06/10/2026
የኢ-ላንድ ሲስተም ሙሉ ለሙሉ ሊተገበር ነው!
---------------------------------
መስከረም 26/2019 ዓ.ም
(የመ/ይ/ም/መ/ኤ) AA-LHRIA
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ከነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት የጀመረውን የኢ-ላንድ (e-Land) ኦንላይን አገልግሎት አሰጣጥ የበለጠ ለማጠናከር እና ቀልጣፋ ለማድረግ ለባለሙያዎቹ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በልደታ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ዲጂታል ላይብረሪ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ስልጠና ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ 180 ለሚሆኑ ባለሙያዎች እና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ዳይሬክተሮች በአራት ዙር ተከፋፍለው በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በዛሬው ዕለትም 39 የሕግ ባለሙያዎች እና ዳይሬክተሮች ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ። የስልጠናው አስተባባሪ እና የኦንላይን አገልግሎት ቡድን መሪ ወ/ሮ ሀና አይቸው እንደገለጹት፤ የስልጠናው ዋና ዓላማ ባለሙያዎች ስለ ኢ-ላንድ ሲስተም ተመሳሳይና ግልጽ ግንዛቤ ኖሯቸው ወጥነት ያለውና ቀልጣፋ አገልግሎት ለህብረተሰቡ እንዲሰጡ ለማስቻል ነው ብለዋል።
የኢ-ላንድ አገልግሎት የከተማ አስተዳደሩ የስማርት ኦፊስ (Smart Office) ትግበራ አካል መሆኑን የጠቆሙት ወ/ሮ ሀና፣ በአሁኑ ወቅት የስም ዝውውር፣ የካዳስተር ቅጂ፣ የእዳ እገዳና ስረዛ እንዲሁም የባንክ ብድር ምዝገባ እና ስረዛ አገልግሎቶች በኦንላይን በመሰጠት ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ተገልጋዮች እስካሁን እየተሰጠ ባለው የኢ-ላንድ አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸውን የጠቆሙት አስተባባሪዋ፣ የባለሙያዎች ስልጠና እንደተጠናቀቀ ከሰልጣኞች አስፈላጊው ግብዓት ተሰብስቦ ሲስተሙ በይፋ በመመረቅ በስፋት ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉Website; https://addiscadaster.gov.et/
👉Facebook; Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information
👉TikTok; A.Acadaster2016
👉Telegram; https://t.me/lhria
👉you tube; Legal cadaster
👉Customer Call Center: 6577
addiscadaster.gov.et (https://addiscadaster.gov.et/)
Addis Ababa City Administration Landholding Registration and Information Agency | Home Page