የኢትዮኤርትራ ጉዳይ EthioEritrea Affairs

የኢትዮኤርትራ ጉዳይ  EthioEritrea Affairs

Share

What is the way forward in the struggle for Democracy & Justice so that it can be achieved, and Eritrea or Ethiopia can be a better place to live in...?

The purpose of this "facebook" page is to promote Democratic Principles within Eritreans or Ethiopians by bringing issues that concern Eritrea or Ethiopia, the people from within, or the Diaspora Eritreans or Ethiopians. These issues are discussed by applying Democratic Principles. It is a Discussion-Forum of which every Eritrean or Ethiopian is expected to take part in the discussion and express

Photos from የኢትዮኤርትራ ጉዳይ  EthioEritrea Affairs's post 04/16/2025

ጀግኖቹ!

04/16/2025
Photos from የኢትዮኤርትራ ጉዳይ  EthioEritrea Affairs's post 04/12/2025

“ቀይ ባህር ለኢትዮጱያ የህልውና ጉዳይ እንጂ ቅብጠት አይደለም” ጠ/ሚ ዓብይ አህመድ

ሰላም፣ አጋርነት፣ መተባበር፣ መከባበር፣ መተሳሰብ (ዲሞክራሲ እና ፍትህ) ለኢትዮጱያም ለኤርትራም ህልውናቸውን ለማስቀጠል መሠረትም ዋስትናም ናቸው፡፡ ለብልጽግናቸውም ዋንኛ መንገዶች ናቸው፡፡ ይህን አንድ የሆነ ህዝብ እንደ ሁለት ህዝብ መታየቱ፣ በሁለት አገር ውስጥ መገኘቱ፡ ጥቅም እንጂ ጉዳት ከቶ ሊኖረው አይችልም፡፡ ይህን በጥልቀት እና በስፋት ለመረዳት፡ ትኩረት ሰጥቶ አቅጣጫን የሚያስይዝ፡ አንድ ቅን የሆነ፣ ባለ ራእይ፣ አርቆ አሳቢ፣ አስተዋይ መሪ በኢትዮጱያ ውስጥ መከሰት አለበት፡፡ ድሮውም ቢሆን ይህን አንድ የሆነ ህዝብ ለሁለት እንዲከፈል፣ ሁለት አገር ሁኖ በሁለት መንግስታት እንዲወከል ያደረጉት እና የገዥዎችን ጫና ለመሸከም ያበቁት የኢትዮጱያ መሪዎች መሆናቸው መዘንጋት የለበትም፡፡ ታሪክ ምስክር ነው፡፡

የኤርትራ ነጻ አውጪ ድርጀት ያካሄደውን ተጋድሎ እና ያከናወነውን ስኬት አሳንሼ ስለአየሁት አይደለም፡፡ ያለ የኢትዮጱያ መሪዎች የተሳሳተ ውሳኔ፣ ያልተቀደሰ እርምጃ፣ የተካሄደ ግፊት የነጻ አውጪ ድርጅትም አይመሠረትም ነበር፣ የ'30 ዓመቱ ለነጻነት የተደረገው መራር ተጋድሎ እና ጉዙፍ መስዋእትነትም ባላስፈለገ ነበር፡፡ የኢትዮጱያ እና የኤርትራ አሁን የደረሰሱበት ሂደት በተከናወነው የስበትና የግፊት ሃይሎች (push and pull strategic forces) ውጤት ነው፡፡ ከአንድ ወደ ሁለት አገር መሆንን የግፊት ሃይል ሳይታከልበት በስበት ሃይል ብቻ ሊሆን ወይም በቀላሉ ሊተገበር እንደማይችል ልብ ሊባል ይገባል፡፡ አሁንም ቢሆን የኢትዮጱያ መሪዎች በሰበብ በአስባቡ ግፊታቸውን እንደቀጠሉበት ነው፡፡ የምሁር አካሉም በባለስልጣናቱ በጥሩ ዓይን ለመታየት ታሪክን እያጣቀሰ ጥንት አሰብ የኛ የኢትዮጱያ ነበረች እያለ ከማምታታት ወደኋላ አላለም፡፡ ምሁራኑ በአፍሪካ የአገራት ዳር ድንበር ቅኝ ገዢዎች ባሰመሩላቸው መሆኑንን ትኩረት አይሰጡትም፡፡ የኤርትራ ነጻ አገር የመሆንን ስር መሠረቱ ይህ የቅኝ ገዢዎች መስመር መሆኑን ሊያስታውሱት አይሹም፡፡ ቀይ ባህርን እንደ የኢትዮጱያ የህልውና ጉዳይ አድርጎ መስበክ ከምያካሂዱት ግፊቶች አንዱ ነው፡፡

ለነጻነት በተደረገው ተጋድሎ የ'30 ዓመት ጦርነቱ እና ውግያው የ'ቀይ ባህር ጉዳይንም ያካተተ እንደነበር እንዴት ይዘነጋል፡፡ የኢትዮጱያ መሪዎች የቀይ ባህር የባለቤትነት ጥያቄን ሲያነሱ፡ በአንድ በኩል የሁለቱንም አገር ህዝቦችን ሰላማቸውን ለመንሳት ሲሆን በሌላው በኩል አልጸና ያለውን መንግስታዊ ስልጣንን ለማጽናት ውግያ ከፍተው መተንፈስ እንዲችሉ እና የስልጣናቸውን እድሜ ለማራዘም ብለው መሆኑን ብሩህ ነው፡፡ የገዢዎች ህልም ገና ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

ህዝቡን ሰላሙን ሲነሱት፣ በውግያ እና በጦርነት ወሬ ሲያጨናንቁት፣ ታሪክ እያጣቀሱ የአገር አንጡራ ሃብት ተውስዶብናል፣ ተዘርፈናል፣ የተውሰደብን የባህር ወደብ የህልውናችን ምሰሶ ነው እያሉ ሲያዋክቡት ያደረሱበትን ጫና ትቶ ትኩረቱ እና ሃሳቡ በአገር፣ ለአገር ስለ አገር እንዲሆን፡ ካላቸው ስልታዊ እቅድ ተነስተው ነው፡፡ የህዝቡን ትክረት አስቀይሰው ስልጣናቸውን ለማጽናት ካላቸው ጥልቅ ፍላጎት በመነሳት ነው፡፡

የኢትዮጱያ መሪዎች ጥያቄ ወደብን የመጠቀም መብት እንጂ የባለቤትነት መብት ጥያቄ መሆን ከቶ አይችልም፡፡ የባለቤትነት ጥያቄ የመሬትን የስበት ሓይል እንደመጋፋት ያህል ይቆጠራል፡፡ ህዝቡን ለማደናገር እና ለውግያ ለማነሳሳት ተብሎ በካድሬዎቻቸው፣ በተቀጣሪ የዜና ማእከናት፣ በማህበራዊ የሚድያ ማእከናት በኩል የማይጠቅሱት የዓለም ተሞክሮ እና የዓለምአቀፍ ህጎች የሉም፡፡ በተለይ የአሁኑ መሪዎች ገደባቸውን እና ልካቸውንም ጠንቅቀው የሚያውቁ አይመሱም፡፡ "might is right" እያሉ ሲደሶኩሩ ይሰማሉ፡፡ "right is might" መሆኑንም ሊገነዘቡት ይገባል፡፡

ኤርትራ ለኢትዮጱያ ቀይ ባህርን እንዳትጠቀምበት የከለከለችበት ወቅትም ሆነ ሁኔታ የለም፡፡ የኢትዮጱያ መሪዎች "ቀይ ባህራችሁን ግመሎቻችሁን ውሃ አጠጡበት" በማለት የተዉት በራሳቸው ፍላጎት እና ውሳኔ ነው፡፡ ከኢትዮጱያ ህዝብ ጥቅም ለራሳቸው ስሜታዊ ባህሪ መታዘዝን እና የእልህ፣ የቁጭት ግባቸውን ማሳካትን ነው የመረጡት፡፡ "የኤርትራን ወደብ በመጠቀም ኢትዮጱያ የምታገኘው ጥቅም ቢኖርም፡ ይበልጥ ኤርትራን ስለሚጠቅማት፡ የጁቡትን ወደብ በከባድ ዋጋም ቢሆን ከፍለን ለመጠቀም መርጠናል" ያሉት የኢትዮጱያ መሪዎች ናቸው፡፡

የኢትዮጱያ መሪዎች ስልጣናቸውን ለማጽናት ሲሉ በኤርትራ እና በህዝቧ ቆምረዋል፡፡ ሲያሻቸው ለቀኝ ገዢዎች አሳልፈው ይሰጧታል፣ በሌላ ግዜ በሰበብ በአስባቡ ጸብ ይጠምቃሉ፣ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ይረጫሉ፣ እንደ ታሪካዊ ጠላት አድርገውም ይፈርጃሉ፡፡ ያለንን ሓይል ተጠቅመን አሰብን በእጃችን እናስገባታለን እያሉም ይፎኩራሉ፡፡ አሰብን በሃይል ወስደው ቀጠናው ሰላም ሆኖ የሚቀጥል ይመስላችዋል፡፡ በሰላም እጦት በሚከብሩ እና ሰላም ሲሰፍን በሚከስሩ የዓለማችን ተዋንያን እጅ እንደሚወድቁ እና አንዴ ከወደቁ በኋላ መውጭያ እንደማይኖራቸው ያልተገነዘቡ፣ ያልተረዱ የኢትዮጱያ ባለስልጣናት በገፍ ናቸው፡፡

ቀዳማዊ ኋይለስላሴ ኤርትራን ከኢትዮጱያ ጋር ሲያዋህዷት፡ ገፊ ምክንያቱ የሚከተለው ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ የካቢንያቸው አባላት የኤርትራን ከኢትዮጱያ ጋር በፌደራል ስርዓት ማዋቀር እንደ አንድ የሙከራ ስልት በማሰብ በቀጣይ በመላው ኢትዮጱያ የፌደራል ስርዓት ለማዋቀር አስቻይ ሁኔታን ይፈጥርልናል የሚለውን ተጓዥ ግንዛቤ ይነጋገሩበት ስለነበር፡ ቀ.ኋ.ስ. ይህን ሃሳብ ስር ሳይሰድ በአጭር ለመቋጨት ሆን ብለው ኤርትራን ከኢትዮጱያ ጋር ለማዋሃድ ተቻኮሉ፡፡ ምክንያቱም በዚያን ግዜ በኢትዮጱያ ውስጥ የፈዴራል ስርዓት ህሳቤው የ'ቀ.ኋ.ስ.'ን የስልጣን ጥልቀቱን እና ስፋቱን የሚፈታተን በመሆኑ ነበር ብዬ አስባለሁኝ፡፡ ይህ ተጽፎና ተስምቶ ባያውቅም ሁልግዜ በአእምሮዬ የሚመላለስ መላምት ነው፡፡ የ'ቀ.ኋ.ስ. የማዋሃድ እርምጃ በኤርትራ ውስጥ የትጥቅ ትግል እንዲጀመር አስገድዷል፡፡

የደርግ መንግስት ያካሄድ በነበረው የቀይ ኮኮብ ዘመቻ እና የቀይ ሽብር ዘመቻ፡ አብዛኛውን የኤርትራ ወጣት የነጻነት ትግሉን እንዲቀላቀል አስገድቶታል፡፡ ወላጆችም የልጆቻቸውን ሬሳ መንገድ ላይ ተጥሎ ከማየት ከከተማው እንዲወጡላቸው ግፊት ያደርጉ እንደነበር ሰምቻለሁኝ፡፡በተጨማሪም ደርግ በተለይ በውጣቶች ላይ ያደርግ በነበረው ግፊት እና የነጻነት ተጋዮች በሚያካሄዱት የነበረው የስበት ፕሮፖጋንዳ፡ የነጻነት ትግሉ እንዲደራ አድርጎታል፡፡

አሁንም የአብይ መንግስት ካለፉት መሪዎች ሳይማር፡ ስልጣኑን ለማራዘም ይጠቅመኝ እንደሆን በማለት፡ ከኤርትራ እና ከህዝቧ ጋር ጸብ ለመጥመቅ ዳርዳር እያለ ነው፡፡ በዚህ ከቀጠለ የመጨረሻ ውጤቱ የሚሆነው እንደ ጸሃይ የበራ እንደ ኮኮብ የደመቀ ውጤት ነው፡፡ የአብይም ህልውናም የሚያከትምለት የሚሆን ነው፡፡

በሰበብ በአስባቡ በዚህ ህዝብ መካከል ጥላቻ ስር እንዲሰድ አታድርጉ፣ እርስ በእርሱ አታፋጁት፣ እስከአሁን በሰላም እጦት የህይወትን እፎይታ ናፍቅዋል እና የጦርነት እና የውግያ ጭምጭምታ አታስሙት፡፡ የሁለት አገር ሰው ስለሆነ በጥላቻ አይን እንዲተያይ አታድርጉት፡፡ መንግስት ይመጣል ይሄዳል፡፡ ህዝቡ ለዘላለም ጎረቤት ነው፣ ወንድማማች ነው፣ የተዋለደ ነው፣ የተጋመደ ነው፣ መቼም ቢሆን የሚለያይ ህዝብ አይደለም፡፡ ሰላሙን ስጡት!!!

Raphael A.
April 06, 2025

Connecting Dots ክስተቶችን ማስተሳሰር 03/28/2025

2000 ሳብስክራይብ ያደረጉ ስንደርስ በድምጽ እና በቪድዮ ለመከሰት አቅደናል፡፡ ትምህርት አዘል ጉዳዮችን፡ በምስራቅ አፍሪካ እና ድያስፖራን በሚመለከት የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የባህላዊ፣ የፖለቲካዊ፣ የህግ፣ የስነምግባር፣ ጉዳዮችን የምንመለከት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ከስር ያለውን ሊንክ በመጭን ሳብስክራይፕ እንድታደርጉ በትህትና እንጠይቃለን፡፡

Connecting Dots ክስተቶችን ማስተሳሰር This channel explores affairs of communities in politics, economics, social, technological, environmental, and legal. Their history, challenges, opportunities, and the way forward for all involved is explored, analyzed, and determined. The falsehood that has been pressed into the minds of members of...

03/01/2025

1-Ethiopia's Chant: "It is My Dam… It is Our Dam… It is Our Water"

A Historical and Contextual Analysis

Introduction

Since 2019, Ethiopians have been fervently chanting “it is my Dam… it is our Dam… it is our water,” a chant that signifies not just a recent awakening but a long-standing awareness and assertion of their rights to the Blue Nile River and the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD). This powerful slogan encapsulates a national sentiment that dates back decades, if not centuries.

Early Aspirations and Historical Context

The dream of harnessing the Blue Nile, known locally as Abbay, is not a new one. The first cornerstone for the construction of a dam was laid by Emperor Haile Selassie in 1951—72 years ago. This historical milestone marked the beginning of Ethiopia's journey towards utilizing its natural resources to foster development and economic growth. Despite the ambitious start, the actualization of this dream faced numerous impediments due to political, social, and economic disruptions.

The Blue Nile: A National Resource

The Blue Nile, a river that originates in Ethiopia, is more than just a body of water for the Ethiopian people; it is a vital natural resource. Ethiopia's claim to the Blue Nile is rooted in geographical and hydrological realities. However, this claim has been contested by Egypt, which has historically benefited from the Nile's waters. The chanting by Ethiopians—asserting their ownership and rights to the dam and the water—stems from a deep-seated need to rectify historical inequities in the utilization of the river.

Geopolitical Tensions

The construction of the GERD has magnified geopolitical tensions, particularly between Ethiopia and Egypt. Egypt's stance has been one of significant concern over the potential reduction in water flow downstream. This concern has led to strenuous diplomatic engagements and, at times, aggressive rhetoric. Egyptians claim a historical right to the Nile, often backed by colonial-era treaties which Ethiopia was not a party to. The Ethiopian chant is, thus, a direct response to Egypt’s claims and its historical dominance over the Nile's waters.

Years of Disruptions and Challenges

The realization of the GERD project has been delayed by numerous internal and external disruptions. Over the past 55 to 60 years, Ethiopia has faced continuous turmoil, which has significantly hindered its development. These disruptions include:

• The 30-year-long war with Eritrean guerilla fighters, which led to Eritrea's independence.

• The revolution that overthrew Emperor Haile Selassie.
• Conflict with Somalia.

• Decades-long conflict with the Tigray People's Liberation Front (TPLF).

• Post-independence war with Eritrea.
Currently, Ethiopia is still grappling with internal conflicts, particularly in the north, west, and north-western regions. Ethnic-based killings and displacements have become alarmingly widespread.

Egypt's Role in Ethiopia's Instability

The assertion that Egypt has played a role in destabilizing Ethiopia is a significant one. According to Daniel Kendie (1999), one of Egypt’s longstanding foreign policy objectives has been to destabilize Ethiopia. This assertion adds another layer of complexity to the ongoing dispute over the Nile waters and the GERD. The impact of external interference in Ethiopia’s internal affairs has had far-reaching consequences, stalled development and perpetuating a cycle of poverty and conflict.

The GERD: A Beacon of Hope

Despite the myriad challenges, the GERD stands as a beacon of hope for Ethiopia. It symbolizes the nation's resilience and determination to harness its resources for the betterment of its people. The dam is expected to significantly boost Ethiopia’s hydroelectric capacity, providing much-needed energy for development, and improving the quality of life for millions of Ethiopians.

The Path Forward

Ethiopia’s journey towards fully realizing the benefits of the GERD is far from over. It requires continued resilience, strategic diplomacy, and a unified national effort to overcome both internal and external challenges. The chant “it is my Dam… it is our Dam… it is our water” is not just a slogan but a rallying cry for justice, equity, and national sovereignty.

Conclusion

The construction of the GERD is more than an engineering feat; it is a testament to Ethiopia’s enduring spirit and its quest for self-determination. The historical and ongoing challenges faced by the nation highlight the complex interplay of internal strife and external pressures. However, the unwavering determination of the Ethiopian people to assert their rights to the Blue Nile and the GERD is a powerful reminder of the importance of natural resource sovereignty. As Ethiopia continues to chant in unison, the world watches a nation steadfastly move towards a brighter and more self-reliant future.

Raphael A.
May 28, 2021

Call now to connect with business.

Eritrea First versus People First.docx 01/19/2025

https://docs.google.com/document/d/1few2oyt01HJx5Hnwor1GYxXN9ZIzngoH/edit?fbclid=IwY2xjawH5fjJleHRuA2FlbQIxMQABHYoSFKvf5FF-w-Xl5Ly5yVZn2NEYNaj4abIk2vLx4YsjtKp90ESMg9FSIw_aem_J02yBebiOVUpibreg5WBDg

Eritrea First versus People First.docx Eritrea First versus People First: A Debate on Prioritization Analyzing Competing Ideologies for Eritrea's Future Introduction The political debate surrounding the prioritization of "Eritrea First" versus "People First" has generated considerable discourse within Eritrean communities and beyond....

The role of history in Ethiopia's conflict 01/19/2025

https://docs.google.com/document/d/1i3VJIgTzzz1hKhomGXea1T1cfKRXWnCwWzhMu_LUAUc/edit?fbclid=IwY2xjawH5fEJleHRuA2FlbQIxMQABHb9wfVZImeaZEvRPswBj_I6qarrVTPKyv3GY1bFosjFiHJS_Et83b8M63Q_aem_vI-_KM241dl1gBKHw5XDnQ&tab=t.0

The role of history in Ethiopia's conflict The Role of History in Ethiopian Conflicts and Disagreements Understanding the Past to Build a Better Future Introduction Ethiopia, a country with a rich and ancient history, faces numerous conflicts and disagreements. Among the many causes of such disputes, the way history is written, read, and ...

Want your business to be the top-listed Government Service in Toronto?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Toronto
Toronto, ON
M9W6Z4

Opening Hours

Monday 5:30pm - 9:30pm
Tuesday 5:30pm - 9:30pm
Wednesday 5:30pm - 9:30pm
Thursday 5:30pm - 9:30pm
Friday 5:30pm - 9:30pm
Saturday 8:30am - 1pm
Sunday 8:30am - 1pm