Addis Ketema woreda 5 Communication

Call Directions Contact the organization

Addis Ketema woreda 5 Communication This is woreda 5 communication office .
(1)

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ...
05/10/2026

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።
05/10/2026

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ*********************7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥ...
05/10/2026

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ
*********************

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

በዚህም ወ/ሮ አየለች እሸቴን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

አቶ አህመድ ሺዴ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ።
05/10/2026

አቶ አህመድ ሺዴ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደስታ ሌዳሞን  ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መረጠአዲስ አበባ፤መስከረም 25/ 2019(ኢዜአ)፦የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደስታ ሌዳሞን   ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል።
05/10/2026

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደስታ ሌዳሞን ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መረጠ

አዲስ አበባ፤መስከረም 25/ 2019(ኢዜአ)፦የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደስታ ሌዳሞን ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል።

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙየኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀ...
05/10/2026

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህም ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

05/10/2026
ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር ዙሪያ ያላትን መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በማንኛውም ኃይል ሊቀየሩ አይችሉም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ...
05/10/2026

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር ዙሪያ ያላትን መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በማንኛውም ኃይል ሊቀየሩ አይችሉም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ መነሻ ስትሆን፣ ከሞላ ጎደል አብዛኛው የዓባይ ውሃ የሚመነጨው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ነው፡፡

ወንዙ ለናይል ወንዝ አጠቃላይ የውኃ መጠን 85 በመቶውን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም እና አስተዳደር ዙሪያ የሚደረጉ ማናቸውም ውይይቶች እነዚህን መሠረታዊ እውነታዎች ያገናዘቡ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡

በተመሳሳይ ቀይ ባሕር ኢትዮጵያ መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ ትስስር ያላት የውኃ አካል መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፤ በጊዜ ሂደት የፖለቲካ ድንበሮች ቢቀያየሩም ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር ያላት የጠበቀ ቁርኝት ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

የኢትዮጵያ ቅርብ የተባለው ድንበር ከባሕር ዳርቻው 48 ኪ.ሜ ብቻ ርቀት ላይ እንደሚገኝም አብራርቷል፡፡

በመሆኑም በቀጣናዊ የባሕር ላይ ጉዳዮች እና የደኅንነት መዋቅር ላይ የሚደረግ ማንኛውም ውይይት የኢትዮጵያን ሕጋዊ ጥቅሞች እና ከቀይ ባሕር ጋር ያላትን ዘላቂ ትስስር ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት ሲል አሳስቧል፡፡

እነዚህ መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በፖለቲካዊ ዲስኩር፣ በማስገደድ እርምጃዎች ወይም ሀገርን በማተራመስ ድርጊቶች ሊቀየሩ እንደማይችሉ የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ በተላላኪዎች አማካይነት የሚወሰዱ እርምጃዎች ወይም የጥቃት ድርጊቶች መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንደማይቀይሩት ሁሉ፣ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሕጋዊ ጥቅም፣ ሚና እና ኃላፊነት ሊያሳንሱት አይችሉም ሲል አስምሮበታል፡፡

ኢትዮጵያ ሰላማዊ ግንኙነትን፣ የጋራ መከባበርን እና ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር እንደምትቀጥል ያረጋገጠው ሚኒስቴሩ፤ ሉዓላዊነቷን፣ የግዛት አንድነቷን እና ዋነኛ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለመጠበቅ ምንጊዜም ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም የቀጣናው ተዋናዮች የጋራ ፈተናዎችን ከግጭት እና አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ተጎጂ ከሚሆንበት (ዜሮ-ድምር) አካሄድ ይልቅ፣ ገንቢ በሆነ ውይይት፣ በአጋርነት እና በመልካም ጉርብትና መርሆች ላይ ተመሥርተው እንዲፈቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መከናወን ተከትሎ፤ አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም. በይፋ ይመሰረታል።‎‎ኢ...
05/10/2026

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መከናወን ተከትሎ፤ አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም. በይፋ ይመሰረታል።
‎
‎ኢትዮጵያ- አዲሲቷ የተስፋ አድማስ
‎
‎ #የመደመርመንግሥት

ታላቁ የምስጋና፣ የፍቅር እና የይቅርታ መድረክ የሆነው የኢሬቻ በዓል አከባበር በወረዳ 5 አስተዳደር  (በምሥል)ሆረ ፊንፊኔ 2019 ዓ. ም
03/10/2026

ታላቁ የምስጋና፣ የፍቅር እና የይቅርታ መድረክ የሆነው የኢሬቻ በዓል አከባበር በወረዳ 5 አስተዳደር (በምሥል)
ሆረ ፊንፊኔ 2019 ዓ. ም

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Telephone

+251925470613

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ketema woreda 5 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ketema woreda 5 Communication:

Shortcuts

Share