የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት
ይህ የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ህጋዊ የፌስቡክ ገፅ ነው። ገፁን ላይክና ሼር በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ።
14/04/2026
ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች የሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆኑ የሀገር ባለቤት መሆናቸውን በጽኑ ያምናል።
ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያ ሀገራችን የወጣቶች ሀገር እንደመሆኗ ወጣቶች ላይ በሁሉም የዕድገት ዘርፎች በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል።
ባለፉት የለዉጥ ዓመታት ወጣቶች በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ያደረጉ ሥራዎች በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ተሰርቷል። ከተሰሩት ሥራዎች መሀከል
✍️በፖለቲካና ዉሳኔ ሰጪነት
የአመራር ተተኪነት፦ በየደረጃው በሚገኙ የመንግስትና የፓርቲ መዋቅሮች ዉስጥ ወጣቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡ ተደርጓል። ይህም የአመራር ትዉልድ ቅብብሎሽ በሚል እሳቤ ወጣቶች በከፍተኛ የዉሳኔ ሰጪነት ቦታዎች ላይ እንዲቀመጡ አስችሏል።
✍️በማህበራዊና በጎ ፈቃድ አገልግሎት
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች በየዓመቱ በአረንጓዴ አሻራ፣ ደም በመለገስ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት በመጠገንና በትምህርት ድጋፍ ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ተደርጓል። ይህም የወጣቱን ማህበራዊ ሃላፊነትና ሀገራዊ ፍቅር አሳድጓል።
✍️በሰላም ግንባታና ሀገራዊ ምክክር
ወጣቶች የሀገሪቱን ሰላም በማስከበርና በሀገራዊ የምክክር ሂደት ውስጥ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው፣ የግጭት አፈታትና የሰላም ግንባታ ስልጠናዎችና መድረኮች ተመቻችቷል።
የፓርቲው ስትራቴጂ ወጣቱን ከ"ተቀባይነት" ወደ "ፈጣሪነት" እና "መሪነት" ማሸጋገር ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፣ ይህም በሂደት ላይ ያለና ተጠናክሮ የሚቀጥል ተግባር እንደሆነ ይገለጻል።
✍️በኢኮኖሚና በስራ ዕድል ፈጠራ
በከተማና በገጠር ለሚገኙ ወጣቶች የብድር አገልግሎት፣ የመስሪያ ቦታና የቴክኒክ ስልጠና በማመቻቸት በርካታ የሥራ እድሎች ተፈጥረዋል።
!
13/04/2026
09/04/2026
የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሳድሁን ለስቅለት እና ትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት እና ፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን!
የስቅለት እና ትንሳኤ በዓል ጨለማው አልፎ ብርሃን የወጣበት፣ ሞት በህይወት የተሸነፈበትና የሰው ልጅ ከፈጣሪው ጋር የታረቀበት ታላቅ የድል ቀን ነው። ይህ በዓል ከምንም በላይ የሚያስተምረን ፍቅርን፣ ትዕግስትንና ለሰው ልጆች ሁሉ የሚተርፍ በጎነትን ነዉ።
ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍቅር ሲል ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ ሁሉ፣ እኛም ይህንን ታላቅ በዓል ስናከብር በመካከላችን ያለውን አንድነት በማጠናከርና እርስ በርስ በመተጋገዝ ሊሆን ይገባል።
በዓሉን ስናከብር በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ የሚገኙ አቅመ ደካሞችንና አረጋዊያን ታሳቢ በማድረግ ካለን በማካፈል እንድናከብር ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
በዓሉ የሰላም፣ የጤና የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን!
አቶ ሳሙኤል ሳድሁን
የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
ሚያዝያ 1/2018 ዓ.ም
08/04/2026
04/04/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. አራዘመ
በምርጫዬ የሞባይል መተግበሪያ ራስዎን ለመራጭነት ይመዝግቡ!
● ከአፕ-ስቶር:- https://url-shortener.me/IHPC
● ከፕለይ-ስቶር https://url-shortener.me/IHPF ላይ በማውረድ ወይም
●በድረ-ገጽ አማራጭ (በቀጥታ) https://url-shortener.me/IHPH ይመዝገቡ።
የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ተግባራዊ የሚደረግባቸውን ምርጫ ጣቢያዎች በአስተያየት መስጫ ሣጥን ውስጥ ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ያገኛሉ። በቀሪ ምርጫ ጣቢያዎች የማንዋል የምዝገባ ሥርዓት ተግባራዊ ይሆናል።
02/04/2026
በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ከወረዳዉ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አባላት ጋር የ2018 ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የምርጫ ምልክት/ማንፌስቶ ማስተዋወቅ እና የክልል እና የፈደራል ዕጩዎችን የማስተዋወቅ መድረክ ተካሄደ።
መጋቢት 24/2018 ዓ.ም
በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ከወረዳዉ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አባላት ጋር የ2018 ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የምርጫ ምልክት/ማንፌስቶ ማስተዋወቅ እና የክልል እና የፈደራል ዕጩዎችን የማስተዋወቅ መድረክ ተካሄዷል።
የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እሴይ ይርጉ ወጣቶች በሀገር ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ኃላፊነት አለዉ ካሉ በኋላ ወጣቱ ትዉልድ ሀገርና ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ፣ በእድገት ጎዳና ላይ ያለችን ሀገር ደግፎ የኢትዮጵያን ብልጽግና ከማረጋገጥ ረገድም ጉልህ ሚና አለዉ ብለዋል።
አክለዉም አቶ እሴይ ይርጉ 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ፍትሃዊና ደሞክራሲያዊ እንድሁም ቅቡልነት ያለዉ ሆኖ እንድጠናቀቅ ወጣቱ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው እንድሁም የምርጫ ካርድ በመያዝ የዜግነት ግደታቸዉን እንድወጡ አሳስበዋል።
የጎርካ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አገዜ አበልም በበኩላቸዉ ካለን የህዝብ ቁጥር ከፍተኛዉን ድርሻ የሚይዘው የወጣቱ ክፍል ነዉ ካሉ በኋላ ወጣቱ ትዉልድ የሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ እንደ ሞተር የሚያገለግል ኃይል ነዉ ብለዋል።
አክለዉም የጎርካ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊው ወጣቱ ከለዉጡ መንግስት ጎን በመቆም
የአጭር ጊዜ፣የመካከለኛ ጊዜና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ያለዉንና የኢትዮጵያ ከፍታን ለማረጋገጥ እየተጋ ያለዉን ፓርቲ በመደገፍ የሀገራችንን ብልጽግና ማረጋገጥ አለበት ስሉ አሳስበዋል።
Cliquez ici pour réclamer votre Listage Commercial.
Emplacement
Type
Contacter l'entreprise
Téléphone
Site Web
Adresse
Democratic Republic Of The
