Wolaita Media Corporation WMC

Wolaita Media Corporation WMC

Share

ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ ፣ስፓርታዊ ዜናዎችን ጨምሮ የተለያዩ ዝርዝር ጉዳዮችን ለውድ ተከታዮቻችን እናቀርባለን ።አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን ።ኢትዮጵያ 🇪🇹👌ዎላይታ ዲቻ !!!

06/07/2026

የኢትዮጵያንግድባንክ 44.9m ደንበኞች አሉት።‎Service charge ብሎ ከሚቆርጠው ውጭ ያለ ደንበኞች ትዕዛዝ 6 ብር ዝርፊያ ይፈጽማል።44.9×6=269.4m birr በየወሩ 🤭‎የምን ፋኖ/ኦነግ ሸኔ ?

Photos from Wolaita Media Corporation WMC's post 06/07/2026

የዳሞት ጋሌ ምርጫ ክልል 1 ውጤት
የህዝብ ልጅ የሆነው ካዎ ኩምቤ ዳጋቶይ በሰፊው አሸንፏል 💪💪💪

1.Dagato Kumbe(ብልጽግና)=57,000

2.Woldemariam Lisanu((ወህነን) =5600

3.Tamenech Tadewos(ኢዜማ)=1120

4.Dr Temesgen Tora(ወህደግ)=900

06/07/2026

በደንብ ይነበብ !!! በደንብ ይደረግ !!!
የነዳጅ አቅርቦቱ ተስተካክሏል፤ የሸቀጦች ዋጋ ግን ለምን አልቀነሰም? ለመንግሥት ሠራተኛው የታለመ ልዩ ድጎማ ያስፈልጋል!
የመንግሥት ሠራተኛው ዛሬም ድረስ የኢኮኖሚው ቀውስ ቀዳሚ ሰለባ ሆኖ ቀጥሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠረው የነዳጅ እጥረት ምክንያት መሠረታዊ የሸቀጦች፣ የምግብ እህሎችና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ዋጋ በአንድ ጀምበር ሰማይ መንካቱ ይታወሳል። ይሁን እንጂ፣ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ አቅርቦቱ ተስተካክሎ ሰፊው ሰልፍ ቢቀንስም፣ በችግሩ ሰበብ የናረው የገበያ ዋጋ ግን ፍንክች ሳይል ባለበት ቀጥሏል። ይህ “ነዳጅ ሲጠፋ ወዲያውኑ የሚጨምር፣ ነዳጅ ሲገኝ ግን መልሶ የማይወርድ” የገበያ ሥርዓት አልበኝነት፣ ቋሚና ውስን ገቢ ያለውን የመንግሥት ሠራተኛ የዕለት ተዕለት ሕይወት ከአቅም በላይ አድርጎታል። ሠራተኛው አሁንም እየኖረ ያለው የወር ደመወዙና የገበያው ዋጋ ፍጹም በማይገናኝበት አስቸጋሪ እውነታ ውስጥ ነው።
ብዙ ጊዜ የኑሮ ውድነት ሲከሰት መፍትሔ ተደርጎ የሚወሰደው የደመወዝ ጭማሪ ነው። ሆኖም ግን፣ አሁን ባለው ተለዋዋጭ የገበያ ሁኔታ የደመወዝ ጭማሪ ብቻውን በቂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ደመወዝ በተጨመረ ቁጥር ገበያው ተከትሎት ዋጋ የሚጨምር ከሆነ፣ ጭማሪው ትርጉም ያጣል፤ እንዲያውም የገንዘብን የመግዛት አቅም በማዳከም የዋጋ ንረቱን (Wage-Price Spiral) ሊያባብሰው ይችላል የሚል ስጋት አለ። ስለዚህ፣ ለሠራተኛው በቀጥታ ገንዘብ ከመጨመር ይልቅ መንግሥት የተለየ እና የታለመለት የድጎማ ሥርዓት (Targeted Subsidy) ሊዘረጋ ይገባል የምንለው ለዚህ ነው።
መንግሥት የሠራተኛውን የመግዛት አቅም ለመጠበቅና የኑሮ ጫናውን ለማቃለል በአስቸኳይ ሊጠቀምባቸው የሚገቡ ሦስት መሠረታዊ የፖሊሲ አማራጮች አሉ፦
፩. የመሠረታዊ ሸቀጦች ድጎማ፦ ለሠራተኞች መሠረታዊ የሆኑትን እንደ ዘይት挑战፣ ስንዴ፣ ስኳርና የመሳሰሉትን ምርቶች በሠራተኞች የሸማች ማኅበራት በኩል በልዩ ቅናሽ ማቅረብ። ይህ በገበያው ላይ ተጨማሪ የገንዘብ ዝውውር ሳይፈጥር የሠራተኛውን ወጪ በቀጥታ ይቀንሳል። ፪. የትራንስፖርት ድጎማን ማጠናከር፦ የትራንስፖርት ወጪ የሠራተኛውን ደመወዝ እየበላው በመሆኑ፣ የመንግሥት ሠራተኞችን በነፃ ወይም በቅናሽ ዋጋ የሚያጓጉዙ የአገልግሎት አውቶቡሶችን (Service Buses) በስፋት ማሰማራትና ያሉትን ማጠናከር። ፫. የግብር ማሻሻያ (Tax Relief)፦ በአነስተኛና መካከለኛ ደመወዝ ላይ የሚጣለውን የደመወዝ ግብር ማሻሻል፣ ሠራተኛው እጁ ላይ የሚቀረው የተጣራ ገንዘብ (Take-home pay) እንዲያድግና የገበያውን ጫና እንዲቋቋም ይረዳል።
በመሆኑም መንግሥት በአንድ በኩል ያለአግባብ ዋጋ በሚጨምሩ አካላት ላይ ጠንካራ የገበያ ቁጥጥር እንዲያደርግ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሲቪል ሰርቪሱን ሕልውና ለመታደግ የተለየ የድጎማ አቅጣጫዎችን በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲያደርግ "የመንግሥት ሠራተኞች ድምፅ" ጥሪውን ያቀርባል።

06/06/2026

‎ከሰኔ ወር ጀምሮ ከመንግስት ሠራተኞች የሚቆረጥ ግብር ይቆማል ! ከሐምሌ 1 ጀምሮ አድስ የደሞዝ ማሻሻያ ፣ የቤት ኪራይ እና የትራንስፖርት ወጪ ጨምሮ የተለያዩ ዉሳኔዎችን መንግሥት ያስተላልፋል።

06/06/2026
06/06/2026

በወላይታ ዞን ቆላማ አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች የምግብ ዋስትና እንዲያረጋግጡ ዘንድ፥ መስኖ ተኮር ልማትን launch ማድረግ ይጠበቅብናል።ህዝባችን ባሁኑ ሰዓት ከፍተኛ ርሃብ ውስጥ ናቸው!!!

06/06/2026

ሙስቬኒ 20 የአርሰናል ደጋፊ ባለሥልጣኖች አባረሩ ።
የዩጋንዳ ፕሬዝዳንት አርሰናል ዋንጫ በላ ብሎ የሚጨፍር ባለስልጣን አባርራለሁ ሲሉ አስጠነቀቁ

የዩጋንዳ ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ አርሰናል ዋንጫ በላ ብለው የጨፈሩ የመንግስት ባለስልጣናትን አባርራለሁ ሲሉ አስጠንቅቀዋል

የህዝብን ችግር ይቀርፋል ከድህነት ያወጣል ብዬ የሾሞኩት ሚኒስትር እንዴት ለአርሰናል ሲዘል ይውላል በማለት የተናገሩት ሙሴቬኒ የተሰጠውን ሀላፊነት ሳይወጣ የቀረው ሚኒስትር ተባራሪ ነው ብለዋል::

አንዱማ ጭራሽ አርሰናል ዋንጫ ስለበላ ለህዝቡ የደስታ መልዕክት አስተላልፍ ብሎ መልዕክት ላከልኝ እኔ ብዬ ነው የመለስኩለት ሲሉ ተናግረዋል።

ህዝቡ የሚበላው አጥቶ እኛ እንዴት ስለ አውሮፓ ክለብ መጨፈር ቻልንበት አርሰናልን መደገፍ ትችላለህ ነገርግን ባለስልጣን ከሆንክ መጀመሪያ የህዝቡን ድህነት አሸንፍ ይሄን አልታገስም ብለዋል።

06/05/2026

ዉድ የሀገሬ መንግስት ሠራተኞች ኑ አብረን ድምፃችንን እናሰማ። በተለያዩ ተቋማት ሆናችሁ እየሰራችሁ የምትገኙ ወገኖቼ: ደከመን ሰለቸን ሳንል በየዘርፋችን ያለንን እውቀትና ብቃት ተጠቅመን ለሀገራችን እድገትና ልማት የምንተጋ የሀገር ባለውለታ ነን። እንደ ኢትዮጵያ መንግስትም የተለየ ክብር የሚገባን ዜጋ ነን። እውነታው ይህ ሆኖ እያለ የኢትዮጵያ መንግስት ሠራተኞች አሁን ያሉበት ሁኔታ እንኳን ለሠራተኛው ለተመልካቹ አሳፋሪ ሆኗል። ስለሆነም የተከበረው የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ጥያቄዎቻችንን በአስቸኳይ እንዲመልስልን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን:
1. የከረረውን ኑሮ ውድነት ለመቋቋም የምያስችል የደመወዝ ማሻሻያ ይደረግ
2. የሠራተኛውን ኑሮ ለማሻሻል በምያስችል መልኩ ግብር ይቀነስ
3 በየጀረጃው ላሉ ሠራተኞች የህክምና እንሹራንስና የቤት አበል በበቂ ሁኔታ ይመቻች
4 በሰዓታት ልዩነት ያልተገባ የዋጋ ጭማሬ በሚያደርጉ ህገወጥ ነጋደዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድ
5 በመንግስት ድጋፍ የተለያዪ ምግብ ነክና ሸቀጣሸቀጦችን ለሠራተኞች የሚያቀርቡ ማህበራት ይስፋፉ

Photos from Wolaita Media Corporation WMC's post 06/05/2026

እጅግ በጣም ዘግነኝና የፍትህ ሥረዓታችን ወድቀት የሚያሳይ ዜና
# # # # # # # # # # # #
በሆለታ ከተማ በችሎት ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት

| በሆለታ ወልመራ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በረፋዱ ክፍለ ጊዜ በህዝብ ዘንድ ታላቅ ሃዘንና ቁጭትን የጫረ አሰቃቂ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተከስቷል።

በወቅቱ የቤተሰብ ክርክር መዝገብ በመመልከት ላይ የነበረችው ወጣት ዳኛ ወርቄ ፈካንሳ የፍርድ ውሳኔውን በማንበብ ላይ እያለች፣ ተከሳሹ በድንገት በታጠቀው ሽጉጥ በፈጸመው ጥቃት ዳኛዋንና የገዛ ባለቤቱን ህይወት በችሎቱ አዳራሽ ውስጥ አጥፍቷል።

የፍትህ የበላይነት ይረጋገጥባቸዋል ተብለው በሚታመኑ የህግ መድረኮች ውስጥ እንዲህ ዓይነቱ ዘግናኝ ድርጊት መፈጸሙ፣ በህብረተሰቡ ዘንድ የደህንነት ስጋትንና ከፍተኛ ጥያቄን አስከትሏል።

ትጥቅ የያዘ ግለሰብ ምንም ሳይታገድ የፍርድ ቤት አዳራሽ ድረስ ዘልቆ መግባት መቻሉ የፍትህ ተቋማቱን የፍተሻ ሂደትና የውስጥ ጥበቃ ሥርዓት ምን ያህል ክፍተት እንዳለበት በግልጽ ያሳየ ክስተት ሆኗል።

Photos from Wolaita Media Corporation WMC's post 06/04/2026

Share ‼️
ወላይታ ሶዶ ከተማ ያላችሁ ወገኖች ይህች ልጅ ያለችበትን ሰፈር የምታውቁ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ወይም በአካል ያለችበት በመሄድ አሁን ካለችበት ሁኔታ እንድትወጣ በማድረግ እንድትተባበሩ ጥሪ እናቀርባለን!

ወጣቶች በህይወታች በቀላሉ ተስፋ አትቁረጡ…የማያልፍ ቀን የለም! 🥹

ይህች ወጣት የእኛን ድጋፍ ትፈልጋለች🥹

Want your business to be the top-listed Government Service in Seattle Heights?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

Bole
Seattle Heights, WA