FDRE Ministry of Education

FDRE Ministry of Education

Partager

Education Is The Base Of Development. Education For All

በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችንለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ (2018) ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈ 18/11/2025

ማስታወቂያ
ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
የትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ በ2 የተለያዩ ጉዳዮች ማለትም፤
1. በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ ረቂቅ ደንብ ሊንክ = https://forms.gle/HisAZoyTpmo1ZFCA6
2. የተማሪዎች የሥነ-ምግባር መመሪያ (የመጀመሪያ ረቂቅ) ሊንክ =
https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6

በመሆኑም ሰነዶቹን በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
 ለመጀመር ከእያንዳንዱ ረቂቅ መመሪያ ፊት ለፊት ያሉትን ሊንኮች መጫን፤
 በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
 ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ትምህርት ሚኒስቴር

በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችንለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ (2018) ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈ ማስፈንጠሪያ (Link)

Photos from Ministry of Education  Ethiopia's post 31/10/2025
Ministry of Education Portal 29/10/2025

ማስታወቂያ

የRemedial ፕሮግራም ምደባ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤

በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች
1. Website: https://student.ethernet.edu.et
2. Telegram bot:

ትምህርት ሚኒስቴር

Ministry of Education Portal Student Admission and Placement Portal

Photos from FDRE Ministry of Education's post 27/10/2025

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ መሰረት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ነጥብ ያመጡና በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎችን ምደባ አከናውኗል።

በዚህም መሰረት ዩኒቨርስቲዎች ሚኒስቴሩ የመደበላቸውን ተማሪዎች መቀበል መጀመራቸውን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አለምሸት ተሾመ እንዳሉት፥ በዩኒቨርስቲው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከ5 ሺህ 5ዐዐ በላይ ተማሪዎች ተመድበዋል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ለመማር ማስተማር ሂደቱ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል ብለዋል።

በተመሳሳይ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን ከ1ሺህ 700 በላይ አዲስ ተማሪዎችን እየተቀበለ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዲን ጊዜው ፈጠነ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በዩኒቨርሲቲው በ2017 የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትለው ያለፉ ከ600 በላይ ተማሪዎችን እየተቀበልን እንገኛለን ነው ያሉት።

ዩኒቨርሲቲው ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የወሰደውን የቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮግራም "የሸዋ የቃል ኪዳን ቤተሰብ" በሚል በዚህ ዓመት መተግበር እንደሚጀምር አስረድተዋል።

በዚህም ተማሪዎችን ከቃል ኪዳን ቤተሰቦች ጋር የማረካከብ ስራ በቅርብ ቀናት ውስጥ ይጀመራል ነው ያሉት።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ ተንሳይ ኃይሉ በበኩላቸው፥ ዩኒቨርሲቲው በመደበኛና የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን የሚከታተሉ 4 ሺህ 67 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መቀበሉን ጠቁመዋል፡፡

Photos from FDRE Ministry of Education's post 21/10/2025



የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ከዘንድሮ ዓመት ጀምሮ የክልሉ የትምህርት ቋንቋ #አማርኛ እንዲሆን እና ሰባት የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች " እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት" እየተሰጡ እንዲቀጥሉ ወስኗል።

" ጊዜያዊ ነው " የተባለው ይህ አሠራር በዚህ ዓመት በቅድመ መደበኛ (ኬጂ) እና በአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የሚተገበር ሲሆን በየዓመቱ ወደ ሌሎች የክፍል ደረጃዎች እያደገ እንደሚሄድ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ የሆነው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፤ በክልሉ በሚነገሩ አፍ መፍቻ ቋንቋዎች ትምህርት መስጠት የጀመረው በ2001 ዓ. ም. ነበር።

የመማር ማስተማሪያ ቋንቋ ሆነው ከሚያገለግሉት አፍ መፍቻዎች መካከል ፦
- ቤኒሻንጉልኛ፣
- ጉምዝኛ፣
- ሽናሽኛ እና ማኦኛ ይገኙበታል።

ኮሞኛ፣ ጓምኛ፣ ኦሮምኛ እና አማርኛም ትምህርት ይሰጥባቸው ከነበሩ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች መካከል ናቸው።

በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎች ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ሒሳብ እና የሳይንስ ትምህርት አይነቶችን በእነዚህ ቋንቋዎች የሚማሩ ሲሆን ሰባተኛ ክፍል ላይ የመማር ማስተማሪያ ቋንቋው እንግሊዘኛ ይሆናል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ ላሉ የወረዳ፣ ልዩ ወረዳ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በጻፈው ደብዳቤ ከዘንድሮ የ2018 ትምህርት ዘመን አንስቶ ይህ አሠራር መቀየሩን አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ ውሳኔው መተላለፉን ለቢቢሲ አማርኛ አረጋግጠዋል።

በቢሮ ኃላፊው የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው ላለፉት 17 ዓመታት ተግባራዊ ሲሆን የቆየው አሠራር የተቀየረው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ካቢኔ ባለፈው ወር መስከረም 10/2018 ዓ. ም. ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነው።

ከሁለት ሳምንት በፊት በመስከረም 21 ለክልሉ ትምህርት ቢሮ የደረሰው የካቢኔው ውሳኔ የተመሠረተው፤ በ2017 ዓ. ም. በተደረገ ጥናት ላይ እንደሆነ ተጠቅሷል።

ደብዳቤው፤ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎቹ በመማሪያ ማስተማሪያነት ጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ "የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዳልተቻለ" ይገልጻል።

ይህ የሆነውም "ከሚያስፈልገው የመምህራን ቁጥር እና ብቃት፣ ከግብአት እና ከሌሎች ችግሮች" ጋር በተያያዘ እንደሆነ ይገልጻል።

የትምህርት ቢሮው ኃላፊው ዶ/ር ተመስገን፤ " መምህራን በቂ አይደሉም፤ እንደውም የሉም ማለት ይቻላል። ያሉትም ላይ የአቅም ማነስ አለ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ሕጻናት በራሳቸው ቋንቋ በሚማሩበት ጊዜ አካባቢውን በአግባቡ ይረዳሉ፣ የትምህርት ይዘቱንም ይረዳሉ ተብሎ ይታሰባል " ያሉት ዶ/ር ተመስገን፤ " ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ሊያስተምር የሚችል፣ በራሱ ብቁ የሆነ መምህር ሲኖር ነው " ብለዋል።

ቋንቋዎቹን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ለመስጠት የሚሆን የመምህር እጥረት አለመኖሩን የሚናገሩት ኃላፊው፤ ሒሳብ እና ሌሎች የሳይንስ ትምህርቶችን በአፍ መፍቻ ለማስተማር የተመረቀ መምህር ግን አለመገኘቱን ገልጸዋል።

" ያሉትም ቢሆን በሌላ ከተማሩ በኋላ ሁለት ወር ወይም አንድ ወር ቋንቋ ትርጉም እና ተያያዥ ሥልጠና የወሰዱ ናቸው " ብለዋል።

ይህ ጉዳይ " የተማሪዎች ውጤት ላይም ተጽዕኖ እያሳየ " መምጣቱን አክለዋል።

ቢሮው፤ ይህንን " ችግር ለመፍታት እና የተማሪዎችን የመማር ውጤት ለማሻሻል በ2017 ዓ. ም. ያጠናውን " ጥናት ለክልሉ ካቤኒ እንዳቀረበ ደብዳቤው ያስረዳል።

ካቤኒውም፤ " የክልሉ አቅም እስኪጎለብት እና ያሉ ችግሮች በሂደት እስኪፈቱ ድረስ በክልሉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መማሪያ ማስተማሪያ ቋንቋ አማርኛ እንዲሆን " ወስኗል ተብሏል።

21/10/2025
Photos from FDRE Ministry of Education's post 20/10/2025

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጲያ UNFPA ተወካይ ጋር ተወያዩ።
-------------------------- // -------------------------

(ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጲያ የUNFPA ተወካይ Mr. Sk Kouameን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚሁ ጊዜ በኢትዮጲያ UNFPA ተወካይ የሆኑት Mr. Sk Kouame UNFPA በሴቶች ትምህርት በተለይም ለሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶችን በማቅረብ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም ይህንን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለክቡር ሚኒስትሩ አብራርተውላቸዋል።

UNFPA ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሌሎች ጋር በመተባበር የሴቶችን የትምህርት ሁኔታ በማመቻቸት ረገድ የበለጠ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚፈልጉም ገልጸውላቸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ በበኩላቸው UNFPA ውስን በሆነ መልኩ ለሴት ተማሪዎች ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

አክለውም በቀጣይ ከእንዲህ ዓይነት ውስን ድጋፎች ተላቆ በራስ አቅም የሴቶችን ንጽህና መጠበቂያ በማምረት ለኢትዮጵያም ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅም ሥራ መስራት እንደሚገባ ለካንትሪ ዳይሬክተሩ አብራርተውላቸዋል።

08/10/2025

የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ምደባ መመልከቻ ድረገጽ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረትም የዩኒቨርሺቲ ምደባ እየተጠባበቁ የሚገኙ ተማሪዎች በሚከተሉት ሊንኮች መመልከት ይችላሉ፡፡

ድረገጽ፥ https://student.ethernet.edu.et

ቴሌግራም ቦት

14/09/2025

"ወላጆች ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶችን መጠየቅ አለባቸው"

- ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ
++++++++++++++

l ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች አካባቢ ያሉ ወላጆች ትምህርት ቤቶቹን መጠየቅ አለባቸው ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ገለፁ።

ሚኒስትሩ በ2017 የትምህርት ዘመን የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በዘንድሮ 12ኛ ክፍል ፈተና 1 ሺህ 249 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም ብለዋል።

ይህም የተማሪዎች ጥፋት ብቻ አለመሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ወላጆች ልጆቻቸው ለምን ማለፍ እንዳልቻሉ ትምህርት ቤቶቹን መጠየቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ይህም ትምህርት ቤቶች ላይ ጫና በመፍጠር የተሻለ የመማር ማስተማር ስርዓትን መዘርጋት እንዲቻል ነው ብለዋል።

ትምህርት ቤቶችን እንደወላጅ ሆኖ የሚከታተል አካል ሊኖር ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም መምህራን የማሰልጠንና ተማሪዎችን የማብቃት ተግባር እንዲከናወን በማድረግ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ይደረጋል ነው ያሉት።

Vous voulez que votre entreprise soit Service Du Gouvernement la plus cotée à Democratic Republic of the ?

Cliquez ici pour réclamer votre Listage Commercial.

Adresse


Democratic Republic Of The