13/02/2026
የታች አርማጭሆ ወረዳ ምክር ቤት የ5ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔ አካሄደ።
በጉባዔው ላይም የምክር ቤቱ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የየዘርፉ አመራሮች ተገኝተዋል።
በዚህ መደበኛ ጉባዔ ላይም ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ስራዎች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በሌላ በኩልም በየደረጃው ከህዝብ የሚነሱ የመሰረተ ልማት፣ የፍትህና የፀጥታ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በመጨረሻም ምክር ቤቱ የቀረቡለትን ሪፖርቶች በጥልቀት በመገምገም የተለያዩ ውሳኔዎችንና ሹመቶችን አፅድቀዋል።
"ጠንካራ ምክር ቤት ለህዝብ ተጠቃሚነት"
13/02/2026
የታች አርማጭሆ ወረዳ ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው::
የካቲት 06/2018 ዓ.ም ሳንጃ :-የታች አርማጭሆ ወረዳ ምክር ቤት የ2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት በሳንጃ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በዛሬው ውሎውም ምክር ቤቱ የወረዳውን አስፈፃሚ አካላት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪም የወረዳው ፍርድ ቤት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ የሚቀርብ ሲሆን፤ በፍትህ ስርአቱ ላይ የታዩ ጥንካሬዎችና የቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።
ምክር ቤቱ በቆይታው የወረዳውን ሰላምና ልማት የሚያረጋግጡ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዋነኝነት የሚመክርባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎችም
የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ሹመት፣የፍትህና የጸጥታ ስራዎች እንዲሁም የግብርና፣ የጤና እና የትምህርት የልማት ሪፖርቶች በዝርዝር የሚቀርቡ ይሆናሉ።
02/02/2026
ለሁሉም ተቋማት፣
የአ.ብ.ክ.መ. ምክር ቤት ድህረ-ገፅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስለማሳወቅ ፣
የአ.ብ.ክ.መ. ምክር ቤት የክልሉን ልማት፣ዕድገት፣ሰላምና የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲፈታ፤የማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እልባት እንዲያገኙ የክልሉን ምክር ቤት አባል፣በየዘርፉ ያሉ የክልሉ ቋሚ ኮሚቴዎችንና የተዋረድ የምክር ቤት አባልን በማነቃነቅ የአስፈፃሚ አካላት ተግባራትን በመገምገም እና በመደገፍ ተቋማት ከተቋማት ካለባቸው ክፍተት እንዲወጡ ከፍተኛ የሆነ ክትትል ያደርጋል፡፡
ስለሆነም እነዚህን ስራዎች በክልል ምክር ቤት ፌስ-ቡክ ፔጅ በመልቀቅ ከፍተኛ አባላትን እያፈራ ይገኛል፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ክልል ምክር ቤቱ 23‚500 አካባቢ ተከታይ እንዳለው በድህረ-ገፁ መረጃ መረዳት ችለናል፡፡ ስለሆነም የወረዳ አስፈፃሚ አካላት በስሩ ያሉ ቡድን መሪዎች እና ሙያተኞች የድህረ-ገፁ ተጠቃሚ በመሆን የሚለቀቁ ተግባሮችን ላይክ ኮሜንትና እና ሼር በማድረግ የተቋሙ አጋር እንድትሆኑ እናሳስባለን፡፡
‹‹ጠንካራ ምክር ቤት ለህዝብ ተጠቃሚነት››
መልሽው አጥቃው
የታች አርማጭሆ ወረዳ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ
ማሳሰቢያ፡- ድህረ-ገፁ Amhara National Reginal
Council በማለት ይጠቀሙ
http://anrscouncil1.gov.et
Send a message to learn more
17/11/2025
በታች አርማጭሆ ወረዳ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡
“ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ከወረዳ ጠቅላላ መንግስት ሰራተኛ ጋር በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የታች አርማጭሆ ወረዳ ተወካይ ዋና አስተዳዳሪና ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንጋው መጣለም የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ብዝኅነትን በአንድነት፣ አንድነትን በብዝኅነት የምናሳይበት ልዩ ቀን ነው።
የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትንና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
ከነጠላ ትርክት ወጥቶ የጋራ ትርክትን መገንባት እንደሚገባም አስገንዝበው ሀገራዊ አንድነትን ለማጎልበት እና ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም አካል መስራት እንዳለበት ተናግረው የኢትዮጵያዊነታችን እሴት ማክበከር እና ሰላምና ማጽናት አለብንም ብለዋል፡፡
የታች አርማጭሆ ወረዳ ሲቪል ሰርቢስ ኃላፊ ወ/ሮ ዘነብ ታደሰ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሀገራችን ያሉት ብሔር ብሔረሰቦች ባህላቸውንና እሴታቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ አንድነትንና አብሮነትን የሚያጠናክር፣ መቻቻልንና መከባበርን የሚያጎለብት መሆኑን ገልፀው ብዝሀነትን ለማስተናገድ እና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡
እንደ ሀገር የወል ትርክትን ለመገንባት እና በጋራ ጉዳዮች ላይ በአንድ ለመቋም በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን አንድነታችንና አብሮታችንን በሚያጠናክር መንገድ ማክበር አለብንም ብለዋል፡፡
የታች አርማጭሆ ወረዳ ም/ቤት ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ጌታቸው እንዳለው እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዚህ መልኩ መከበሩ ጥሩ መሆኑን አንስተው የዲሞክራሲ ባህልን በማዳበር እና ህብረ ብሔራዊ መግባባትን በማጠናከር ሀገራዊ አንድነትን መገንባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ከመጣንበት የነጠላ ትርክት ወጥተን የጋራ ትርክትን መገንባት እንደሚያስፈልግም ጠቁመው እንደ ሀገር አንድ በሚያደርጉን እና በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ መስራት አለብንም ብለዋል፡፡
የድልፋና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የዜግነት የትምህርት ክፍል መህምር አኪያ ሲሳይ ዲሞክራሲ እና የፌደራሊዝም ስርአት በኢትዮጵያ በሚል ርእስ ለፓናል ውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ አቅርበዋል፡፡
የፌደራሊዝም ስርዓት የፖለቲካ ተሳትፎን እንደሚያበረታታ፣ የአስተዳደር ብቃትን እንደሚያሳድግ፣ የሀይል ሚዛንን እንደሚያስጠብቅ፣ ብዝሀነትን እንደሚያስተናግድ ገልፀው በሀገራችን ኢትዮጵያ የፌደራሊዝም ስርአትንን በአግባቡ ማስኬድ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የውይይት ተሳታፊዎች እንደገለፁት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዚህ መንገድ መከበሩ ጥሩ መሆኑን እና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረው ብዝሀነትን በአግባቡ ለማስተናገድ በትኩረት ተይዞ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡
መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ሊሰራ እንደሚገባም ጠቁመው የኢኮኖሚ ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ እና አንድነትን ለማጠናከር መሰራት አለበትም ብለዋል፡፡
06/11/2025
ባህላዊ የሽምግልና ስርዓት መማክርት ጉባዔን ማቋቋም የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለማስወገድና ሰላምን ለማስፈን ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተገለፀ።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ የሽምግልና ስርዓት መማክርት ጉባኤ ለማቋቋም በወረዳው የሚገኙ በየቀበሌዉ የተወጣጡ የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት ዉይይት ተካሂዷል ።
በውይይቱም የሽምግልና ስርአት መማክርት ጉባኤ ማቋቋም በየአካባቢያችን ግጭትን ለማስወገድና ሰላምን ለማስፈን ህዉከትም ሆነ ብጥብጥ ሲፈጠር ግጭትን በዉግዘት ማስወገድና ሰላምን ማስፈን የመማክርት ጉባኤዉን መመስረት አስፈላጊ ነው ተብሏል ።
በተጨማሪ በወረዳዉ የሽምግልና ስርአት ተቋም መፋጠኑ ግጭትን በማስወገድ እርቅ በማድረግ የህብረተሰቡን የሰላምና የመቻቻል እንዲሁም አብሮ የመኖር ፍላጎትን ለማሟላት የሚደረገዉ ጥረት የራሱን አስተዋፅኦ የሚያበረክተው ፍይዳ ከፍተኛ ነው ተብሏል ።
በሃላዊ የሽምግልና ስርዓት ወረዳዊ ስሜት ብቻ ሳይሆን አገራዊ ስሜት መግባባትና አንድነታችንን በማጠንከር መልካም አገራዊ ገፅታን እንዲገነባ የሚያግዝና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፍይዳው የጎላ ነው ተብሏል ።
በውይይቱም በሁሉም ቀበሌዎች የሚመረጡ የሽምግልና ስርዓት መማክርታት የአካቢያቸውን ሰላም ለማስፈን ፣ የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለማውገዝና ለማስወገድ በትኩረት ለመስራትና ለማቋቋም የፍትህ አካላት የምክር ቤት ሙያተኞችና የባህልና ቱሪዝም አካላት በተገኙበት በስፋት ተወያይተዋል ።
28/10/2025
18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በታች አርማጭሆ ወረዳ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከበረ።
በዓሉም "ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ህዳሴ!" በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስማረ የኋላሸት፣ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳላማው ዘውዱ ፣ የወረዳ አመራሮች፣ የፀጥታ አካላትና የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤት ባለሙያዎች በተገኙበት በፓናል ውይይት፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር በታጀበ ሰንደቅ ዓላማ በክብር በመስቀልና በሌሎች ሁነቶች በድምቀት ተከብሯል ።
ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም
የታች አርማጭሆ ወረዳ ምክር ቤት
ሳንጃ
18/10/2025
ሰላምን ዋነኛ የውይይት አጀንዳ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
የታች አርማጭሆ ወረዳ ምክርቤት 5ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ።
በጉባዔውም ልዩ ልዩ የመወያያ አጀንዳዎች ቀርበው በስፋትና በጥልቀት የተመከረባቸው ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ሰላምን ዋና የውይይት አጀንዳ በማድረግ በወረዳው የታየውን አንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት ወደ ዘላቂ ወይም አዎንታዊ ሰላም ለማሸጋገር ሕዝባዊ ውክልናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ተብሏል::
ይህንን ለማሳካት ደግሞ የምክር ቤት አባላት በምክር ቤቶች አሰራርና ዕቅድ መሠረት ሰፊ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረኮችን በማካሄድ ሰለሙ እንዲጸና ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።
በመጨረሻም የወረዳው የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት መሪ ዕቅድና የማስፈፀሚያ በጀትን በማጽደቅ ጉባዔው ተጠናቋል።
31/01/2025
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የታች አርማጭሆ ወረዳ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 12ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ።
የጉባዔውን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክርቤቱ ምክትል አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ መልሺው አጥቃው ሲሆኑ ምክር ቤቶች ታላቅ ህዝባዊ ውክልና የተጣለባቸው መሆኑን በመጥቀስ አባላት በጉባዔዎች ከመሳተፍ ባሻገር የወከላቸውን ህዝብ ታች ድረስ በመውረድ ከወካዩ ህዝብ የተረከቡትን አደራ በአግባቡ በማንጸባረቅ ውክልናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በጉባኤውም የ2017 የበጀት ዓመት በ6ወራት የተከናወኑ የሠላም፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስማረ የኋላሸት የቀረበ ሲሆን በዚህ አጀንዳም አባላት ሰፊ ውይይት በማድረግ በድክመት የታዩ አፈጻጸሞችን ቀጣይ መሙላት እንደሚገባና አባላትም ከእነሱ የሚጠበቀውን የውክልና ሚና በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ተገልጿል። በመጨረሻም በቀጠይ በሚሰሩ ቀሪ ወራት አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል ።
22/07/2023
የታች አርማጭሆ ወረዳ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔ እያካሄደ ይገኛል።
ጉባዔው ወ/ሪት መልሺው አጥቃውን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ ሾሟል። ከዚህም በተጨማሪ በጉባኤው የምክር ቤቱ ዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የተጠቃለለ ወረዳዊ የልማትና መልካም አስተዳደር ሪፖርት ቀርቦ በጥልቀት ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል ።
14/04/2023
እንኳን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለእኛ ምሳሌ በመሆን ጥልን በመስቀሉ እንዳስታረቀ ሁሉ እኛ ኢትዮጵያንም በመካከላችን ያለውን መጠላላትና መጠላለፍ አስወግደን መተሳሰብና መዋደድን የምንሰብክበትና አንድነታችን የምናጠናክርበት ጊዜ እንዲሆንልን እንመኛለን !
መልካም የስቅለት በዓል ይሁንልን!