ANRS Public Participation Coordination Office

Call Directions Contact the organization

ANRS Public Participation Coordination Office ANRS Public participation Coordination Office. Government Authority

27/10/2026
የህብረተሰብ ተሳትፎ (Community Participation) በማንኛውም የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ እጅግ ከፍተኛ እና አስፈላጊ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ። የኮምቦ...
24/10/2026

የህብረተሰብ ተሳትፎ (Community Participation) በማንኛውም የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ እጅግ ከፍተኛ እና አስፈላጊ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ከክፋለ ከተማ፣ የቀበሌ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር የህብረተሰብ ተሳትፎ መመሪያ ና ደንብ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ። ጥቅምት /14/2019 ዓ.ም ኮምቦልቻ ።

የማህበረተሰብ ተሳትፎ አሰራር እና አተገባበር መመሪያ ዙሪያ የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ መልሶ ማቋቋም ኘሮጀክት አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ደምስ አለባቸው ሰነድ ቀርቦ ውጤታማ ውይይት ተደርጐበታል ።

የኮምቦልቻ ከተማ የኘላንና ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ምስጌ ጥላሁን አንድን ልማት ዘላቂ፣ ውጤታማ እና ፍትሃዊ ለማድረግ የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።በመሆኑም በየአስተዳደር እርከኑ ያሉ አመራሮች ህዝባቸውን በማስተባበር ልማቱን ማፋጠንና የህዝቡን የልማት ፋላጎት መመለስ ያስፈልጋል ብለዋል።

የገንዘብ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ተሚማ እንድሪስ እና ም/ሀላፊው አቶ መሀመድ ይመር ህብረተሰባችን በልማቱ የሚያደርገውን ተሳትፎ ውጤታማነት ለማረጋገጥ መምሪያው ግልጸኝነት የሰፈነበት አሰራርን ተግባራዊ በማድረግና ውጤታማነቱን የማረጋገጥ ስራውን በሀላፊነት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ተሳታፊዎች የተሰጣቸውን ሀላፊነት በውጤታማነት አንደሚተገብሩ በመግለፅ መድረኩ ተጠቃሏል።

ምንጭ/// ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በክልል ደረጃ የአማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ።=======================ጥቅምት 5/2019 ዓ.ምየአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መን...
15/10/2026

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በክልል ደረጃ የአማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ።=======================
ጥቅምት 5/2019 ዓ.ም

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አታላይ ጥላሁን የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በክልል ደረጃ የአማካሪ ምክር ቤት በይፍ መቋቋሙን አስታወቁ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን አያይዘውም ልማት በመንግሥት አቅም ብቻ የማይሰራ መሆኑን ለአባላቱ አስገንዝበው ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ልማት በራሱ አቅም ሰርቶ የክልሉን ገቢ እንዲያሳድግ የህብረተሰብ ተሳትፎን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

በመቀጠልም የአብክመ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ወርቁ ያየህ በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰበሰቡ ሀብቶች በግልጽነት፣ የተጠያቂነት የአሠራር ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ማስተባበሪያ የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወርቁ ያየህ በማስቀጠል ለምክር ቤቱ አባላት የተቋሙን አደረጃጀት ተግባር እና ኃላፊነት ፣ ተቋሙ ከተቋቋመ ጀምሮ በ2018 ዓ.ም ያከናወናቸው ተግባራት እዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ለአማካሪ ም/ክር ቤቱ በጽሁፍ አቅርበዋል።

አማካሪ ምክር ቤቱም በቀረበው ፅሁፍ ጥያቄና አስተያየት ተሰጦበት ውይይቱ ተጠናቋል።

በተዘጋጀ የመመሪያ ረቂቅ ዙሪያ ከባለድርሻ እና አጋር    አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።መስከረም 29/01/2019 ዓ.ም ባ/ዳር  በአብክመ ህብረተሠብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሃብት አ...
09/10/2026

በተዘጋጀ የመመሪያ ረቂቅ ዙሪያ ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

መስከረም 29/01/2019 ዓ.ም ባ/ዳር

በአብክመ ህብረተሠብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሃብት አሰባሰብ እና አስተዳደር መመሪያ ረቂቅ ላይ ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ውይይት ተደርጓል።

ለውይይቱ ረቂቅ መመሪያውን የአብክመ ህብረተሠብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ወርቁ ያየህ በፓዎር ፖይንት አዘጋጅተው ሳቢ እና ማራኪ በሆነ አቀራረብ ለተሳታፊዎቹ አቅርበዋል።

ረቂቅ መመሪያው 30 አንቀጾች ያሉት ሲሆን ከዚህ ቀደም ወጥ ባልሆነ መንገድ ሲሰበሰብ የነበረውን ሃብት በአግባቡ እንዲሰበሰብ እና ጥቅም ላይ እንዲውል ሊያደርጉ የሚችሉ የአሰራር ማእቀፎች ተካተውበታል።

የልማት ኮሚቴ አደረጃጀት፣ የሃብት አይነቶች እና በህብረተሠብ ተሳትፎ ሊሰሩ የሚችሉ የፕሮጀክት አይነቶች እንዲሁም የግዢ እና ንብረት አሰተዳደር ማዕቀፎች የረቂቅ መመሪያው አካል እንደሆኑ ከገለጻው ማወቅ ተችሏል ።

አቶ ወርቁ ሰነዱን ሲያቀርቡ የሃብት አሰባሰብ ሂደቱ ባመዛኙ ፕሮጀክት ቤዝድ እንደሆነ ነው ከገለጻው ማወቅ የተቻለው።

ውይይቱን የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ መሠረት አዱኛ እና አቶ ወርቁ ያየህ የመሩት ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሡ ሃሳቦች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ወ/ሮ መሠረት በሚሠሩ የልማት ስራዎች የህብረተሠቡ ተሳትፎ መኖሩ የተሻለ ውጤት እንድናመጣ እና ህብረተሠቡ የተሠሩ የልማት ስራዎችን የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማውና እንዲ ጠብቃቸው ስለሚያደርግ የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራችን ወሳኝና አስፈላጊ ነው ብለው አጠቃለዋል።

እንኳን ለመስቀል እና ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!መስከረም 16/2019 ዓ.ምየመስቀል በዓል የፍለጋ፣ የጽናት፣ የብርሃን እና የእውነት መገለጫ ነው። ንግሥት ዕሌኒ የጠፋውን የጌታችን የ...
26/09/2026

እንኳን ለመስቀል እና ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

መስከረም 16/2019 ዓ.ም

የመስቀል በዓል የፍለጋ፣ የጽናት፣ የብርሃን እና የእውነት መገለጫ ነው። ንግሥት ዕሌኒ የጠፋውን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ለመፈለግ ባደረገችው ከፍተኛ ጥረት እና በደመራው ጭስ መሪነት እውነተኛውን መስቀል ማግኘት የቻለችበት ታላቅ ዕለት ነው። ይህ በዓል የተባበረ ክንድ፣ የማይናወጥ እምነት እና ተስፋን ወደ ስኬት እንደሚያደርሱ ያስተምረናል።

የኢትዮጵያዊያን መገለጫ የሆነው የደመራ በዓል በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል። ይህ ወቅት ክረምቱ አልፎ አደይ አበባ የሚፈካበት፣ ጨለማው በብርሃን የሚተካበት አዲስ ምዕራፍ በመሆኑ ለሁላችንም አዲስ ጥንካሬንና መነሳሳትን የሚሰጥ ነው።

ተቋማችን በዚህ በዓል ወቅት የተሰነቁትን የአንድነት፣ የሰላምና የፍቅር እሴቶች በመያዝ፣ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት እና የደስታ እንዲሆን በድጋሚ ይመኛል!

መልካም በዓል!!!

አብክመ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

ኢሜል አድሬስ
Email address= [email protected]
ፊስ ቡክ አድራሻ
https://www.facebook.- ANRS Public Participation Coordination Office
Telegram:- ANRS Public Participation Coordination Office

25/09/2026

የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን በራስ አቅም ለመፍታት በደብረታቦር፣ በጎንደር እና በጉባላፍቶ (ወልድያ) የህብረተሰብ ተሳትፎን የማሳደግ፣ የፋይናንስ እቅዶችን የማስተዋወቅ ስራዎች በስፋት እየተካሄዱ ይገኛሉ።

መስከረም 15/1/2019 ዓ.ም

በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር፦ የ2019 በጀት ዓመት የህብረተሰብ ተሳትፎ እቅድ ግምገማ ተካሂዷል። የከተማ አገልግሎት ገቢ አሰባሰብን ለማሻሻል አመራሩ በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል። በበጀት ዓመቱ በጥሬ ገንዘብ፣ በዕውቀቱ፣ በጉልበትና በቁሳቁስ 2.3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ለመሰብሰብ ግብ ተይዟል።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር፦ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን፣ ለ2019 በጀት ዓመት በህብረተሰብ ተሳትፎ በጥሬ ገንዘብ ከ3.1 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሁም በጉልበት ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዷል። አሰራሩን ግልጽና ከብልሹ አሰራር የጠራ ለማድረግም ያለደረሰኝ ይሰበሰብ የነበረው አሰራር ቆሞ በአዲስ አካውንት እንዲሰበሰብ፣ ክፍት የሰው ኃይል እንዲሟላና ጣምራ አካውንት በአስቸኳይ እንዲከፈት በጥብቅ ተልዕኮ ተሰጥቷል።

በጉባላፍቶ ወረዳ (ወልድያ)፦ የወረዳው ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ከሰራተኞችና ከቀበሌ ባለድርሻ አካላት ጋር በተከታታይ ባደረገው ውይይት፣ በ2019 በጀት ዓመት ከህብረተሰብ ተሳትፎ ከ170 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዷል። የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት የህዝቡንና የቀበሌ መዋቅሮችን ቅንጅታዊ ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ተገልጿል።

ባጠቃላይ በተለያዩ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የገቢ አሰባሰብ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄዎች ህዝባዊ የልማት ጥያቄዎችን በራስ አቅም ለመመለስ ትልቅ መነሳሳትን እየፈጠሩ ይገኛሉ።

ኢሜል አድሬስ
Email address= [email protected]
ፊስ ቡክ አድራሻ
https://www.facebook.- ANRS Public Participation Coordination Office
Telegram:- ANRS Public Participation Coordination Office

ተግባራትን በሚፈለገው መንገድ ለመፈፀም አመራሩ በትኩረት ይዞ መስራት እንዳለበት ተመላከተ፡፡መስከረም 6/2019 ዓ.ምበደብረታቦር ከተማ አስተዳደር የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስራዎችን እና የገቢ...
23/09/2026

ተግባራትን በሚፈለገው መንገድ ለመፈፀም አመራሩ በትኩረት ይዞ መስራት እንዳለበት ተመላከተ፡፡

መስከረም 6/2019 ዓ.ም
በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስራዎችን እና የገቢ ስራን አፈጻፀም ግምገማ እንዲሁም በህብረተሰብ ተሳትፎ እቅድ ላይ ትውውቅ ተደርጓል፡፡

በመድረኩ ላይ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የሪፎርም ስራዎች ክትትል ቡድን መሪ አቶ ወርቁ ሁኔ በ2018 በጀት ዓመት ተቋማትና ክፍለ ከተሞች የነበራቸውን የሪፎርም ስራዎች አፈጻፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በርካታ ተቋማት የሪፎርም ስራውን በጥሩ መንገድ ማስኬድ መቻላቸውን አንስተው ጥቂት ተቋማት እና ክፍለ ከተሞች ደግሞ ከሚጠበቀው በታች በመሆናቸው በትኩረት ይዘው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ መለሰ ፈንታ በ2019 በጀት ዓመት ሁለት ወራት የተከናወነውን የገቢ ስራ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በመደበኛ ገቢ ያለው አፈጻፀም በተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በአንጻሩ በከተማ አገልግሎት ገቢ ላይ ያለው አፈጻፀም ከዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን ገልፀው ገቢውን በተገቢው ሁኔታ ለመሰብሰብ ባለድርሻ ተቋማት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ሀላፊ አቶ ማሩ አሰፋ የ2019 በጀት ዓመት የህብረተሰብ ተሳትፎን እቅድ አቅርበዋል፡፡ 2 ቢሊየን 300 ሚሊየን ብር የሚሆን በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በቁሳቁስና በሌሎችም መንገዶች ህብረተሰቡን ለማሳተፍ መታቀዱን ገልፀው ከ600 ሚሊየን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ተሳትፎ ይደረጋል ተብሎ መያዙን ጠቅሰዋል፡፡

በህብረተሰብ ተሳትፎ በሚገኘው ሀብት የተለያዩ የልማት ስራዎች እንደሚሰሩ ጠቁመው እቅዱን ለማሳካት ሁላችንም በባለቤትነት መስራት አለብን ብለዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተሳተፉ አካላትም በሰጡት ሀሳብ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስራዎች የተግባራት ማሳለጫ በመሆናቸው ጥንካሬዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እና ክፍተቶችን እንደሚያስተካክሉ ገልፀው ተከታታይነት ያለው ድጋፍና እገዛ መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ገቢ ለማንኛውም ጉዳይ ወሳኝ በመሆኑ ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ ጥረት እንደሚያደርጉ አንስተው የህብረተሰብ ተሳትፎን በሚፈለገው መንገድ ለመሰብሰብ ማህበረሰቡን በደንብ ማስተባበር አለብንም ብለዋል፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ደበበ አክሎግ እንደተናገሩት የሪፎርም ስራዎች ትልቅ ፋይዳ ያላቸው በመሆኑ በአግባቡ መፈፀም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበው የገቢ ስራን በተሻለ ሁኔታ ለማስኬድ ሁሉም በባለቤትነት ይዞ መስራት እንዳለበት ጠቁመው የህብረተሰብ ተሳትፎ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን እንደገለጹት የሪፎርም ስራዎችን በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበው ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ ባለድርሻ ተቋማት በባለቤትነት ይዘው መስራት እንዳለባቸው ተናግረው የህብረተሰብ ተሳትፎን በሚፈለገው መንገድ ለመሰብሰብ ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደሴ መኮንን በበኩላቸው በየተቋማቱ ያለው የሪፎርም ስራዎች አፈጻፀም ሰፊ ልዩነት ያለው መሆኑን ተናግረው በጥሩ መንገድ የፈፀሙ ተቋማት አጠናክረው መቀጠል በአንጻሩ ዝቅተኛ አፈጻፀም ያላቸው ተቋማት ደግሞ ከችግራቸው ለመውጣት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበው ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ ሁሉም በትኩረት ይዞ ሊሰራ እንደሚገባ እናየህብረተሠብ ተሳትፎንም በሚጠበቀው ልክ ለመሠብሠብ መስራት አለብን ብለዋል።

ዘገባው የደብረታቦር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

እንኳን አደረሳችሁ የአብክመ ህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት !  ዻጉሜ 4/2018 ዓ.ምክቡራን ደንበኞቻችን፣ አጋሮቻችን እና መላው የተቋማችን ሰራተኞች፤                   ...
10/09/2026

እንኳን አደረሳችሁ የአብክመ ህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት !

ዻጉሜ 4/2018 ዓ.ም
ክቡራን ደንበኞቻችን፣ አጋሮቻችን እና መላው የተቋማችን ሰራተኞች፤ በቅድሚያ ፈጣሪ አመቱን በሰላም አሳልፎ ለሁለት ሺህ አስራ ዘጠኝ (2019) ዓመተ ምህረት አዲስ ዓመት በጤና ስላደረሰን ምስጋናችን የላቀ ነው።

ጽሕፈት ቤታችን የክልላችንን ሕዝብ በዕውቀቱ፣ በጉልበቱና በገንዘቡ በልማትና በመልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፍ በማስተባበር፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችንን በራሳችን አቅም ለመፍታትና የዜጎችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህል ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

በመሆኑም በ2022 ዓ.ም በህብረተሰብ ተሳትፎና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በራስ አቅም በመፍታት የጋራ ተጠቃሚነቱ የተረጋገጠበት ክልል የማየት ራዕያችንን ለማሳካት በአዲሱ ዓመትም የተጀመሩ የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን።

በአዲሱ ዓመትም ካለፈው ልምድ በመቅሰም፣ አገልግሎታችንን ይበልጥ በማዘመን እና ጥራቱን በማሻሻል ህዝባችንን በተሻለ ቁርጠኝነት ለማገልገል ዝግጁ ነን። 2019 ዓ.ም የተጀመሩ ስራዎቻችን የሚቀጥሉበት፣ አዳዲስ እቅዶቻችን የሚሳኩበት እና ተቋማችን ይበልጥ ወደ ላቀ ከፍታ የሚሸጋገርበት ዓመት እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለን።
አዲሱ ዓመት፦
o የሰላም፣ የፍቅር እና የጤና፣
o የብልጽግና እና የትጋት፣
o የስኬት እና የአዳዲስ እድሎች ዓመት እንዲሆንላችሁ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ይመኛል።

መልካም አዲስ ዓመት!

Address

Bahir Dar
Abba
461

Telephone

+251582201657

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Public Participation Coordination Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ANRS Public Participation Coordination Office:

Shortcuts

Share