11/04/2026
በ23 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል
በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ልዩ ስሙ "አምቦ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኩታበር ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡20 ሰዓት ላይ ሲሆን፣ ከደሴ ወደ ማሻ 85 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮ-3-አማ 34510 የሆነ የ"ታታ" የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ኩታበር ወረዳ 06 ቀበሌ ላይ ተገልብጧል።
እስከ አሁን ባለው መረጃ መሠረት በ12 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሌሎች 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። በአደጋው የጠፋ የሰው ህይወት የሌለ ሲሆን ተጎጂዎቹም በአሁኑ ወቅት አስፈላጊው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
የተሽከርካሪው አሽከርካሪ ከአደጋው በኋላ ከአካባቢው ያመለጠ ሲሆን የፖሊስ ሃይል አደጋው የተከሰተበትን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
© Kutaber/ኩታበር/
08/12/2025
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተስፋፋ ያለው የጥላቻ ንግግር በብዙ ንጹሃን ዜጎች ላይ የከፋ ሰብዓዊ ጉዳት እያደረሰ ነው።
በአንዳንዶቻችን ዘንድ የሚስተዋለው አጉል ትዕቢትና እብሪት በተሞላበት መንገድ፣ በሰላማዊ ቦታ ተቀምጠን፣ በተመቸ አልጋ ላይ ተኝተን፣ የታጠቁ ኃይሎችን በንቀት መመልከት ወይም ማጣጣል ተገቢ አይደለም።
በአፍ የሚተፋው እሳት የሚያስከትለው መዘዝ: እኛ በቃላት የምንተፋው እሳት፣ ሁኔታውን በማባባስ፣ በሌላ ወገን ደግሞ በመሣሪያ ሊቀለበስ እንደሚችል መገንዘብ ይገባል።
የሰላም መሠረት: የመፍትሄው መጀመሪያ ጠላትህንም ቢሆን ማክበር ነው። መከባበር ሲኖር፣ ከዚያ በኋላ ስለ ሰላም በንግግርና በውይይት ዘላቂ መፍትሔ መፍጠር ይቻላል።
💡 መልእክታችንን እናስተውል!
በቃላችን ከማጥፋት ይልቅ መገንባትን መርጠን፣ በሶሻል ሚድያ ላይ የምናደርገው ንግግር ለሰላም እንጂ ለግጭት ምክንያት እንዳይሆን በኃላፊነት እንጠቀም።
27/11/2025
የደሴ እና የኩታበር "የተድበሰበሰ" ሴራና የተጋለጠው እውነት!
ከደሴ ከተማ በ15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኩታበር ወረዳ እና በደሴ ከተማ ዙሪያ እየተከናወነ ያለው ክስተት ወታደራዊ ሽንፈት ሳይሆን፣ በአመራሮች የተቀነባበረ "የመናበብ ሴራ" ውጤት መሆኑን የሚያጋልጡ መረጃዎች ወጥተዋል። ጉዳዩን በጥልቀት እንደሚከተለው እንመለከተዋለን፡-
1. የአመራሮች ድርብ ሚናና የአካባቢው መያዝ
በአሁኑ ሰዓት በኩታበር ወረዳ ከቀበሌ 14 እስከ 21 ያለው ሰፊ ቀጠና ከ23 ቀበሌ 21 ቀበሌ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል። ለዚህ ሁኔታ መፈጠር ዋናው ምክንያት የኃይል ሚዛን መዛባት ሳይሆን፣ የደሴ እና የኩታበር ወረዳ አመራሮች እየተጫወቱት ያለው አደገኛ ድርብ ሚና ነው። እነዚህ አካላት በአንድ በኩል የመንግስት (PP) ባለስልጣን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የፋኖ ደጋፊ በመሆን ህዝብንና መንግስትን እያምታቱ መሆናቸውን የሚያሳይ ጥቆማ አለ።
2. የሚሊሻዎች ክህደትና ዘግናኙ የ021 ቀበሌ ክስተት
ጉዳዩ ከፖለቲካ ሴራ አልፎ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ አስከፊ ወንጀልንም አካቷል፡-
የኩታበር አመራሮች ከደሴ ጋጃግሬዎች ጋር በመናበብ በ021 ቀበሌ የሚገኙ #ከ50 በላይ #ሚሊሻዎችን ለጠላት አሳልፎ በመስጠት በጅምላ ኢንድጨ*ፈጨፉ ሁኔታዎችን አመቻችተዋል።
ይህንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በእጃችን የሚገኝ ሲሆን፣ የንጹሃን ደም የፈሰሰው በዚህ የውስጥ ሴራ ምክንያት ነው።
3. የግሸን ደብረ ከርቤ በዓልና ተከትሎ የመጣው ጥፋት
የመከላከያ ሰራዊት የግሸን ደብረ ከርቤን ዓመታዊ በዓል በሰላም ለማስከበር ከኩታበር በወጣበት ቅፅበት የተፈጠረው ክፍተት የታቀደ ነበር የሚል ጥርጣሬን አጭሯል፡-
መከላከያ አካባቢውን ለቆ ሲወጣ፣ በከተማዋ ውስጥ እያሉ በቢሯቸው ስራ እየሰሩ #ፋኖ ከተማዋን ተቆጣጥሯል።
በዚህም #ከ10 በላይ ንፁሃንና #ሚሊሻዎች ተጨ**ፍጭፈዋል።
የሚገርመው ነገር፣ ይህ ሁሉ ሲሆን አመራሮቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው፣ መልሰው ወረዳውን እንዲያስተዳድሩ ይሁንታ ተሰጥቷቸው ዛሬም ድረስ ለፅንፈኛው ኃይል አገልጋይ ሆነው ቀጥለዋል።
4. የደሴ ዙሪያ ወረዳዎች እጣ ፈንታ
የደሴ ዙሪያ ወረዳ መቀመጫው ራሱ ደሴ ከተማ ሆኖ ሳለ፣ ከ40 በላይ ቀበሌዎች ውስጥ ግማሽ ያህሉ በታጠቁ ሃይሎች እጅ ወድቀዋል። ይህ ሊሆን የቻለው በአመራሩ በሚስጥር የተደራጀ ሴራ እንጂ በሌላ አይደለም።
#ማስጠንቀቂያ
በአሁኑ ወቅት በደሴ ከተማ እየታፈሱ ያሉ ንጹሃን ወጣቶች፣ በከተማዋ የመሸገውና በድርብ ሚና የሚንቀሳቀሰው አመራር ለራሱ ህልውና ሲል የፈጠረው ስጋት ሰለባዎች ናቸው።
#መልዕክታችን_ግልጽ_ነው፡-
"ለከተማዋ ውበትና ሀብት ዘብ የቆሙ ልጆቿን በዚህ ልክ የምታሳድዱ ከሆነ፣ የደሴ ከተማ ነገ ፊቷን ታዞርባችኋለች። ያኔ መድረሻችሁ የት ይሆን? ከዋና ዋናዎቹ የቡድኑ መሪዎች ጋር በጥቀሻ እየተግባቡ ያሉትን የደሴ ቁልፍ ሰዎች በአሉባልታ ሳይሆን ከፈረሱ አፍ ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን። የተሸፈነው ሴራ ሁሉ ተገልጦ መከራችሁ እንዳይበዛ አደብ ግዙ!"
25/11/2025
ሰውን በጦርነት ውስጥ ሆናችሁ እንኳን ቢሆን ሊገድላችሁ የሚመጣን ጠላት ለመገደል ሰውን አታሰቃዩ እንድሁም እንስሳትን ለምግብነት ለማረድ እንስሳትን ስታርዱ አታሰቃዩ የሚል እምነትን በሀሰት ሲከሱ የነበሩ የፅንፈኛ ስብስብ ሰውን በመጥረቢያ አካል ሲቆራርቱ በአደባባይ ተጋለጡ።
25/11/2025
የኩታበር ወረዳ የከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ አያሌዉ በድንገተኛ ህመም ምክንያት ህዳር 15/2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹና ለስራ ባልደረቦቹ በሙሉ መጽናናትን እንመኛል!
Kutaber/ኩታበር/
22/11/2025
እነ ሳሙኤል ቦሩ መስጅድ ሲያፈርሱ "ሸገር ሲቲ መሰላችሁ እንዴ?" የተባሉትን ወይም "ደላንታን ለደሴ ልማት reference" አታድርጉ ከፍ ብላችሁ እዩ! የተባሉበትን ቆርጦ ቀጣጥሎ ለሳሙኤል ታማኝነቱን ለማረጋገጥ በጎጥ ከፋፈላችሁን የምትል ጽሁፍ በግጥም ሳይሆን በ ስ ድ ንባባብ ጃኖ መንግስቱ አጋርቷል። ያው አሰላለፉን ግልጽ ላድርግ ብሎ እንጂ ከተረዳነው ቆየ። ከነበረን ውሎ አንጻር ቆርጦ ቀጥልነት እንኳን አይመጥነውም ነበር። ለማንኛውም ዘመዶችህ በሀይማኖት ተወሽቀው አገር አያጥፉ። እንኳን አንተ እነ አሳየ ደርቤም ፋኖም መከታ የቆመላቸው የዘረጉት ሰንሰለት እንደሆነ አይጠፋንም። ከሁሉ በላይ የመንግስቱ ድክመት ወሎየነትን ልንገራችሁ የሚለው ነገር 😁😁😁😁
ደግሞ አለማፈራቸው የደሴ ከንቲባ ጠበቃ መንግስቱ ዘገዬ ከፋኖ አሳዬ ደርቤ መሰለፋቸው የምንመለከተው ወሎን በሀይማኖት የተደራጀው ፋኖና የሞዓ ተዋህዶ በጋራ መናበባቸውን እራሳቸውን የደበቁትን በአደባባይ ማስወጣታችን ነው። ማን ከማንም ጋር እንደሚሰለፉ በንቃት እየተከታተልን ነው።
20/11/2025
የደሴ ባለስልጣናት በልማት ድክመት ሲወቀሱ የት ሄደው እንደሚደበቁ ተመልከቱ 👇 ማን እንደሚመክትላቸውም ያስተውሉ። የፋኖ ቃል አቀባዩ አቶ ሳሙኤል በፋኖ አሳየ ደርቤ ምስክርነት ሲሰጥ። ደሴን በልማት ስም የመሬት ነጋደው የደሴ ከንቲባው ለማንና ማን ጋር እንደሚሰራ ተመልከት።