ ወር በኃላ ይመስለኛል ቤቱ ተኝቶ ሬዲዮ እየሰማ የሁለተኛው እጣ ሎተሪ ባለእድል እስካሁን እንዳልተገኘና የእድል ቁጥሩን በተደጋጋሚ በመናገር ጋዜጠኞቹ ያስታውቃሉ።

ልጁ ከአንገቱ ቀና ብሎ በሩን ሲያይ የእሱ ሎተሪ እንደሆነ ያውቃል። ሎተሪውን ከበሩ ላይ ከላጠው ሊቀደድበት ነው ...በቅርፅ ቆርጦ ካወጣው ደግሞ ላይታመን ነው ..

አስቦ አስቦ በመጨረሻም ሙሉ በሩን ገንጥሎ በባጃጅ አስጭኖ ብሔራዊ ሎተሪ ይዞት ሄደ 😂😂

ምን ለማለት ፈልጌ ነው በጥንቃቄ ያልተያዘ ወይም በእጅህ በደንብ ያልያዝከው ጉዳይን በመጨረሻ ልታጣው ስትል እራስህን እንደ ተለጠፈው የበሩ ሎተሪ በመገንደስ መስዕዋት ከምታቀርብ .. ከመጀመሪያው በአግባቡ ይዘህ ብታስቀምጠው ጥሩ ነው ባይ ነኝ 😆 !!

Want your business to be the top-listed Government Service in Jeddah?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Hera Street
Jeddah