11/08/2016
Cultural Festival in Comboni College
Comboni College for Science and Technology (which is a private college in Khartoum) organized an "african cultural festival" from 6th -11th of August 2016 in the compound of the college.
Students from Sudan, Ethiopia, South Sudan and Eritrea (those attending their education in the college) are the top participants of the festival.
Ethiopian students colorfully presented the Ethiopian Culture during the festival.
08/08/2016
በሱዳን ካርቱም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተመሰረቱ ልማት ማህበራት የ2008 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ።
==========================================================
በሱደን በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተደራጁ 9 ልማት ማህበራት የሚገኙ ሲሆን፣ እነዚህም የአማራ፣ የትግራይ፣ የኦሮሚያ፣ የስልጤ፣ የከምባታ፣ የሀዲያ፣ የሀላባ፣ የጉራጌ እና የወላይታ-ዳውሮ-ጋሞጎፋ ልማት ማህበራት ናቸው።
በካርቱም የሚገኘው ኢፌዴሪ ኤምባሲ የልማት ማህበራቱን እንቅስቃሴ ቼክ ሊስት አዘጋጅቶ ክትትል የሚያደርግ ሲሆን፣ በ2008 በጀት አመት ያከናወኑትን የዕቅድ አፈጻጸም በቼክ ሊስቱ መሠረት ገምግሟል። የሁሉም ልማት ማህበራት አመራሮች በቼክ ሊስቱ እና በዓመቱ ለማከናወን በያዙት ዕቅድ መሠረት ባለፎ ሮቡዕ ሐምሌ 27 ቀን 2008 ዓ.ም ምሽት በኤምባሲው አዳራሽ ጠለቅ ያለ ግምገማ በማካሄድ አፈጻጸማቸውን በመመልከት የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡትን የስልጤ፣ የትግራይ፣ የሀላባ እና የከምባታ ልማት ማህበራት በA ደረጃ በማስቀመጥ በቅደም ተከተላቸው መሠረት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ የወጡ መሆናቸውን መለየት ተችሏል። እንዲሁም የአማራ፣ ኦሮሚያ እና የወላታ-ዳውሮ-ጋሞጎፋ ልማት ማህበራት በB ደረጃ የተቀመጡ ሲሆን፣ የጉራጌና የሃዲያ ልማት ማህበራት ደግሞ በC ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በአመቱ ከፍተኛ ውጤት ላሳዩት የስልጤ፣ የትግራይ እና የሀላባ ልማት ማበራት ኤምባሲው በደረጃቸው መሠረት ሽልማት ያበረከተ ሲሆን፣ እንዲዚሁም የከምባታ ልማት ማህበር ቀደም ሲል ፈርሶ ከነበረበት እንደገና በመደራጀት በ6 ወራት ብቻ የተሻለ ውጤት አስመዝግቦ በመገኘቱ ልዩ ሽልማት ተበርክቶለታል።
ልማት ማህበራቱ ማከናወን አለብን ብለው በዕቅዶቻቸው የያዟቸው፣ በኤምባሲው የመከታተያ ቼክ ሊስት ላይ የሰፈሩና ለግምገማው ጥቅም ላይ የዋሉት ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ማህበራቱ አዳዲስ አባላትን በመመልመል ከአባላት መዋጮ ማሰባሰብ፣ የተሰባሰበውን ገንዘብ በተገቢው መንገድ መያዝ፣
2. በሕገደንቡ መሠረት በቋሚ ፕሮግራሞች ስብሰባዎችን ማድረግ፣
3. አገር ቤት ካሉት እናት ማህበራት ጋር ትስስር በመፍጠር በአገር ልማት ላይ ተሳትፎ ማድረግ፣
4. በኤምባሲው በሚዘጋጁ አገራዊና ክልላዊ በዓላት ላይ እንዲሁም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ የፓናል ውይይቶች ላይ አባላትን በስፋት በማሳተ አባላቱ ስለአገራቸው በቂ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ ማድረግ፣
5. የታላቁ ህዳሴ ግድብ በቦንድ ግዥ፣ በስጦታ እና በተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ላይ አባላት እንዲሳተፉ በማድረግ አገር ልማት እንዲያግዙና ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ ማድረግ፣
6. በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በሕገ ወጥ በደላሎችና በሌሎች አካላት የሚደርስባቸውን ችግር አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ መፍታትና የሚያጋጥሟቸውን የመብት ጥሰቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መከላከልና ደላሎችን ማጋለጥ፣
7. የማህበራቱን አባላት እና ኢትዮጵያውያንን በአንድ ለአምስት አደረጃጀቶች እንዲታቀፉ በማድረግ ኢትጵያውያኑ እርስ በርስ እንዲረዳዱና ችግሮቻቸውን በጋራ እንዲፈቱ፣ የሚያጋጥሟቸውን የመብት ጥሰቶች በጋራ እንዲከላከሉ ማድረግ፣
8. ዕቅድ አውጥቶ በመንቀሳቀስና አፈጻጸም ሪፖርቶችን በየጊዜው ለምክር ቤቶቻቸውና ለመላው አባላት እንዲሁም ለኤምባሲው ማቅረብ ናቸው።
በዚሁ መሠረት ልማት ማህበራቱ ባደረጉት ንቁ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ውጤት የተገኘ ሲሆን የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፤ በአመቱ 2‚329 አዳዲስ አባላት ተመልመለዋል፣ ከአባላት መዋጮ እና በሌሎች ገቢ ማሰባሰቢያ ዘዴዎች 28‚200.00 የሱዳን ፓውንድ ተገኝቷል፣ ለክልል ልማት ድጋፍ ከአባላት መዋጮና ከሌሎች ገቢዎች በተወሰኑ ልማት ማህበራት ብቻ የተሰራ 72‚640.00 የሱዳን ፓውንድ ወደ አገር ቤት ተልኳል፣ 40‚000 የአሜሪካን ዶላር የሚጠጋ ቦንድ ግዥ ተፈጽሟል፣ የ341 ችግር ያጋጠሟቸው ኢትዮጵያውያን እገዛ ተደርጓል፣ በዚህም 51‚160.00 የሱዳን ፓውንድ የልማት ማህበራቱ በማዋጣት ዜጎችን ረድተዋል። ከዚህ ወጪ የልማት ማህበራት በሚያስተባብሯቸው ዕድሮች አማካይነት ሰፊ ስራ የተሰራ ሲሆን የዕድሮች አፈጻጸም በሌላ መድረክ የሚታይ በመሆኑ በዚህ አልተካተተም።
በግምገማው ወቅት የተወሰኑትን የልማት ማህበራት አባላት ማነጋገር የተቻለ ሲሆን፣ የአፈጻጸም ግምገማው መካሄዱ ልማት ማህበራቱ ጥሩ አፈጻጸም ካሳዩት ተሞክሮ ለመውሰድ፣ በአፈጻጸም ሂደት ያለባቸውን ደካማ ጎኖች በማሳየት ለቀጣይ የሚቀርፉበትን ሁኔታ እንደፈጠረ እና ከግምገማው በኋላ ለተሳተፎአቸው ለሁሉም ልማት ማህበራት የማበረታቻ ሰርቲፊኬት መሰጠቱ እና የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩት ሽልማት መሰጠቱ በቀጣይ በመልካም ውድድር መንፈስ ወደ ስራ ለመግባት ጥሩ ስሜት የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
አጠቃላይ የልማት ማህበራቱ እንቅስቃሴ በሱዳን የሚኖሩ ዜጎቻችንን የሚያጋጥሟቸውን በርካታ ችግሮች በመተጋገዝ ለመፍታትና እርስ በርስ ለመደጋገፍ፣ በደላሎችና በሌሎች የሚደርስባቸውን የመብት ጥሰቶች ለመከላከልና ሕገወጦችን በማጋለጥ ለፍርድ እንዲቀርቡ ለማድረግ፣ በግንዛቤ እጥረት ለችግር የሚጋለጡ ዜጎችን ግንዛቤ በማሳደግ ችግሮችን ለመቀነስ፣ በአገር ቤት ያለውን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ በውል ተገንዝበው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ብሎም አቅማቸው የቻለውን ያህል በአገር ልማት ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል ጠቃሚ በመሆኑ ይህንን ይበልጥ አጠናከረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን አንዳንድ የልማት ማህበራቱ አባላት ገልጸዋል።
02/08/2016
አምባሳደር ፍሰሀ ሻዎል በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለዲፕሎማቶች ገለፃ ሰጡ፣
በጁባ የኢፌዲሪ ኤምባሲ አምባሳደር ፍሰሀ ሻዎል የJMEC ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ካርቱም በመጡበት ወቅት በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እና የስብሰባው ውጤት ዙሪያ ለካርቱም ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ገለፃ አድርገዋል።
22/07/2016
የኢፌዲሪ ካርቱም ኤምባሲ ሰራተኞች በኤምባሲው የ2009 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አደረጉ፣
======================================================================
የኢፌዲሪ -ካርቱም ኤምባሲ ሰራተኞች በኤምባሲው የ2009 በጀት ዓመት ውጤት ተኮር ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱን የመሩት በሱዳን የኢፌዲሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አባዲ ዘሞ እንዳሉት የኤምባሲው ዕቅድ የተዘጋጀው የ2008 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እንደ መነሻ በመውሰድ፣ እንዲሁም የአገራችን እና የሱዳንን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገባ እንደሆነ ገልጸዋል።
በ2008 በጀት ዓመት የነበሩ ጥንካሬዎችን በማጎልበትና ድክመቶችን በማረም በ2009 በጀት ዓመት ዕቅድ ተፈጻሚ እንዲሆን የሁሉም ሰራተኞች ሚና ትልቅ መሆኑ ከመግባባት ተደርሷል።
መልካም የስራ ዘመን!
06/07/2016
በካርቱም የኢፊዲሪ ኤምባሲ የ2008 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መዝግያ ስነ ስርዓት ተካሄደ፣
=====================================================================
በካርቱም የኢፊዲሪ ኤምባሲ የ2008 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መዝግያ ስነ ስርዓት አካሂዷል።
በፕሮግራሙም ሁሉም የኤምባሲው ሰራተኞች በተገኙበት ከሎካል ሰራተኞች መካከል በስራ አፈጻጸማቸው እና በሌሎች ተያያዥ መስፈርቶች የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ ሰራተኞች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር አባዲ ዘሞ በስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ኤምባሲው የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ የሎካል ሰራተኞች አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር በመናገር፣ ዛሬ በስራቸው የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ስራተኞች የማበረታቻ ሽልማት ስሰጥ በቀጣይ ሁሉም ሰራተኞች የተሻለ ስራ ለማስመዝገብ እንዲጥሩ፣ እንዲበረታቱ ለማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል።
ተሸላሚ ሰራተኞችም ዛሬ በተሰጣቸው ሽልማት እንደተደሰቱና በቀጣይ ከአሁኑ በተሻለ ለመስራት ሞራል እንደሚሆናቸው ገልጸዋል።
06/07/2016
በካርቱም የኢፊዲሪ ኤምባሲ ሰራተኞች በኤምባሲው ዓመታዊ የስራ ክንውን ላይ ውይይት አካሄዱ፣
================================
በሱዳን፣ ካርቱም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ሰራተኞች በኤምባሲው የ2008 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት አድርጓል።
የኤምባሲው በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በተወሰኑት ተግባራት አካባቢ ከታየው ዝቅተኛ አፈጻጸም በስተቀር በአጠቃላይ ሲታይ የተሻለ አፈጻጸም እንደነበር ተገምግሟል።
05/07/2016
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
01/07/2016
በካርቱም የኢፌዲሪ ኤምባሲ ዲፕሎማት በክበር ተሸኙ፣
================================
በካርቱም የኢፌዲሪ ኤምባሲ ላለፉት አራት ዓመታት በዲፕሎማትነት ደረጃ በትጋትና በታማኝነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አረጋ ካሳ በኤምባሲያችን የነበራቸው አገራዊ ተልእኮ አጠናቅቀው ወደ ዋና መ/ቤት በመመለሳቸው ምክንያት በሚሲዮኑ ሰራተኞች የአሸኛኘት ፕሮግራም ተደረገላቸው።
01/07/2016
H.E Amb. Abadi Zemo hosted Remedan Iftar Dinner at the Embassy’s residence.
================================
H.E Abadi Zemo, Ambassador Extraordinary Plenipotentiary to the Republic of the Sudan, hosted Remedan Iftar Dinner to Sudanese journalists from different media outlets at the Embassy’s Residence. More than 130 journalists were in attendance.
H.E Abadi Zemo in his speech appreciated the constructive role that the Sudanese Medias are playing in further strengthening the relation between the two sisterly countries by providing the right information. He briefed them about the different areas of cooperation among others in implementing the different economic projects that enhances the economic integration of the two countries.
H.E Abadi briefed them also on the construction of Great Ethiopian Renaissance Dam, which will have enormous benefits to the Sudan. Finally, requested the journalists to continue playing their positive roles in further strengthening
26/06/2016
The Ethio -Sudanese Friendship Association organized Remedan Iftar Dinner.
H.E Dr. Omer Sulaiman, the Speaker of the States Council of the Republic of the Sudan, H.E Abadi Zemo, Ambassador of Ethiopia in Sudan, African diplomatic corps,and Ethiopian friends were in attendance.
12/06/2016
በዘላቂ የልማት ግቦች (SDGs) ዙሪያ ለኤምባሲው ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ፣
=============================
(ካርቱም: 4/10/2008 ዓ.ም):- እ.ኤ.አ በ2000 የታቀደው የምእተ ዓመቱ የልማት ግብ (Millennium Development Goals-MDGs) በ2015 መጠናቀቅን ተከትሎ ከ2012 ጀምሮ ስነደፍ የቆየውና በሰፕቴምበር 2015 በዓለም መንግስታት የጸደቀው የዘላቂ የልማት ግቦች (Sustainable Development Goals-SDGs) ሰነድ ዙሪያ በሱዳን የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አባዲ ዘሞ አማካኝነት ለኤምባሲው ሰራተኞች ገለጻ ተደርጓል።
ክቡር አምባሳደር አባዲ አክለውም አገራችን የምእተ ዓመቱን ግቦች በመፈጸም ረገድ በስኬት ማጠናቀቋን የተናገሩ ሲሆን በSDG የተቀመጡ ግቦችን ለመተግበር በአፈጻጸም ወቅት ብዙ ተግዳሮቶች ሊገጥሙን እንደምችል ብታመንም ግቦቹ ከአገራችን ፖሊሲ እና አገራዊ ዕቅዶች ጋር ተመሳሳይነት ስላለው፣ በMDGs ዕቅዶች አፈጻጸም ላይ የታየው የመንግስት እና ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት ተጠናክሮ ከቀጠለ በስኬት እንደሚጠናቀቅ እምነት ተይዞ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
01/06/2016
The Steering Economic Committee meeting headed by H.E Dr. Debretsion G/Michael, With Rank of Deputy Prime Minister Coordinator of the Economic Cluster, of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and H.E. Dr. Hassabo Mohamed Abdurahman, Vice President of the Republic of the Sudan, kicked off in the city of port Sudan of the Republic of the Sudan.