10/02/2026
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!!
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ማድረስ
10/02/2026
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!!
14/01/2026
Happy birthday, Declan 🥳
13/01/2026
የሰላም ስምምነቱ ትሩፋት
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት(አፋህድ) መካከል በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት የዘላቂ ሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል።
ለክልላችን ሕዝብ ሰላምንና እፎይታን የሚያመጣው ይኸው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን በመወከል በካፒቴን ማስረሻ ሰጤ የተፈረመ ነው።
ከስምምነቱ ማግስት በመሬት ላይ የታየው ዋነኛው የሰላም ስምምነቱ ትሩፋት፤ የአፋህድ ወታደራዊ ምክትል ዋና አዛዥ እና የወሎ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ ከነሙሉ ሠራዊታቸው ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለሳቸው ነው።
የኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ እና የሠራዊታቸው ውሳኔ፣ የተደረሰው ውል በሰነድ ላይ የሰፈረ ቃል ብቻ ሳይሆን በመሬት ላይ ያለውን እውነታ የመለወጥ እውነተኛ አቅም በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። እንዲህ ዓይነቱ ተግባራዊ እርምጃ በአካባቢው አስተማማኝ ጸጥታን ለማስፈን፣ የሕዝባችንን የሰላም ዋስትና ለማረጋገጥ እና ወደ ልማት ፊትን ለመመለስ ለተጀመረው ጥረት ትልቅ ስኬት ነው።
አሁን የታየው የሰላም ፍሬ ለቀሪው ኃይልም ትልቅ አርአያ የሚሆን ሲሆን፤ ልዩነቶችን በውይይትና በሰላም በመፍታት ረገድ በአህጉራዊና ቀጠናዊ ተቋማት አደራዳሪነት የተደረሰው ስምምነት ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የሚያበስር ነው።
~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
~•~••~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
11/01/2026
02/10/2025
30/05/2025
02/04/2025
15/03/2025