02/26/2025
“የአድዋ ጦርነት፤ የአፍሪካ ሕዝቦችን አይበገሬ ጠንካራ መንፈስ፣የውጪ ወራሪ ኃይልን ለመመከት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው ለምስክርነት የቆመ ታሪክ ነው”
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ
#አድዋ #ኢትይጵያ #1888
BALDERAS SUPPORT GROUP OF TORONTO AREA
02/26/2025
“የአድዋ ጦርነት፤ የአፍሪካ ሕዝቦችን አይበገሬ ጠንካራ መንፈስ፣የውጪ ወራሪ ኃይልን ለመመከት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው ለምስክርነት የቆመ ታሪክ ነው”
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ
#አድዋ #ኢትይጵያ #1888
02/19/2025
ማንነትን መሰረት በማድረግ የሚፈፀም ግድያ እና ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ ጦርነት እንዲቆም ባልደራስ ፓርቲ ያሳስባል
ከባልደራስ ፓርቲ የንፁሀንን ግድያ እና መፈናቀል አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ዋላ በተባለ ቀበሌ የካቲት 6/2017ዓ.ም.ጀምሮ ማንነትን መሠረት ባደረገ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ በዞኑ ጌራ ወረዳ ዋላ በተባለ ቀበሌ የአንድ ግለሰብን ሞት ተከትሎ የታጠቁ ወጣቶች ማንነትን መሠረት አድርገው በፈፀሙት ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ የጥቃቱ ሰለባዎች እንደገለፁት ከሆነ፣ የአማራ ተወላጆችን ኢላማ ያደረገ ውድመት በታጠቁ ዘራፊ ኃይሎች ተፈፅሟል ፡፡ ጥቃቱ የአማራ ተወላጆች የሚኖሩበትን በርካታ አካባቢዎችን ያዳረሰ ሲሆን የቦሬ ከተማ በእሳት እና በዝርፊያ የወደመች መሆኗን የጥቃቱ ሰለባዎች አብራርተዋል፡፡
በጥቃቱ የእድሜ ባለ ፀጋ አዛውንቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የሟቾችን ቁጥር እስካሁን በትክክል ማወቅ አልተቻለም፡፡ ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ወደ ደቡብ ምዕራብ ክልል መሰደዳቸውን እና በርካታ ሰዎች ነፍሳቸውን ለማዳን ወደ ጫካ መግባታቸውን የዐይን እማኞች አረጋግጠዋል፡፡
እነዚህ ወደ ደቡብ-ምዕራብ ክልል የተሰደዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰለባዎች፣ በክልሉ ከፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በከፋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሚዲያዎች ጭምር አረጋግጠዋል። የብልፅግና አገዛዝ ወደ ስልጣን ከመጣ አንስቶ አማራውን በሁሉም ቦታ እየገደለው እና እያፈናቀለው ይገኛል፡፡
በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች በተገደሉበት እና በተፈናቀሉበት ተመሳሳይ ጊዜ የካቲት 1/2017ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ ዘንቦ ቀበሌ በርካታ ሰዎች በድሮን ጥቃት መገደላቸውን የአይን እማኞች አረጋግጠዋል፡፡በተመሳሳይ ዕለት የካቲት 6/2017ዓ.ም.በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ጂብጎዶ ቀበሌ በርካታ ንፁሐን በድሮን ጥቃት ተገድለዋል፡፡
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በንፁሐን ዜጎች እልቂት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ የሚከተሉትን ጥሪዎች ያቀርባል፦
1. ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ የሚፈፀም ግድያ እና ማፈናቀል ባስቸኳይ እንዲቆም እና ተጎጅዎች አፋጣን መፍትሄ እንዲያገኙ ያሳስባል፤
2. በአገዛዙ የሚፈስ የንፁሐን ደም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያበቃ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህ ስርዓት የሚፈፅመውን ኢ- ሰብዓዊ እልቂት እንዲያቆም ሕዝባዊ ጫና እንዲደረግበት ባልደራስ ጥሪውን ያቀርባል።
የባልደስራ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
አዲስ አበባ ጣሊያኖች በለኮሱት እሳት ተቃጥላ ስትጨስ ቀን አይተው ነበር። ሌሊት ደግሞ በቃጠሎዋ ነበልባል እንደ ኮከብ ስታበራ አይተው አንድ ጊዜ አለቀሱ። ዕንባቸው በቁስላቸው ወረደና ፈጃቸው። ለበለባቸው።
“አምላክ ቦታውንና ሕዝቡን ትቶት ሔዷል” አሉ።
የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ/ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
02/08/2025
ከባልደራስ ፓርቲ ታሪካዊ ቀናት በጥቂቱ
👉 የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት (ባልደራስ)፦ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም በባልደራስ አዳራሽ ተመሠረተ
👉 በይፋ ወደ ፓርቲነት እንዲያድግ ከህዝብ ጥያቄ ፦ በሕዳር 15/2012 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ ቀረበ
👉 የቅድመ ፓርቲ ምስረታ ጉባኤውን ፦ ጥር 3/ 2012 ዓ.ም ካዛንቺስ ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል አካባቢ (መንገድ ላይ) አደረገ
👉 የፓርቲውን ስያሜው "ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ" ብሎ በመሰየም ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋን ጊዜያዊ ፕሬዝዳንቱ አድርጎ መረጠ
👉 የፓለቲካ ፓርቲ የጊዜያዊ የምዝገባ ፍቃድ የምስክር ወረቀት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፦ ጥር 4/2012 ዓ.ም ተቀበለ
👉 የመስራች ጉባኤውን፦ የካቲት 1/2012 ዓ.ም በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ አካኼደ
👉 ፕሬዝዳንቱን እስክንድር ነጋን ጨምሮ አመራሮቹ ፦ ሰኔ 23/2012 ዓ.ም ከዋናው ፅ/ቤት እና ከሌሎች አካባቢዎች ተወስደው ታሰሩ
👉 ከአመት ከስድስት ወር የእስር ቆይታ በኋላ መሪዎቹ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋን ጨምሮ አመራሮቹ ፦ ታህሳስ 29/2014 ዓ.ም ተፈቱ
👉 ከ25 በላይ አባላቶች እና አመራሮች የካራማራን ድል ሊያክብሩ በሄዱበት በአገዛዙ ፦ የካቲት 26/2014 ዓ.ም ድላችን ሀውልት፣ ጥቁር አንበሳ አካባቢ ተይዘው ታሰሩ
👉 የሀገር አቀፍ ፊርማ ማሰባሰብ ማስጀመሪያ ፕሬዝዳንቱ እስክንድር ነጋ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት በአርባ ምንጭ ተካሄደ፦ ሚያዝያ 12/2014 ዓ.ም
👉 ወደ አርባምንጭ የሄደው በፕሬዝዳንቱ የተመራው ልኡክ ቡድን ታስሮ በማግስቱ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ፦ ሚያዝያ 12 እና 13 /2014 ዓ.ም ተደረገ
👉 መሪው እስክንድር ነጋ ለቤተሰብ ጥየቃ እና ለፓርቲ ስራ ወደ አሜሪካ፦ ሚያዝያ 15/2014 ዓ.ም ሄዱ
👉 ከወራት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ አቶ እስክንድር ነጋ ወደ ሀገር ፦ ሐምሌ 6/2014 ዓ.ም ተመለሱ
👉 ፕሬዝዳንቱ እስክንድር ነጋ በፃፉት ደብዳቤ ምክንያቶቻቸውን ጠቅሰው ከአመራርነትም ሆነ ከአባልነት ከፓርቲው መልቀቃቸውን ፦ ሐምሌ 16/2014 ዓ.ም አሳወቁ
👉 በወቅቱ ም/ፕሬዝዳንት ኋላ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አምሃ ዳኜው ጉባኤ ለማካሄድ በስራ ላይ እያሉ በአገዛዙ ፦ መጋቢት 2/2015 ዓ.ም ከፓርቲው ዋና ፅ/ቤት ተወስደው ለሰአታት ታገቱ
👉 ከብዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች/ፈተናዎች በኋላ የአንደኛ መደበኛ ጉባኤውን ለማድረግ:- መጋቢት 3/2015 ዓ.ም በጋምቤላ ሆቴል ቢሰበሰብም በአገዛዙ አፈና ምክንያት ጉባኤው ሳይደረግ ቀረ
👉 ፓርቲው ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ "አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን" ፦ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል በማካኼድ አቶ አመሃ ዳኜውን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም የምክርቤት፣ የኦዲትና ቁጥጥር እና የዲሲፕሊን ኮሚቴ አባላትን መረጠ
👉 ፓርቲው ወደ ሀገር አቀፍነት እንዲያድግ እና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ እንዲሰራ ጠቅላላ ጉባኤው ፦ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም ወሰነ
👉 ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት ለማደግ የፊርማ ማሰባሰብ ስራ ፦ የካቲት 24/2016 ዓ.ም ጀመረ
👉 ከአራት ክልሎች 6 ሺህ ፊርማ ብቻ ቢጠበቅበትም፣ ከስድስት ክልሎች አስር ሺህ ፊርማ በማሰባሰብ ለምርጫ ቦርድ ፦ ግንቦት 19/2016 ዓ.ም አስገባ
👉 የሀገር አቀፍ ፓርቲነት የምስክር ወረቀቱን ፦ ነሐሴ 23/2016 ዓ.ም ተቀበለ
02/08/2025
አምስት አመታትን ለህዝብ በመታመን
ከክልል አቀፍ ፓርቲነት እስከ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት!
ድል ለኢትዮያ!
ድል ለዲሞክራሲ!
02/04/2025
በአፋር ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥቃት በጥብቅ እናወግዛለን
ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ይርተሰጠ መግለጫ
በጥር 22/2017 ዓ.ም በአውሲ ራሱ ዞን ኤሊዳር ወረዳ ኪያሩ ቀበሌ በደረሰ የድሮን ጥቃት ቢያንስ ስምንት የሚሆኑ የአፋር ወገኖቻችን መሞታቸው ታውቋል። ጥቃቱ የተፈፀመው በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ድሮን መሆኑን የጅቡቲ መንግስት ያመነ ሲሆን፣ ነገር ግን በራሱ ግዛት ላይ እንደተፈፀመ አሳውቋል። እንደ ምክንያት የጠቀሰውም የሽብር ጥቃትን ለመከላከል እንደሆነ ገልጿል። የአፋር ክልል ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ጭምር ግን ጥቃቱ በአፋር ክልል ላይ እንደተደረገ እና በጥቃቱም ንፁሀን እንደተገደሉ እማኝነታቸውን ገልፀዋል።
ሆኖም የኦህዴድ-ብልፅግና አገዛዝ ጉዳዩን አስመልክቶ እስካሁን ምንም አይነት መግለጫ አልሰጠም። ይህም አገዛዙ በህዝብ ላይ ለሚደርስ ሞት እና ውዥንብር ደንታ ቢስ መሆኑን በግልፅ የሚያሳይ ነው። ይህ በርሀብ፣ በኑሮ ውድነት፣ በሙስና፣ በመልካም አስተዳደር እጦት... ወ.ዘ.ተ ፍዳውን እየበላ የሚገኝ ህዝብ ላይ ተጨማሪ የድሮን ድብደባ ሲደርስበት እጅግ አሳዛኝ ነው። ከደረሰው ግድያ ባልተናነሰ በተለይ አደጋው በሚመለከታቸው ተቋማት ትኩረት ሳይሰጠው መቅረቱ አሳዛኝነቱን ያጎላዋል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ሞት እና ጉዳት እያዘነ ፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል። አገዛዙም በአስቸኳይ በንፁሀን ላይ ለደረሰው ግድያ እውቅና እንዲሰጥ እና በአስቸኳይ ግልፅ ማብራሪያ እንዲያቀርብ ፓርቲው ያሳስባል።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
01/28/2025
በሕዝብ ማታገያ ድርጅት ላይ በፈጠራና በሀሰተኛ ወሬ የሚሰነዘር የስም ማጥፋት፣ የሕዝብን ትግል ከማደናቀፍ ተለይቶ አይታይም!
ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እስከ ነሀሴ 2016 የመጨረሻ ሳምንት ድረስ በክልል አቀፍ ፓርቲነት ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወቃል። ሆኖም ፓርቲው ወደ ሀገር አቀፍነት ማደግ እንዳለበት በጠቅላላ ጉባኤ ታምኖበት ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ፣ ከ6 ክልሎች ከሚጠበቅበት ከአስር ሺህ ፊርማ በላይ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ለምርጫ ቦርድ ሀገር አቀፍ ፓርቲነቱ እንዲፀድቅለት ጥያቄ አቅርቦ፣ የቀረቡት ፊርማዎችም ተጣርተው የሀገር አቀፍ ፓርቲነት የምስክር ወረቀቱን ነሐሴ 23/2016 ዓ.ም ከምርጫ ቦርድ ተረክቧል። ይህ ስራ በሚሰራበት ጊዜ በስራው ላይ የተሳተፉ አባሎቻችን እና አመራሮች እስራትና እንግልት ደርሶባቸዋል። ሆኖም ፓርቲያችን ባልደራስ መስዋዕትነት የማይበግረው ስለሆነ ስራው ከዳር ደርሶ ባልደራስን ሀገር አቀፍ አድርገውታል። የሀገር አቀፍ ፓርቲነት አውቅናን ካገኘ ከ2016 ሶስተኛ ሳምንት ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ አባላትን እየመለመለ እና አደረጃጀት እየሰራ ይገኛል።
ነባራዊ ሀቁ እንዲህ ሆኖ እያለ ፓለቲካ ትንተናን ከተራ አሉባልታ መለየት የተሳናቸው አዋቂ ነን ባዮች፣ የዚህን ከተመሰረተ ጀምሮ እስካሁኑ ድረስ ለገዥዎች ያለጎበደደ፣ ለህዝብ ጥቅም አመራሮቹ እና በርካታ አባሎቹ ከባድ መስዋዕትነት የከፈለሉለትን ፓርቲ፣ በዚህም ክንወኑ በሕዝብ ህሊና ውስጥ በአወንታዊ መልኩ የተቀረፀን ፓርቲ፣ ፓርቲው ሳይደርስባቸው ስሙን በፈጠራ ወሬ እያጠፉት ይገኛሉ። እነዚህ የሴራ ፖለቲካ አራማጆች ምንም መረጃ በሌላቸው እና በመሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በካደ መልኩ ፓርቲው ፈርሷል እስከ ማለት ደርሰዋል። ከእነዚህ ጥቂት የውሸት አምራቾች ውስጥ በመረጃ ቲቪ ላይ የሚታወቁት አቶ ግርማ ካሳ ይገኙበታል። እኚህ ፖለቲካን በቅርበት እከታተላለሁ ብዙ መረጃዎችን አገኛለሁ የሚሉ ግለሰብ "ባልደራስን የቀድሞው የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ እስክድር ነጋ አፍርሰውታል፤" የሚል ዐይን ያወጣ በውሸት የታጀበ የፈጠራ ወሬ ነዝተዋል፡፡
የቀድሞው የባልደራስ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ በመርህ እና በህግ የመሰረቱትን ፓርቲ በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ እንጂ፤ ባልደራስን የመሰለ ለሕዝብ ጥቅም በመታገል እና ለገዥዎች ባለማጎብደድ የሚታወቅን ፓርቲ አላፈረሱም፡፡ ይልቁንም ሐምሌ 16/2014 ዓ.ም በፃፉት የመልቀቂያ ደብዳቤ፣ ፓርቲው በቀጣይ የበለጠ እንዲጠነክር መልካም ምኞታቸውን ጭምር ገልፀዋል። ይህ ሀቅ በግልፅ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ፣ ባልደራስ ፓርቲን እንደፈረሰ፣ አቶ እስክንድር ነጋ እንዳፈረሱት ተደርጎ የሚነዛው ቅጥፈት እጅግ አስነዋሪ ነው፡፡ እነዚህ ዓይነት የሃሰት ወሬ የሚያናፍሱ ግለሰቦች መሰሪ የሆነ ተልዕኮ ያላቸው ወይም የተሰጣቸው መሆኑን ያመላክታል፡፡ ፓርቲው ሳይፈርስ ፍርሷል ብሎ የፈጠራ ወሬ ማውራት፣ እሳቸው አሜሪካ ቁጭ ብለው በወሬ እየታገሉ የተለያዩ ጫናዎች ሳይበግረው በሃገር ውስጥ እስካሁኑ ሰዓት ድረስ በሰላማዊ መንገድ አገዛዙን እየታገለ ያለን ፓርቲ፣ በዚህም ምክንያት የፓርቲው አመራሮችና በርካታ የፓርቲው አባላት እስራትን ጨምሮ ልዩ ልዩ ጫናዎች እየደረሰባቸውም ቢሆን፣ ለመረጡት የትግል ስልት መስዋዕትነት እየከፈሉለት ያለን ፓርቲ እንዲፈርስ መመኜት የኦህዴድ/ብልፅግናን እና የተላላኪውን የብአዴንን ተልዕኮ ከማራመድ ወጭ ሌላ ተልዕኮ ሊኖረው አይችልም።
በመጨረሻም መላው ሕዝባችን፦
➣ ባልደራስ በአሁኑ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ የአባላት ምልመላ እና የመዋቅር መዘርጋት ስራን እየሰራ እንደሚገኝ፣
➣ እንዲሁም ፓርቲያችን ባልደራስ እንደዚህ ቀደሙ ለህዝብ በመወገን እና አምባገነኑን የኦህዴድ/ብልፅግናን አገዛዝ በመቃወም እየታገለ እንደሚገኝ ለመግለፅ እንወዳለን።
በመሆኑም በዓለም አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የምትገኙ አባሎቻችን እና ደጋፊዎቻችን በሙሉ ይህን የፈጠራ ወሬ እንድታወግዙት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ
01/22/2025
ከስራቸው የተፈናቀሉ ሰራተኞች በአስቸኳይ ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሱ
ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የአንበሳ አውቶቡስ እና የኢትዮ ፖስታ አገልግሎት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት መስሪያ ቤት ሰራተኞች በግፍ ከስራቸው እየተባረሩ መሆናቸውን ባልደራስ ከደረስው የህዝብ ቅሬታ አረጋግጧል፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንት ብቻ ከአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከ480 በላይ ሠራተኞች አለ አግባብ ከስራቸው ሲባረሩ ፣ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ደግሞ እንደዚሁ ተመሳሳይ 450 በላይ ሰራተኞች ተባረዋል፡፡ ለፓርቲያችን የሚደርሱት የሕዝብ ጥቆማዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ ምን አልባትም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ከስራ ገበታቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት የመንግሥት ሰራተኞች ብሔራቸውን በመጥቀስ ፎርም ሞልተው የብቃት መመዘኛ በሚል ፈተና መሰጠት ሲጀመር ፣ሆነ ተብሎ የአማራ ተወላጆችን እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ከስራ የማፈናቀል ተግባር መሆኑን አጋልጠናል፡፡‘’የብቃት መመዘኛ‘’እየተባለ የሚሰጠው ፈተና ለዓመታት ብቸኛ መፈተኛ ቋንቋ ሁኖ ሲያገለግል በቆየው የአማርኛ ቋንቋ ተፈትነው በአንድ መስሪያ ቤት ሲሰሩ የኖሩ ሰራተኞችን ፣በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲፈተኑ የተደረገበት ስልታዊ የማባረሪያ ምክንያት ነበር፡፡ በተጨባጭ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከስራ ገበታቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉት አብዛኞቹ በአማርኛ ቋንቋ ፈተና የወሰዱት ናቸው፡፡
በነገድ ላይ የተመሰረተው አገዛዝ ሆነ ብሎ የአንድን ማሕበረሰብ አባል ለማጥቃት የሚጠቀምበት መሳሪያውም የብሔር ብረሰቦች እና ሕዝቦች የሚባለውን’’ ሕገ መንግሥት’’ ነው፡የኦሕዴድ/ኦነግ/ ብልፅግና ፖለቲከኖች የፌዴራል የመንግሥት መስሪያ ቤት ‘’በአንድ ማሕበረሰብ ተይዟል’’ በሚል ሲለፉት የነበረውን የጥላቻ አካሄድ ተግባራዊ እያደረጉት ነው፡፡ በዚህ ኢ ህገ - መንግሥታዊ አካሄድ የአዲስ አበባን ሕዝብ ጨምሮ የአማርኛ ቋንቋ ተናገሪውን ሕዝብ ግንባር ቀደም የጥቃቱ ሰለባ አድርገዋል፡፡ ይህ አይነቱ አካሄድ ደግሞ በሀገር እና በሕዝብ ላይ ከባድ መከራን ከማስከተል እና ሀገርን ከማውደም የዘለለ ለማንም ቡድን ወይንም ግለሰብ የሚሰጠው ዘላቂ ጥቅም አይኖርም፡፡
ባልደራስ ለአውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ለአስርት ዓመታት ያገለገሉ ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸውን ጎዳና ላይ የሚጥል ውሳኔ በአገዛዙ መሰጠቱን አጥብቆ ይቃወማል፡፡ ፓርቲያችን ባልደራስ በዚህ የግፍ ውሳኔ ተጠቂ የሆኑ ወገኖቻችን ፍትሕ እንዲያገኙ እና ህዝብን አደጋ ላይ የሚጥሉ አሰራሮች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የሚከተሉትን ጥሪዎች ያቀርባል።
1. በግፍ ከስራቸው የተፈናቀሉ ሰዎች በአስቸኳይ ወደ ቀድሞ ስራቸው እንዲመለሱ እናሳስባለን፤
2. ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከስራቸው ከተባረሩ ዜጎች ጎን ቁሞ ሰላማዊ ተቃውሞ እንዲያሰማ ጥሪ እናቀርባለን፤
3. ከስራቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ለሚያደርጉት ማንኛውም ሰላማዊ ተቃውሞ ፓርቲያችን ሙሉ ድጋፉን ይሰጣል፤
4. የሚመለከታችሁ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ የምትስሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና የሚዲያ አካላት የመስራት መብት በፈረንጆች አቆጣጠር በ1966 በተባበሩት መንግሥታት አጠቃላይ ጉባኤ ላይ የፀደቀው የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ (United Nation Universal Declaration of Human Rights) (UNDHR)በአንቀፅ 23 ንዑስ አንቀፅ አንድ (1)ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን የዜጎች መብት እንዲሁም በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚያዊ ፣የማሕበራዊ እና ባህላዊ መብቶች (The International Covenant on Economic, Social and Cultural Rights) (ICESCR) ቃል ኪዳን ውስጥ የተካተተውን መሠረታዊ መብት ግልፅ በሆነ ሁኔታ የሚጥስ በመሆኑ ፣ይህን ህገ ወጥ ድርጊት ለዓለም በማጋለጥ ለመብቶች መከበር እየተደረገ ላለው ሀገራዊ ትግል የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ እና የሰላማዊ ለውጡ አካላት በሙሉ የዜጎችን ከስራ መፈናቀል በፅኑ በመቃወም የሰላማዊ ትግሉ አካል እንድትሆኑ ፓርቲያችን ባልደራስ አበክሮ ይጠይቃል፡፡
የባልደራስ ለአውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
01/21/2025
በአዲስ አበባ ከተማ ከጥምቀት በዓል አስቀድሞ የተጀመረው የወጣቶች አፈና ተባብሶ መቀጠሉን የአይን እማኞች ለባልደራስ ፓርቲ ተናገሩ
ባልደራስ ለአውነተኛ ዴሞክራስ ፓርቲ
13/05/2017 ዓ.ም
የኦሕዴድ ብልፅግና ፖሊሶች በአዲስ አበባ ከተማ ከበዓለ ጥምቀት አስቀድሞ በርካታ ወጣቶችን በማፈን ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች መውስዳቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች አብራርተዋል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች እንዳሉት ከሆነ፣አገዛዙ በአፈና ያሰራቸው ወጣቶች የጥምቀት በዓል በሃይማኖታዊ ስርዓቱ ተከብሮ እንዲውል የሚያስተባብሩ ወጣቶች ናቸው፡፡
ምን ያህል ወጣቶች ታስረው ይሆን የሚል ጥያቄ ባልደራስ ፓርቲ ያቀረበላቸው እማኞች፣በሁሉም ክፍለ ከተሞች ወጣቶች መታሰራቸውን ገልፀው ቁጥራቸው በመቶዎች ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ገልጠዋል፡፡
አገዛዙ የጥምቀት በዓል መንፈሳዊ እና ባሕላዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዳይከበር በሕዝቡ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ወጣቶችን በማፈን ሰውን ከኃይማኖቱ ማራቅ አይቻልም ብለዋል፡፡
ነዋሪዎቹ አክለው እንደገለፁት ከሆነ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በርካታ ወጣቶች ከበዓለ ጥምቀቱ በኋላም ሳይቀር በፖሊሶች እየታፈኑ ይገኛሉ ፡፡
አገዛዙ ወጣቶችን በማፈን እና አማኞች ላይ ያልተገባ ጫና በመፍጠር የፖለቲካ ውድቀቱን የሚያባብስ ተግባር እፈፀመ መሆኑን ነዋሪዎቹ አስገንዝበዋል፡፡
ባልደራስ ለአውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አገዛዙ ወጣቶችን በማፈን በአማኞች ላይ እየፈፀመ ያለውን በደል በፅኑ ይቃወማል፡፡
የኦሕዴድ /ብልፅግና ቡድን ወንበር ላይ የተቀመጠበትን ‘’ህገ -መንግሥት’’ ሳይቀር በሚቃወም መልኩ በአማኞች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እንዲያቆም እና ያፈናቸውን ወጣቶች በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቅ ፓርቲያችን ባልደራስ ያሳስባል፡፡
01/18/2025
እንኳን ለከተራ እና የጥምቀት በአል አደረስዎ!
መልካም በአል!!
በጥምቀት በዓል መዳረሻ በርካታ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ እየታፈሱ መሆኑ ታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ስፍራዎች በተለይ በደማቁ የጥምቀት በአል ወቅት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቁ ወጣቶች እየታፈሱ መሆኑ ታውቋል።
መሠረት ሚድያ የደረሰው መረጃ እንደሚያሳያው እንደ ሽሮ ሜዳ፣ ፈረንሳይ፣ ካዛንችስ፣ ሳሪስ፣ አዋሬ ወዘተ ባሉ ስፍራዎች የሚገኙ ወጣቶች በብዛት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።
ሽሮ ሜዳ አካባቢ ትናንት ማታ ከ30 በላይ ወጣቶችን የሽሮ ሜዳ ፖሊስ አፍሶ እንደወሰዳቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወጣቶቹ የቤተክርስቲያን ጥምቀት አስተባባሪዎች እና ምንጣፍ የሚሸከሙ ልጆች መሆናቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በዛሬው እለት ሳሪስ አዲስ ሰፈር እና ብሄረ ፅጌ አካባቢ ለጥምቀት በአል የተሰቀሉ ማስዋቢያዎችን ፖሊስ በሀይል ያነሳ ሲሆን ፤ ሰቅላችኋል የተባሉ አንዳንድ ወጣቶችም እንደታሰሩ ታውቋል።
ከዚህ በፊት በየመንገዱ የሚሰቀሉ እና የኦርቶዶክስ አርማ ያለበት ባንዲራ ጭምር በፖሊስ በበርካታ ስፍራዎች እንዲወርድ እየተደረገ መሆኑን ሰምተናል።
ማምሻውን ከፖሊስ ምላሽ ለማግኘት ያረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ፎቶ: ፋይል
መረጃው የመሰረት ሚዲያ ነው
01/08/2025
የብልፅግናን መንግሥት ገፍትሮ ለመጣል በቅርብ ርቀት ያነጣጠረው የሙስና ኢምፓየርና ሌብነት - ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ Balderas for true democracy % ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች ዋነኛው ተፎካካሪ ፓርቲ ነው። ፓርቲው የተመሰረተው በታዋቂው ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድ....