02/11/2022
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 10 አስተዳደር
በዛሬው ዕለት
ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ
ለተሰው ጀግኖቻችን!!!
አረሳውም!!!
እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ!!!
ጥቅምት 24 መቼም አንረሳውም!!!
በሚሉ በርካታ የሀገር መከላከያ ሰራዊታችንን የሚያወድሱ፣ የሚዘክሩና ለማንኛውም ተልዕኮ ከጎኑ እንደምንቆም የሚገልፁ ድጋፎችን በማሳየት ጥቅምት 23/2013 ዓ/ም አጥቢያ በሰሜኑ ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ጠላት የፈፀመውን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት የሚገልፅ የፓናል ውይይት በርካታ የወረዳችን የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ተከናውኗል።
ላፍቶ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት
ጥቅምት 23/2015 ዓ/ም
30/10/2022
ላፍቶ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት
"መንግስት መጪው ትውልድን በመስራት ሀገርን የማሻገር ስራ ትኩረት ሰጥቷል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
መንግስት ትውልድን በመስራት ሀገር የማሻገር ስራ ትኩረት ሰጥቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሸገርን ማስዋብ ምዕራፍ ሁለት አካል የሆነውን የወዳጅነት አደባባይ ምዕራፍ ሁለት መርቀው ከፍተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚህ ወቅት ከለውጡ በኋላ ኢትዮጵያ ቁጥሩ ከፍ ያለ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች እንዳሏት ገልጸው ፥ ከተጨማሪ ግንባታ ይልቅ የቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲገነቡ መደረጉን አንስተዋል።
በዚህም ሰው ለሚሰራባቸው ነገሮች ቅድሚያ ተሰጥቶ ተሰርቷል እየተሰራም ይገኛል ነው ያሉት።
የወዳጅነት ምዕራፍ ሁለት ግንባታም ህፃናት የሚጫወቱባቸውና ጊዜያቸውን የሚያሳልፉባቸው ፕሮጀክቶችን ያካተተ እንደሆነም አንስተዋል።
ህፃናት ላይ መስራት የነገ ሀገርን የመገንባት አካል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በተያያዘ 9 ሚሊየን ህፃናትን መመገብ እንደተቻለም ገልጸዋል።
በፕሮጀክቱ የተካተቱ መጫወቻዎች ህፃናት የአካል ብቃት እየሰሩ አዕምሯቸውን የሚያበለፅጉባቸው እንደሆኑም ነው ያብራሩት።
ፕሮጀክቱ ለህጻናትና ታዳጊዎች ብቻ ሳይሆን በየትኛውም የእድሜ ክልል ለመገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችና ጎብኚዎች የሚሆን ስፍራ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በሌሎች አካባቢዎችም ሊደገም ይገባልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
የወዳጅነት ምዕራፍ ሁለት ለመጪው አንድ ሳምንት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በነፃ መጎብኘት እንደሚችሉም ነው ያስታወቁት፡፡
አሁን የሚታዩ ችግሮች ልጆች ላይ ያለመስራት ውጤት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለነገ ሀገር ግንባታ መሰረት የሚጥሉ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ብለዋል ሲል ከፋና ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ጥቅምት 20/2015 ዓ/ም
30/10/2022
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር
በዛሬው ዕለት በወረዳችን ከሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ
ውይይት እየተደረገ ይገኛል
በውይይቱ ላይ በፀጥታ ጉዳይ
በኑሮ ውድነት ላይ
በህገወጥነት ዙሪያ
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
የከተማ ግብርና ስራዎቻችን በማስቀጠል ዙሪያ
በህዳሴ ግድብ የመጨረሻ ስራዎች ማድረግ ያለብን ስራዎች
በስንዴ ምርታችን ላይ ያሳየነው መልካም እመርታ
ማስቀጠል ላይ እና
ከውጪ ሀገራት ጋር ያለን ግንኙነት
በተሻለ አጠናክረን መቀጠል ላይ
መስራት እንደሚኖርብን
ሰፊ ማብራሪያ የተደረገ ሲሆን መድረኩን የመሩት የወረዳችን
የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት
አቶ ቴዎድሮስ ዘመድኩን እና
የወረዳችን ምክትል ስራ አስፈፃሚና
የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተረፕራይዝ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት
ሲስተር አዜብ ተስፋዬ
እየመሩት ሲሆን
ከህብረተሰቡ የተገኙ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽም እየተሰጠባቸው ይገኛል።
ላፍቶ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት
ጥቅምት 20/2015 ዓ/ም
20/10/2022
ላፍቶ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን
----------------------------------
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
መንግስት በአፍሪካ ህብረት በኩል
በሚካሄደው
የሰላም ንግግር ላይ
ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን አስታወቁ
መንግስት በአፍሪካ ህብረት በኩል በሚካሄደው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።
አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ
የአፍሪካ ህብረት የሰላም ንግግሩ የፊታችን
ሰኞ ጥቅምት 14 ቀን
በደቡብ አፍሪካ እንደሚካሄድ
ማሳወቁን ጠቅሰዋል።
መንግስትም በዚህ የሰላም ንግግር ላይ
ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጹት።
ሆኖም አሁንም መንግስት የኢትዮጵያን
ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚወስደውን
የመከላከል እርምጃ ለማጠልሸት፣ የሀሰት ክስን ለመሰንዘርና የሰላም ሂደቱን
ለማደናቀፍ
በሚጥሩ አካላት ላይ የተሰማውን ቅሬታ ገልጸዋል።
19/10/2022
ላፍቶ ወረዳ 10 አስተዳደር
*********************
#በዛሬው ዕለት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ 2015 ዓ/ም #የ1ኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት #ለባለ ድርሻ አካላት አቅርቧል በሪፖርቱ ላይ በጥንካሬና በክፍተት
የታዩ ስራዎች
በቀጣይ የተሻለ አድርጎ ለመስራት
የጤና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ከዚህ በፊት ሲያሳዩ የነበረው ጥንካሬ አጠናክረው መቀጠል እንደሚኖርባቸው የወረዳው
ጤና ጣቢያ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት #ቴዎድሮስ ጌታቸው
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ
አቶ #መንግስቱ መሀሪ
የክ/ከተማ ጤና ፅቤት ኃላፊ የሆኑት
ወ/ሮ #ቅርስነሽ ደጉ
ለተሰሩ ስራዎች ምስጋናቸውን በመግለፅ ለቀጣይ ስራዎች እንዲበረቱ አሳስበዋል።
ላፍቶ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ፅቤት
***************************
ጥቅምት 9/2015 ዓ/ም
*******************
19/10/2022
ላፍቶ ወረዳ 10 አስተዳደር
*********************
#በዛሬው ዕለት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ 2015 ዓ/ም #የ1ኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት #ለባለ ድርሻ አካላት አቅርቧል በሪፖርቱ ላይ በጥንካሬና በክፍተት
የታዩ ስራዎች
በቀጣይ የተሻለ አድርጎ ለመስራት
የጤና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ከዚህ በፊት ሲያሳዩ የነበረው ጥንካሬ አጠናክረው መቀጠል እንደሚኖርባቸው የወረዳው
ጤና ጣቢያ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት #ቴዎድሮስ ጌታቸው
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ
አቶ #መንግስቱ መሀሪ
የክ/ከተማ ጤና ፅቤት ኃላፊ የሆኑት
ወ/ሮ #ቅርስነሽ ደጉ
ለተሰሩ ስራዎች ምስጋናቸውን በመግለፅ ለቀጣይ ስራዎች እንዲበረቱ አሳስበዋል።
ላፍቶ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ፅቤት
***************************
ጥቅምት 9/2015 ዓ/ም
*******************
19/10/2022
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 10 አስተዳደር
#በዛሬው ዕለት በወረዳችን
በመንግስትና በህዝብ
እየተሰሩ ያሉ ስራዎች
ያሉበት ደረጃ የተገመገመ
ሲሆን በሁለተኛነት
ውይይት የተደረገበት
አጀንዳ በቀን 12/02/2015 ዓ/ም የሀገራችንን ሉዓላዊነትና አንድነት ለመሸርሸር ሌት ተቀን
ከውስጥና ከውጪ እየሰሩ ያሉ ጠላቶቻችንን
ለማውገዝ መላውን የወረዳችን ማህበረሰብ በመቀስቀስ
የጠላትን አጀንዳ ማፍረስ
እንደምንችል ማሳያ ተልዕኮ ስለሆነ
ሁሉም አመራር በዕኩል ስሜት መንቀሳቀስ የኖርብናል ሲሉ
የወረዳችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ መሀሪ እና የወረዳችን የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት/ሮ ዘይነባ ጀማል እንዲሁም የክ/ከተማ ደጋፊ አመራሮች አሳስበዋል።
ላፍቶ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት
ጥቅምት 8/2015 ዓ/ም
26/09/2022
#የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
====================
#የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር በዛሬው ዕለት ታሪካዊውና በሀገራችን ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ስም ያለው የመስቀል ዳመራ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በወረዳችን ነዋሪዎች ስም ያስተላለፉ ሲሆን
በዓሉ የሰላም
የጤና
የበረከት
የአንድነት
የፍቅር
የመተሳሰብ
ያለንን በጋራ የምንጠቀምበት
እንዲሆንልን በማለት የወረዳችን ዋና ስራ አስፈፃሚ
#አቶ መንግስቱ መሀሪ
--------------------------
ላፍቶ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት -------------------------------------------
መስከረም 16/2015 ዓ/ም -----------------------------------
26/09/2022
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 10
********************************
የፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት የመስቀል ዳመራ የሚደመርበት የብሄረ ፅጌ ማሪያም ቤተክርስቲያንና ዙሪያውን ፅዳት የማፅዳት ስራ የተሰራ ሲሆን የወረዳ 10 እና የወረዳ 07 አመራሮችና የፅዳት ሰራተኞች፣ የፖሊስ አካላት፣ የሽርክና ማህበራት፣ ወጣቶች እና የብሎክ ነዋሪዎች በፅዳት ዘመቻው ላይ ተሳትፈዋል፤ የፅዳት ስራውን ያስተባበሩት የወረዳችን ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አቡሌ አለሙ እና ባለሙያዎቻቸው ዛሬ የተካሄደው ፅዳት በዓሉን ምክንያት በማድረግ ሲሆን በቀጣይ ግን ሁሉም አካባቢውን የማፅዳት ግዴታውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
ላፍቶ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት
መስከረም 16/2015 ዓ/ም