ድሞክራሲ በተግባር

ድሞክራሲ በተግባር

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ድሞክራሲ በተግባር, Political organisation, tmujon07@gmail. com, Ma`adi.

01/12/2015
ethsat.com 16/11/2015

ethsat.com ethsat is the No. 1 Ethiopian news website. Ethiopian news, daily Ethiopian news esat radio and Video

Untitled album 24/10/2015
Photos 21/10/2015

ድሞክራሲን በተግባር ለማየት የናፈቀች ሀገር ኢትዮጵያ
ገዥው ፓርቲ ኢሒዴግ/የድሞክራሲ መሰል ጥገኛ መንግስት/ በኢትዮጽያ ህዝብ ላይ አምስት የምርጫ ቁማሮችን ጭካኔ በተሞላበት የሰባዊ መብት እረገጣ፣ ድብደባ እና ግድያ አሣልፎ እነሆ እንደለመደው
ሁለተኛውን የእርገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በማለት ለህዝቦቹ የተስፋ እንጀራ እያበላ የዘወትር ጾሎቱን ተሳስተው ከሽንኩርትና ቲማቲም ዘገባ በማይዎጡት ሚድያዎቹ ህዝብን ማደንቆር ጀምሯል ፡፡ ወያኔ ከህዝብ የነጠቀውን ስልጣን ለማራዘም በየቦታው ባደራጃቸው እውር አመራር ተብየዎች በራሳችው ስብሰባ እነኳን ምን እንደተባለ የማይሰሙ፣ ህዝብን ሊመሩ እና ሊየስተዳድሩበት በተሰጡት የክብር ወንበር ላይ የተኙ ፣ህዝብ ላይ የሚያንኮራፉ.፣ የመፎክር ጋጋታን ከማስተጋባት በስተቀር ቃል እና ተግባርን አገናኝተው ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት የማይሰጡ፣ ህዝብ በመልካም አስተዳደር እጦት ፣ በሙስና፣ በመንገድ፣ በውሃ፣ በመብራት ሲሰቃይ የራሳቸውን የስልጣን ጥማት ከባለሙያ እውቀት እየለመኑ ሲሻቸውም እያስፈራሩ የህዝብን ገንዘብ እና ንብረት እንደፈለጉ ይመናኙበታል፡፡
ለመሆኑ ወያኔ ስልጣን ላይ እንድቆይ ያደረጉት ምክንያቶች ምንድን ናቸው
የመጀመርያው ኢህድግ በተፈጥሮው ብቃት የሌላቸው እና የአጥፊ ሹማማንቶች ጥርቅም መሆኑ ነው፡፡ ለሀገር ፣ለወገን ያገልጋይነት መንፈስ የሌላቸው በየመድረኩ እና በየሆቴሉ እየተሰበሰቡ የንብላው ፣ የናጥፋው ማህበረሰብ ጥርቅም መሆኑ የማይካድ ሀቅነው ለዚህም በየመስርያ ቤቱ ያሉ ባለሙያች ምስክር ናቸው፡፡ እነዝህ የመሀይም ጥርቅሞች አጥብቀው ከሚፈሯቸው ጉዳዮች የአመራር ለውጥን ፣ ምርጫን ፣ በአመራርና በኤክስፐርት ደረጃ ከነሱ ሳንባ ውጭ የሚተነፍስን፣ በአጠቃላይ ሀገርን መምራት የሚስችል ብቁ ዜጎችን ከመካከላችው እንድቀላቀሉአቸው አይፈልጉም፡፡ ከኢሀድግ ውጭም አማራጭ የላቸውም፡፡ ብቃታቸውንም በሚገባ ፈትሸው የመንግስት ለውጥ ቢመጣ ከጨዋታ ውጭ እንደሚሆኑ እርገጨኛ ናቸው፡፡ ስለዚህ የነሱ አማራጭ የህዝብን እጅ እየጠመዘዙ ፣ ካለፉት ስረአቶች አንብበው ሳይሆን አፈታሪክ ጠይቀው እየለቃቀሙ በማነጻጸር፣ በማሸበር እና በማስፈራራት የኢህድግ የስልጫን ማራዘሚያ ሆነዋል፡፡ ኢሕድግም ብቃትን መሰረት ያደረገ ሹመትን አጥብቆ በመሸሽ 25አመትን አስቆጠረ፡፡
ሁለተኛው አለምን ለመቆጣጠር በሚሹ የምእራባዊያንን አወንታ ማገኘቱ ነው በመገኛና ብዙሀን እና በየስብሰባው የምእራባዊያንን መገናኛ ብዙሀንን በምሳሌነት በመጥቀስ የአድገናል የመፎክር ጋጋታ በስደት፣ በርሀብና ፍትህ በማጣት የተሰቃየውን የኢትዮጵ ህዝብ ግራ አጋብቶታል፡፡ ምእራባዊያን BBCን,CNNን ከኳታር የሚሰራጨውን AL JAZEERAን በመጠቀም የኢፔርያሊዝም ዘመቻቸውን በሚያጧጧጡፉበት በአሁኑ ወቅት ኢሕድግን የሚመስል እንደፈለጉ የሚጋልቡት ፈረስ እስካላገኙ ድረስ ኢትዮጽያ መንግስት አልባ ሆና መቀጠሏ አይቀረየ ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን በየመን የሳልህ መንግስት በህዝቡ ላይ ጭካኔ እና ግፍ እንድፈጽም ከምእራባዊያን የመሳርይ እርዳታ እንደሚደረግለት እና በተቃራኒው የምእራባዊያን ሀሳብ የማይቀበሉ የግብጹን ሙባረክን፣ የቱኒዚያውን ቤን አሊን አብዮቱን በማቀጣተል በ3 እና በ10 ቀናት ከስልጣን አንኮታኩተዋቸዋል በሊቢያም ሙሀመድ ጋዳፊን በተመሳሳይ ሁኔታ፡፡ በ1973 ዓ.ም በአሜሪካና በእንግሊዝ ተጽእኖ ስር የነበረችው ግብጽ ከመካካለኛው አረብ ሀገራት አፈንግጣ እስራኤል እንድትመሰረት እውቅና ከሰጠች ጀምሮ የእራባዊያን ቀኝ እጅ ሆና ትኖር እንደነበር ይታዎቃል፡፡ ምእራባዊያ የሙባረክ መንግስት ከጃቸው መውጣቱን ሲያውቁ ኢትዮጵያን እጇን ጠምዘው በቁጥጥራችው ስር ካዋሏት ሰንብተዋል፡፡ በአፍሪካ ቀንድም የስራ አስካጅ ስልጣንን ከግብጽ ተቀብላላች፡፡ የምእራባዊያንን አለኝታ ያገኘ መንግስት አህያም ይሁን ማን ነክቶት!!፡፡ ህዝብ በርሀብ እና በስደት እያለቀ ኢትዪጵያ አድጋለች የሚል መፎክር በራሱ የካቢኔ ጋሪዎች እና በምእራባዊያን ሚድያ የሚራገብለት ኢህድግ ደርቱን ነፍቷል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ንብረቱን ከማዘረፍ ባልተማረ ማሀይም ካቢኔ ከመጨቆን አልዳነም፡፡ ምርጫው ትክክል ነው፣ ድሞክራሲያዊ ነው ፣ ለሚሉት ጥያቄወችም ግፍና ጭቆና የደረሰበት የኢትዮጵያ ህዝብ እየዘበው የድሞክራሲ መሰል ጥገኛ አስተሳሰቡን ከምእራባዊያን የምስክር በህዝቡ ፊት ያነባል፡፡ ያልተማር የመሀይም አገዛዥ እንድቆም እንታገል!! አባቶጫችን ከምእራባዊያን ድማቸውን አፍሰው ነጻ ያወጧትን ሀገር ኢህድግ ለስልጣን አይሸጣትም!! ትውልድሆይ ንቃ ታሪክህን እዎቅ!!!!!!!

Want your business to be the top-listed Government Service in Ma`adi?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Tmujon07@gmail. Com
Ma`adi